Friday, April 28, 2017

ከመቀሌ – እንዳስላሴ የታቀደውን የባቡር ሀዲድ ሀይለማርያም ሰረዘው እየተባለ የሚለቀቀው ዲስኩር ሽፋን ነው፡፡ Tesfaye Ru


    


ከመቀሌ – እንዳስላሴ የታቀደውን የባቡር ሀዲድ ሀይለማርያም ሰረዘው እየተባለ የሚለቀቀው ዲስኩር ሽፋን ነው፡፡ Tesfaye Ru
ከአዋሽ-ኮምቦልቻ-መቀሌ ያለው የባቡር ሀዲድ ዋጋ ከአባይ ግድብ በላይ ዋጋ ወጥቶበት በመሰራት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ብር አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አቅም ግን ከሙስናና ዝርፊያ ተርፎ አባይን መጨረስ አቅቶት በ6ኛ አመቱ ግማሽ ላይ ደርሶ አሁን መራመድ አቅቶት ወገቤን እያለ ነው፡፡
ባቡር ትርፋማ ስለሆነ ከአዋሽ- ኮምቦልቻ-ሃራ ገበያ ያለውን የአውሮፓ ህብረት አበደረ፡፡ ከሀራ መቀሌ ያለውን የቻይና ባለስልጣናትን አስክረው በስካር መንፈስ አስፈርመዋቸው ነው መሰለኝ፤ የቻይና ኤግዚም ባንክ ሸፍኖታል፡፡
እስከ ኮምቦልቻ- ሀራ ገበያ ያለው ሀዲድ የተሰራው በወሎ፣ ጎንደርና፣ ጎጃም ማሊያ መቀሌ ተጫውታ ባስለቀቀች ገንዘብ ነው፡፡
economically profitable, technically feasible የሚል ነገር መጨረሻው ላይ ላልተፃፈበት ፕሮፖዛል ፈረንጅ አያበድርም፡፡ እና እንዳስላሴ ይቺን የአዋጪነት መስፈርት ስላላሟላች ብድር ስላልተገኘ ተገደው የቀረውን ፕሮጀክት ወያኔ በራሱ ፍላጎት፥ ተመጣጣኝ የመሰረተ ልማት ክፍፍል ሊያደርግ አስቦ እንደተወው አድርጎ መወራቱ ያሳፍራል፡፡
ወያኔ ለተንኮል ከባህር ዳርና ከመተማ የሚነሳው ሀዲድ በወልዲያ ብሎ አዋሽ ጋር ይገናኛል በሚለው ፕሮፖዛሉ የመቀሌውን ሀዲድ በግርግር በአማራ ከተሞች ሽፋን ተጠቀመ፡፡
ትክክለኛው፣ አትራፊውና ለመስራትም ምቹ የሆነው መንገድ ከመተማና ጎንደር የሚነሳው ወረታ ላይ ተገናኝቶ በባህር ዳር ብሎ፣ በማርቆስ አድርጎ፣ በደጀን ብሎ፣ 20ኪ/ሜ አካባቢ የመሬት ውስጥ ተነል ከደጀን ውስጥ ለውስጥ አባይ ላይ በሚሰራ ድልድይ አልፎ ዳግም በተነል ወደ ጎሃ ጽዮን አካባቢ ወጥቶ በመሬት ላይ ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ መግባት ይችላል፡፡ ከአባይ ሸለቆ በስተቀር ሁሉም ሜዳ ለሜዳ ስለሆነ ለመስራት ርካሽና በጣም ጠቃሚ አማራጭ ነበር፡፡ ነገር ግን ለትግራይ ጥቅም ጎጃምና ጎንደርን መስዋዕትነት አስከፈሉ፡፡
አሁን ከባህር ዳር አዲስ አበባ ለመግባት የዙሪያ ጥምጥም መጓዝ ምን ይባላል? ያውም ለጉዞ ምቹ ባልሆነ ሞቃት መንገድ በረሃ ለበረሃ፡፡ ሰዎች በባቡር በዚያ ከሚጓዙ በመኪና በደጀን መሄድን ይመርጣሉ፡፡
እዳውን ለመክፈል ግን አብረን ስንገተገት እንኖራለን፡፡
ደግሞም አበዳሪ ያጣው የእንዳስላሴና አክሱሙም አይቀርም፡፡ አበዳሪ ቢጠፋም እንደ አባይ ግድብ “እኛው በእኛው እንሰራዋለን” ይባልና የህዳሴው ሀዲድ እየተባለ ህዝቡ መገፍገፍ ይጀምር ይሆናል፡፡

No comments:

Post a Comment