በኢትዮጵያ በድርቅ የተጠቃው ህዝብ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልገው ታወቀ፡፡ በአሁን ሰዓት በኢትዮጵያ 8 ነጥብ 7 ሚሊዬን ሰው በድርቅ መጠቃቱ ይታወቃል፡፡ ለድርቅ ተጎጂዎቹ በአብዛኛው ድጋፍ እየተደረገ ያለው በውጭ ረድኤት ተቋማት ሲሆን፣ በዚህ ውስጥ የመንግስት ሚና እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ የውጭ ተቋማት ለድርቅ ተጎጂዎቹ በገንዘብም ሆነ በቁስ ድጋፍ እያደረጉ ቢሆንም፣ ከተረጂው ሰው ቁጥር አንጻር ግን እርዳታው በቂ ሆኖ አልተገኘም፡፡
የውጭ ተቋማት እያደረጉ ያሉት ድጋፍ በትክክል ቢሰላ በበቂ ሁኔታ ሊከፋፈል የሚችለው ለ6 ሚሊዬን ሰዎች ብቻ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ለሁሉም ማለትም ለ8 ነጥብ 7 ሚሊዬን ህዝብ እርዳታውን ለማዳረስ ሲባል ብቻ፣ እርዳታውን ብዙ ቦታ የመቀነጣጠብ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይህም እየተደረገ ያለው የተገኘውን እርዳታ ለሁሉም ለማዳረስ ሲባል መሆኑን የገለጹት መረጃዎች፣ በዚህ ሁኔታ ብዙም መንገድ መጓዝ አዳጋች መሆኑንም ጠቁመዋል-መረጃዎቹ፡፡
No comments:
Post a Comment