Sunday, September 10, 2017

የሕወህት ድራማ – “ምህረት አደረኩ እያለን ነው” #ግርማ_ካሳ


By ሳተናውSeptember 10, 2017 17:05



በአሥር ሺሆች ከሚቆጠሩ የሕሊና/ፖለቲካ እስረኞች መካከል ሕወሃት 697 እስረኞችን ፈታው ብሎ “መሀሪነቱን” ሊነግረን እየሞከረ ነው። አንደኛ እነዚህ ተፈቱ የተባሉቱ አብዛኞቹ በሙስና ተከሰው ታስረው የነበሩ፣ ዘመዶቻቸው ወዳጆቻቸው ከአገዛዙ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ መገመቱ አስቸጋሪ አይደለም።
አገዛዙ አሁንም በሕዝብ የተወደዱ፣ ህዝብ እንዲፈቱ በተደጋጋሚ ጥያቄ ሲያቀርብላቸው የነበሩ፣ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆችን አሁን በወህኒ እያሰቃየ፣ ህዝብን እያሸበረና እያወከ ለመቀጠል መወሰኑን ይሄ አስቂኝ ፣ የሕወሃት ድራማ ፣በግልስጽ የሚያመላክት ነው። ቀደም ሲል በዘገብኩት መሰረት የእሕሊና እስረኞች እንደማይፈቱ ገለዤ ነበር።
1. ዶር መራራ ጉዲና (የኦፌኮ ሊቀመነበር)
2. ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ የወልቃይት ኮሚቴ አባል
3. አንዱዓለም አራጌ የአድንነት ፓርቲ ም/ፕሬዘዳንት
4. እስክንደር ነጋ (ጋዜጠኛ)
5. ተመስገን ደሳልኝ (ጋዜጠኛ)
6. ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ የቀድሞ የሕዝብ ግንኙነት ክፍላ ሃላፊ
7. ናትናኤል መኮንን የአንድነት ምክር ቤት አባል
8. ኦልባና ለሌሳ የኦፌኮ አመራር አባል
9. በቀለ ገርባ የኦፌኮ ም/ፕሬዘዳንት
10. አንዱዋለም አያሌው የአንድነት አባል
11. አንጋው ተገኝ (የአንድነት የጎንደር አመራር)
12. አግባው ሰጠኝ (የሰማያዊ የጎንደር አመራር)
13. ንግስት ይርጋ (አንጋፋዋ የጎንደር ጀግና)
14. አስቴር ስዩም (የአንድነት የጎንደር አመራር)
እያልኩም መቀጠል እችላለሁ …. አንዳቸውም አልተፈቱም።
——————-//———————-

መንግስት አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ697 የፌደራል የህግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረገ


አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2010 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ የይቅርታ ቦርድ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ለ697 የፌደራል የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መደረጉን ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ ይፋ አደረጉ።
ፕሬዚዳንቱ ይቅርታ የተደረገላቸው የህግ ታራሚዎችም ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ሰላማዊና አምራች ዜጋ እንዲሆኑ አሳስበዋል።
የ2010 አዲስ ዓመትን አስመልክተው ዛሬ ለመላው ኢትዮጵያውን ባስተላለፉት የ”እንኳን አደረሳችሁ” መልዕክት፥ በርካታ የልማትና የእድገት ተግባራት የሚከናወኑበት ሊሆን እንደሚገባ ነው ብለዋል።
ሀገሪቱ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለምታደርገው ጉዞ ስኬታማነት፥ መንግስት፣ ህዝቡና ባለሃብቱ በህብረት የሚሰሩበት ዓመት እንደሚሆን ተናግረዋል።
በተለይም የማምረቻ ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ የግል ባለሃብቱ ተሳትፎ በልዩ ሁኔታ የሚጠናከርበት መሆኑን ነው የገለፁት።
የ2010 አዲስ ዓመት ኢትዮጵያ የሌሎች ሀገራት ሰላም አምባሳደር እንደሆነች ሁሉ፥ የውስጥ ሰላሟን ከዚህም በላይ የምታስጠብቅበት እንዲሆን ይሰራል ብለዋል።
የመንግስት ሰላም የማስጠበቅ ተግባር ስኬታማ እንዲሆንም የህዝቡ ድጋፍ ሊጠናከር እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።
ፕሬዚዳንቱ አዲሱ ዓመት ለመላው ኢትዮጵያውያን የሰላም፣ የጤና እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የ2010ዓ.ም አዲስ ዓመት ዋዜማ በልዩ መርሃግብሮች “መጪው ዘመን ለኢትዮጵያ ከፍታ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ነው።
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያውያን ቀን “እኛ ኢትዮጵያውያን የጥቁር ህዝቦች ተምሳሌት ነን” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገሪቱ እየተከበረ ይገኛል።

No comments:

Post a Comment