Friday, September 15, 2017

ምስራቅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት የሕዝብን እልቂት እያደረሰ ነው ።


ሕወሓት መራሹ የኢሕአዴግ አገዛዝ የውስጥ ሽኩቻውንና የመስፋፋት ድብቅ አላማውን ለማስፈፀም በሰሜንና ምስራቅ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጦርነት በመክፈት የሕዝብን እልቂት እያደረሰ ነው ።Minilik Salsawi የኢሕአዴግ የውስጥ ሽኩቻ የፈጠረው የምስራቅ ኢትዮጵያ ግጭትና በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የተቃጣ ግድያና ማፈናቀል እንዲሁም የሕወሓት የመስፋፋት እቅድ በጎንደር የአማራ ሕዝብ ላይ በቅማንት ሪፍረንደም ሽፋት እልቂት ደግሶ ሕዝቡን ለመፍጀት ቅልብ ጦሩን አሰማርቷል ። ይህ በሕወሓት የጦር መሪዎችና የደሕንነት ሹሞች በጋራ የሚመራው መንግስታዊ ሽብር የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በኦሮሞ ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን አሰቃቂ ጥቃት ለመቃወም በሐረር ህዝባዊ ተቃውሞ እየተደረገ ይገኛል፡፡ የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ተቃውሞ አቅራቢዎች በቀጥታ... በመተኮስ የሰው ህይወት መቅጠፋቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የሟቾች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ አልተረጋገጠም ። የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል በጅጅጋ ይኖሩ በነበሩ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ በፈጸመው ጥቃት ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል፡፡ የሟቾች አስከሬን ወደ ሐረር ሲጓጓዝ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ ትዕዛዝ ከጅጅጋ የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆች ወደ ሐረር እየተወሰዱ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮችም ሐረር ያለመጠለያ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡
ደም የተጠማው የሕወሓት አገዛዝ ለመስፋፋት እቅዱን ለማሳካት በቅማንት ሕዝበ ውሳኔ ስም የአማራውን ሕዝብ ለመፍጀት ገዳይ ሰራዊቱን በጎንደርና ሕዝበ ውሳኔ በሚካሔድባቸው አከባቢዎች አስፍሯል ። እንዲሁም ለሕዝበ ውሳኔው ተሳታፊ እንዲሆኑ የአከባቢው ነዋሪ ያልሆኑ አባሎቹን ሐሰተኛ መታወቂያ በመስጠት በአከባቢው አምጥቶ በማስቀመጥ የማጭበርበር ተግባሩን ለመፈፀም እየተሯሯጠ ነው ። ሕዝብ ያልቀበለውን የምርጫ ሒደት በኃይል ለማወጅ መንግስታዊ ሽብሩን እየገፋበት ነው ። ተጨማሪ ሰራዊት ኦሮሞና ሶማሌን በምስራቅ እያባለ የዐማራን ደም ለማፍሰስ ደግሞ ወደ ጎንደር በገፍ እየተጓዘ ነው፡፡ በጎንደር፣ በጭልጋና መተማ አካባቢዎች ከነዋሪው እኩል ቁጥር ያለው አጋዚ ገብቷል፡፡ ፈታኝ ጊዜ ላይ በመሆናችን በአንድነት ልንቆም ይገባል ። #MinilikSalsawi
Se mer

No comments:

Post a Comment