Saturday, September 23, 2017

የመለስ ራእይና የከፍታው ዘመን?


የመለስ ራእይና የከፍታው ዘመን?  – BBN
የአክሱም ሙስሊሞች በህገመንግስት የተረጋገጠ መብታቸዉን ተነፍገዋል። አክሱማዊ ስርኣት የነበረው ክርስትናና እስልምና ኢትዮጵያ ከመግባታቸው በፊት ቢሆንም ከተማይቱ በእብሪት በተወጠሩ ባለ ስልጣናት ቅድስት ተደርጋ መስጊድ መስራቱ እርም ተደርጓል።
ቁጥራቸው ከ15ሺ የሚበልጥ የከተማዉ ነዋሪዎች የአርብ ስግደትን (ጁመአ ሶላትን) በየሰው ቤትና መተላለፊያ ላይ በመስገድ ጭቆናን በጫንቃቸው ላይ ተሸክመው ይኖራሉ። ሙስሊሞቹ መስገጃ ቦታ ብቻ ሳይሆን የመቃብር ቦታ ተነፍገው ሞት ሲከሰት የሙት አስክሬንን እያንገላቱ ከከተማዉ ራቅ ወዳለ ቦታ ወስደው እንዲቀብሩ ይገደዳሉ። የሙስሊም አስክሬን ለአክሱም ምስጥና አፈር የማይመጥን ተደርጎ በድርብ ጭቆና መሰቃየቱ የህወሃት ትሩፋት ሆኗል።ባንጻሩ ግዙፍ መስቀል ትግራይ ዉስጥ ሲተከል ይታያል።

ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ለዘመናት የሚደርስባቸውን ጭቆና በመቻል ቢኖሩም መቻሉ በቂ አይደለም ለማለት እስኪያስመስል ህወሃት የእምነት አንጃን ከሊባኖስ አምጥቶ ለመጫን ሲሞክር በቃህ መባሉ ይታወቃል።ህዝብ ተሰባስቦ ወኪል መርጦ ህወሃትን ስማኝ ቢልም ህወሃት ለሰላማዊ ጥያቄው የሰጠው ምላሽ ግድያን፣እስርን፣ዝርፊያን፣ድብደብባን መፈጸም ነበር።
ስድስት የትግል አመታት ተቆጠሩ።ህወሃት የማይታረም፣የማይለወጥና በጸረ-ሙስሊም አቋሙ የጸና ቢሆንም ይህንን የእብሪት አባዜውን በአገርም በዉጪም በመቀናጀት መታገል ሲገባ ጭቆናዉ ይለመድ ዘንድ ነገሮችን ለማላዘብ የሚደረጉ ጥረቶች ሲታዩ ያሳዝናል የሚል፡አስተያየት ተበራክቷል።
ህወሃት እንደሚሄድ ያዉቀዋል።ህወሃት ዘላለማዊ እንዳልሆነ ያዉቀዋል። ግን ከመሔዱ በፊት የስልጣን ኮርቻዉን ያዛነፉበት ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞችን መበቀል ይሻል።ለሚቀጥለው ትዉልድ ህወሃት የጥፋት መርዝን ቀብሮ ለማለፍ እየሰራ ነው።በመሆም ይህንን አምባገነናዊ ስርኣት አለም አቀፋዊ ህጎች በሚፈቅዷቸው የትግል ዘይቤዎች ታግሎ ለውጥን ማምጣቱ ግድ ነው የሚል ጣምራ ድምጽ ቢሰማም ይህንን ድምጽ ለማፈን የዉስጥም የዉጪም ጥረቶች ይሰተዋላሉ።
ለመሆኑ የአክሱም ሙስሊሞች መስጊድን መስራት ተከልክለው ግዙፍ መስቀልን በትግራይ ዉስጥ መትከሉን እንዴት ታዩታላቹ?

No comments:

Post a Comment