Wednesday, April 5, 2017

ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት ዛሬ ቀርበው ነበር



ከሙሉቀን ተስፋው
ዛሬ መጋቢት 27 ቀን 2009 ዓ.ም የኮሎኔል ደመቀ ዘዉዱ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጎንደር ምድብ ችሎት ቀርበው የነበር ሲሆን ተይዞላቸው የነበረው ቀጠሮ ጠበቆቻቸው ባቀረቡት የክስ መቃወሚያ ላይ እና በማረሚያ ቤቱ እየተፈመባቸው ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት እና አያያዝ በሚመለከት ብይን ለመስጠት ሲሆን በችሎቱ የተሰየሙት ዳኞች ሁለት ብቻ በመሆናቸው እና ለመዝገቡ አዲስ በመሆናቸው ወደፊት ዳኞች ሲሟሉ በሁለቱም ነጥቦች ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮው ለሚያዝያ 16 /2009 ዓ.ም ተልቀጥሯል።
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በማረሚያ ቤት ውስጥ ብቻቸውን አንድ ክፍል ውስጥ ተቆልፈው እና እግራቸው በሰንሰለት በመታሰሩ ኢ-ሰብዓዊ አያያዝ እየተፈፀመባቸው መሆኑን ለችሎት አመልክተው ችሎቱ የማ/ቤት ፖሊስ ካለ እንዲያስረዳ ጠይቆ አንድ የማረሚያ ቤት ፖሊስ ከችሎት ቀርቦ ሲናገር ካሁን በፊት የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ( አቶ ጀማል ሰዒድ) ቀርቦ ያስረዱ ስለሆነ የተለየ ነገር የለም ብለው አክለውም ማረሚያ ቤቱ ከተለያዩ ክፍሎች የሚታዘዘውን ይፈፅማል በማለት በኢ-ሰብአዊ አያያዙ ላይ ፍ/ቤት የሰጠው ትዕዛዝ ያልተፈፅመ መሆኑን አረጋግጠዋል ።
ከዚህኛው ቀጠሮ በፊት የነበረውን እና ዳኛ ቢንያም ችሎት ላይ የታፍፕኑበትን የክልሉ ጠ/ፍቤት ፕሬዚደንት መጥተው ችሎቱን የዳኙ እና ለማረሚያ ቤቱ ትዕዛዝ ቢያስተላልፉም ተፈጻሚነት ሳያገኝ ዛሬም በዚሁ መልኩ ችሎቱ ተቀጥሯል።

No comments:

Post a Comment