(ኢሳት ዜና፣ መስከረም 3 ቀን 2010 ዓም) በኬንያ 60 ኢትዮጵያዊያን በፖሊስ ተያዙ
በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው የነበሩ 60 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአገሪቱ ፖሊስ አስታወቀ።
የናይሮቢ የፖሊስ ኮማንደር ጆሴፍ ኮሜ ፣ ''ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች እሁድ እለት ነው ናይሮቢ የገቡት። በስተምስራቅ ናይሮቢ በኪዮሌ ሚሃንጎ አካባቢ በአንድ መኖሪያ ቤት ውስጥ ተደብቀው ባሉበት ነው የያዝናቸው” ብለዋል።
በስፍራው ስናገኛቸው በአንድ ቤት ውስጥ ታጭቀው ደረቅ ዳቦ እየበሉ ለጤና አስጊ የሆነ አንድ መጸዳጃ ቤት በጋራ ይጠቀሙ ነበር። ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ምንም ዓይነት ሕጋዊ የሆነ የመኖሪያ ፈቃድ ስለሌላቸው በሕግ ይጠየቃሉ። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች ፍርዳቸውን ሲጨርሱ ወደ አገ...ራቸው እንዲመለሱ ይደረጋሉ።'' ብለዋል።
ፖሊስ በተለያዩ ጊዜያት ደቡብ አፍሪካ እና ወደ አውሮፓ አገራት ለመሻገር በኬንያ የተለያዩ ከተሞች በህገወጥ መንገድ የሚገቡ ስደተኞች ያሉ ሲሆን አብዛሃኞቹ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች መሆናቸውንም አዛዡ አክለው አስታውቀዋል።
ሕገወጥ ስደተኞችን የሚያዘዋውሩ ደላላሎች መኖራቸው እና እነሱን ለመያዝ ጥረት እንደሚደረግም ፖሊስ እና የስደተኞች ጉዳይ በጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል። ባለፈው ሳምንትም በተመሳሳይ 13 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም ዥንዋ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment