በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች እንደሚሉት መስከረም ከጠባ ጀምሮ ሰላም አላገኙም፡፡ ከአፋር ክልል ጋር ኩታ ገጠም በሆኑ አካባቢዎች ከሐምሌ 2008 ዓ.ም ጀምሮ ሲግም ሲቀዘቅዝ የቆየው የወሰን ግጭት ዳግም አገርሽቶ ሰዎች ተገድለዋል፡፡ የሰሞኑ ግጭት የተቀሰቀሰው መስከረም 2 ቀን 2010 ዓ.ም እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ ትላንት ምሽት በአካባቢው ተኩስ ይሰማ እንደነበር ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለዶይቼ ቨለ ተናግረዋል፡፡
...
“ግጭቱ እንደቀጠለ ነው፡፡ አሁንም ትላንትም ተኩስ ነበር፡፡ ከትላንት በስቲያም ተኩስ ነበር፡፡ ያው ከባድ የተኩስ ልውውጥ አለ፡፡ ትላንትና ማምሻ ከሁለት ሰዓት እስከ አራት ሰዓት የተኩስ ልውውጥ ነበረ፡፡ ያው በሁለቱም ወገን ግን የሞተ የለም፡፡ ከአፋር ወገን ግን አንድ አራት የቆሰለ ሰው አለ” ይላሉ ነዋሪው፡፡
ግጭቱ የደረሰበት ቦታ ጃራ ተብሎ የሚታወቅ እና ከወልዲያ ወደ አሳይታ በሚወስደው መስመር ላይ ባለ ቦታ እንደሆነ ነዋሪው ያስረዳሉ፡፡ ትላንት አምቡላንስ በአፋር ወገን የቆሰሉትን ሰዎች ሲያመላልስ እንደነበር ከጭፍራ ከተማ ነዋሪዎች መስማታቸውን ይናገራሉ፡፡ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የሚያረጋግጡት ሌላው የአካባቢው ነዋሪ አካባቢው “አለመረጋጋቱን” እና በአማራ እና አፋር ወገን ያሉ ሰዎች በ“አፈ ሙዝ ፍጥጫ ውስጥ” እንዳሉ ያስረዳሉ፡፡ በሰሞኑ ግጭት ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ እኚሁ ነዋሪ ይገልጻሉ፡፡ #DWAmharic #MinilikSalsawi
Seግጭቱ የደረሰበት ቦታ ጃራ ተብሎ የሚታወቅ እና ከወልዲያ ወደ አሳይታ በሚወስደው መስመር ላይ ባለ ቦታ እንደሆነ ነዋሪው ያስረዳሉ፡፡ ትላንት አምቡላንስ በአፋር ወገን የቆሰሉትን ሰዎች ሲያመላልስ እንደነበር ከጭፍራ ከተማ ነዋሪዎች መስማታቸውን ይናገራሉ፡፡ የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የሚያረጋግጡት ሌላው የአካባቢው ነዋሪ አካባቢው “አለመረጋጋቱን” እና በአማራ እና አፋር ወገን ያሉ ሰዎች በ“አፈ ሙዝ ፍጥጫ ውስጥ” እንዳሉ ያስረዳሉ፡፡ በሰሞኑ ግጭት ሶስት ሰዎች መሞታቸውን ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ እኚሁ ነዋሪ ይገልጻሉ፡፡ #DWAmharic #MinilikSalsawi
No comments:
Post a Comment