Thursday, April 20, 2017

በጎንደር የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመድ የሆነ የሕወሓት አባል መኖሪያ ቤት ላይ ቦምብ ተጣለ



(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ቀበሌ 15 በተለመዶው አብዮት አደባባይ እየተባለ በሚጠራው እና የሕወሓት አባል የሚኖርበት የተባለበት ቦታ ላይ የቦምብ ጥቃት መድረሱ ተሰማ::
__________________

___________________
የዘ-ሐበሻ የጎንደር ምንጮች እንደዘገቡት ጎንደርንና ከፊል የምስራቅ ጎጃምን ያሽከረክራሉ የተባሉት አቶ አምባዬ አማረ መኖሪያ ቤት ላይ ነው ቦምብ የተጣለው:: ይህ የተጣለው ቦምብ ከምሽቱ ሦስት ሰዓት ሊሆን አካባቢ እንደፈነዳ የሚገልጹት ምንጮቹ መኖሪያ ቤቱ እንደጋየ ገልጸዋል:: አቶ አምባዬ የአቶ መለስ ዜናዊ የቅርብ ዘመድና የአድዋ ተወላጅ መሆናቸውንም የአካባቢው ምንጮች አስታውቀዋል::
በዚህ የቦምብ አደጋ በሰውና በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ መጠን ለዘ-ሐበሻ ያልደረሰ ሲሆን ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደ አካልም የለም:: በጎንደር ሰሞኑን በተደጋጋሚ ቦምብ እየፈነዳ ሲሆን የ እንግሊዝ መንግስትን ጨምሮ ሌሎች ሃገራት ዜጎቻቸው በነዚህ ፍንዳታዎች የተነሳ ዜጎቻቸው ወደዚያው እንዳይጓዙ ቢመክሩም መንግስት አንዱንም የቦምብ ፍንዳታ በሚዲያዎቹ አልዘገበም:: እንደታዛቢዎች ገለጻ መንግስት ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ያለበት ምክንያት ሊያስከትለው በሚችለው ፍራቻ ነው::

No comments:

Post a Comment