Saturday, April 29, 2017

ጋዜጠኞችን በማሰር ኢትዮጵያ በዓለም አምስተኛ ነች

    


የዓለም የፕሬስ ነጻነት ባለፈው የአውሮፓውያን 2016 ዓመተ ምህረት በአስራ ሦስት ዓመታት ውስጥ ባልታየ ደረጃ አሽቆልቁሉዋል ሲል ጽህፈት ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርት አስታውቋል።
የዓለም የፕሬስ ነጻነት ባለፈው የአውሮፓውያን 2016 ዓመተ ምህረት በአስራ ሦስት ዓመታት ውስጥ ባልታየ ደረጃ አሽቆልቁሉዋል ሲል ጽህፈት ቤቱ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ዛሬ ይፋ ባደረገው ዓመታዊ ሪፖርት አስታውቋል።
ይህ የሆነው በትላላቆቹ ዴሞክራሲያዊ ሃገሮች ከምን ጊዜውም በከፋ ደረጃ በጋዜጠኞችና በዜና ማሰራጫ ድርጅቶች ላይ በሚደርሰው ዛቻ አምባገነን መንግስታት ጥቃታቸውን እያባባሱ በመምጣትቸው ነው ሲል ፍሪደም ሃውስ ዛሬ ባወጣው የፕሬስ ነጻነት ሪፖርቱ ገልጿል።
በሪፖርቱ መሠረት አሁንም ቀንደኞቹ የፕሬስ ነፃነት ረጋጮች በአምባገነኑ ኪም ጆንግ ኡን የምትመራዋ ሰሜን ኮሪያ፣ ላለፉት ስድስት ዓመታት በርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች ያለችው ሶሪያ እና የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃኑን ሙሉ በሙሉ ኮምዩኒስት ፓርቲው የሚቆጣጠርባት ቻይና ናቸው።
በአሁኑ ጊዜ እየታየ ያለው አንድ ለውጥ ግን “እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ባሉ ዴሞክራሲያዊ ሀገሮችም የፕሬስ ነፃነት እየተጎዳ መምጣቱ ነው” ብለዋል የፍሪደም ሃውስ የምርምር ዳይሬክተር ጀነፈር ደነም።
አንዱ ትልቁና አሳሳቢው ለውጥ ዴሞክራሲ እየተሸረሸረ መሄዱ መሆኑን የገለፁት ደነም በተለይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ በጋዜጠኞች እና በዜና አውታሮች ላይ የሚሠነዝሯቸውን ውረፋዎች በተለይ ጠቅሰዋል።
ይሁንና ሥጋቱ ቢኖርም “የዩናይትድ ስቴትስ የመናገር ነፃነትና የሚድያውም ነፃነት እንደተቋም እንደተጠበቀ ነው” ብሏል ፍሪደም ሃውስ የሚባለው የዴሞክራሲ አስተሳሰቦች አራማጅ ተቋም፡፡

No comments:

Post a Comment