የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት የሆነው ህወሓት እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ፣ በዚህኛውም ዓመት ምንም ዓይነት የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት ፈቃደኛ አለመሆኑ ታወቀ፡፡ ፓርቲው አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር ከሚረጨው ፕሮፓጋንዳ ውጭ ምንም የተለየ ነገር እንደማይፈጥር የሚገልጹ ታዛቢዎች፣ ህወሓት ሊለወጥ የሚችለው በሌላ ስርዓት ሲለወጥ ብቻ መሆኑን ያሰምሩበታል፡፡ በአዲሱ ዓመት እንደተለመደው ሁሉ፣ ሰዎች በፖለቲካ አመለካከታቸው መታሰራቸው እንደሚቀጥልም የህወሓትን የስነ ፖለቲካ ባህሪ በቅርብ የሚከታተሉ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡
ድርጅቱ ላለፉት አስር ቀናት ‹‹የአንድነት ቀን የፍቅር ቀን…›› እያለ ፕሮፓጋንዳ ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ከዚህ ቀደም ተጨንቆበት ስለማያውቅበት የአንድነት ፖለቲካ ሲሰብክ የቆየው ህወሓት፣ በጳጉሜ ወር የአንድነት ቀን የሚል የፕሮፓጋንዳ በዓል ማክበሩ ይታወቃል፡፡ ከወሬ እና ከባዶ ፕሮፓጋንዳ የተለየ ነገር ሲያደርግ የማይስተዋለው ህወሓት፣ የፍቅር ቀን ብሎ ባከበረበት ቀን፣ የተለያዩ የተቃዋሚ ፖለቲካ ኣራማጆች ለእስር መዳረጋቸውንም ለማወቀ ተችሏል፡፡
በርካታ የፖለቲካ እስረኞች እስር ቤት እየማቀቁ ባሉባት ኢትዮጵያ፣ ዘመን ቢለዋወጥ ብቻውን ትርጉም እንደማይኖረው የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ ከዘመን ጋር የስርዓት ለውጥ አልያም የስርዓት ባህሪ ለውጥ ሊኖር እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡ ህወሓት ከስልጣን በፊት ጫካ እያለ እና ወደ ስልጣን ከመጣ በኋላ ሲከተለው የቆየው አጥፊ የፖለቲካ አካሔድ፣ ዘንድሮ መጨረሻው ይሆን ዘንድም ታዛቢዎቹ ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

No comments:
Post a Comment