መስከረም 18፣2010
በአዲስ አበባ የሚገኙ ሁለት የነገሥታት ሃውልቶችና ሶስት ጥንታዊ ቤቶች እድሳት ሊደረግላቸው ነው፡፡
መንግስት ለሃውልቶቹና ለጥንታዊ ቤቶች እድሳት 3ዐ ሚሊዮን ብር በጀት መመደቡንም የአስተዳሩ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡
እድሳት የሚደረግላቸው ሃውልቶች የአፄ ሚኒልክና የአፄ ቴዎድሮስ ሃውልቶች መሆናቸውንም ቢሮው አስታውቋል፡፡
የአዲስ አበባ የመጀመሪያው ከንቲባ ቢትወደድ ወልደፃድቅ ጎሹ መኖሪያ ቤት፣ የሼክ ኦጄሌ አል ሀሰን ቤተ መንግሥትና በአሁኑ ጊዜ የአራዳ ፍርድ ቤት ሆኖ የሚያገለግለው የቀድሞ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትም እድሳት የሚደረግላቸው ጥንታዊ ቤቶች ናቸው፡፡
የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወርቁ መንገሻ ሃውልቶቹ የተቀመጡት አደባባይ ላይ በመሆኑ ለጎብኚዎች የማይመቹ ቢሆንም የትራፊክ እንቅስቃሴን በማይረብሽ መልኩ እንዲጎበኙ ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
No comments:
Post a Comment