Friday, September 15, 2017

አሣዛኝ ዜና …. በሶማሌ ክልል ወደ 40 የሚጠጉ የኦሮሞ ተወላጆች ወያኔ(ህወሃት) በሚደግፈው በሶማሌ መንግስት በግፍ ተገድለው እሬሣቸው ወደ ሃረር ተልኳል።




By ሳተናውSeptember 15, 2017 01:08
  






ሞገስ ሞኮነን
ብዛት ያላቸውም የኦሮሞ ተወላጆች ተደብድበውና ተፈነካክተው ፡የሚኖሩትን ህይወት፡ቤትና ንብረታቸውን ጥለው ወደ ሃረር ተሰደዋል።
ይህ ድርግት እየተፈፀመ ያለው፡ በሱማሌ ህዝብና በኦሮሞ ህዝብ መሃከል ሣይሆን፡ ገዢው መንግስት ሆን ብሎ ስልጣኑን ለማራዘም፡ የሶማሌን መንግስት በማገዝ ፡የኦሮሞ ተወላጆች ላይ በደል ለመፈፀም ሆን ተብሎ፡ ታቅዶበት የሚደረግ ሴራ ነው።
በሰሜን ጒንደርም ወያኔ ስልጣኑን ለማራዘም የቅማንት ህዝብን ከአማራው ጋር ለማጋጨት ያሴረው ሴራ ዛሬ ላይ ከሽፏል።
ወያኔ በሰሜን ጒንደር የቀበሌዎች የክልል ሪፈረንደም በማለት ለምርጫ የትግራይ ሰዎችን ቀንና ለሊት እያጓጓዘ በአካባቢው እያሰፈረ ይገኛል።
ይህ ሃገር ለማተራመስ፡ ገዢው መንግስት ጠዋትና ለሊት እንቅልፍ አጥቶ እየሰራ ነው።
ህዝብ እና ህዝብ መናቆሩን ትተን፡ነገሩ እየከፋና እየበረታ ከመምጣቱ በፊት ፊታችንን ገዢው መንግስት ላይ በማተኮር ፡በመደራጀትና በወኔ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ወያኔን አሶግደን የነፃነት ችቦዋችንን እናብራ። አለበለዚያ እንደሰም በነን፡ እንደሻማ ቀልጠን እንጠፋለን።

No comments:

Post a Comment