Tuesday, September 19, 2017

በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላትና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል ከፍተኛ ተኩስ ሲካሄድ አድሯል።

መረጃ ESAT DC
በምስራቅ ጉጂ፣ ከቡሌ ሆራ 80 ኪሜ ርቆ በሚገኘው ዳዋ እና ቡሌ ካሀር በሚባሉ ቀበሌዎች ላይ በሶማሊ ልዩ ሃይል አባላትና በኦሮሞ ተወላጆች መካከል ከፍተኛ ተኩስ ሲካሄድ አድሯል። ጦርነቱ አሁንም ቀጥሎአል። ግጭቱ ወርቅ በሚቆፈርበት አካባቢ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።ትናንት ከሶማሊ ክልል ተፈናቅለው ወደ ሃረር በመጓዝ ላይ የነበሩ ዜጎች የተሳፈሩበት ሲኖ ትራክ መኪና ኮምቦልቻ ፋጤ በሚባለው ዳገት አካባቢ በመገልበጡ 6 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ፣ 3ቱ ሆስፒታል ገብተዋል። ማፈናቀሉ አሁንም ቀጥሎአል።

No comments:

Post a Comment