“ድርድሩ” ከሽፏል። ሕወሃት በሶስተኛ አካል ለመደራደር ፍቃደኛ አልሆነም። አንድ ጦማሪ እንዳስቀመጠው ” ከኛ ውጭ ማንም አደራዳሪ አይገባም። በሀገር ጉዳይ፣ ከፈለጋቹ እኔ አደራድራለሁ፣ ካልሆነም በዙር እርስ በእርሳችን እንደራደራለን” በሚል ህወሃት የመጀመሪያም/የመጨረሻም ውሳኔዉን ዛሬ አሳውቋል።
ሰማያዊ፣ መኢአድና ኢዴፓ በዋናነት ሶስተኛ አካል በሌለበት መደራደር የማይታሰብ መሆኑ በመግልጽ አገዛዙ ከግትር አቋሙ እንዲለሳለስ ተማጽኖ ቢያቀርቡም፣ ገዢው ፓርቲ በዚህ ጉዳይ ላይ የደረቀ አቋም በመያዙ ስብሰባው ተበትኗል። ኢሕአዴግ ዉስጥ ካሉ ምንጮቼ በደረሰኝ መረጃ፣ ይህ ዉሳኔ የሕወሃት ዉሳኔ ነው።
ሰማያዊ፣ መኢአድ እና ኢዴፓ በአመራር ደረጃ መክረው በይፋ አገዛዙ “ለመደራደርና የአገርን ችግር በዉይይት ለመፍታት ፍቃደኛ አለመሆኑ” ያሳወቃሉ ተብሎ በተጠበቀው መሰረት፣ ሰማያዊና መኢአድ አቋማቸዉን ግልጽ በማድረግ፣ ያለ ሶስተኛ አደራዳርሪ ድርድር እንደማይኖር ገልጸዋል።
ሌሎች ቀደም ሲል ግብስብስ ድርጅቶች ብዬ ያልኳቸውን በመያዝ አገዛዙ “ከተቃዋሚዎች ጋር ዉይይት እያደረግን ነው” የሚል ዳንኪራ ለማሳየት መሞከሩ አይቀርም። ያሳያልም። ሆኖም መድረክ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ ምን አልባትን ኢዴፓ የሌሉበት የ”የተቃዋሚዎችን” ዉይይት ማንም ለቁም ነገር አይቆጥረውም።
ለሰማያዊ፣ መኢአድ፣ መድረክና ኢዴፕ አመራሮች በዚህ አጋጣሚ ያለኝን ትልቅ አክብሮት መግልጽ እወዳለሁ። ትእግስተኛ ሆነው፣ ከደጋፊዎቻቸውና ከብዙ ወገኖች ጠንካራ ትችት እየቀረበባቸውም በመርህ ደረጃ ዉይይትን መሸሽ አያስፈለግም በሚል አስተዋይ ዉሳኔ ብመወሰን፣ አገርና ህዝብን በማስቀደም የአገር ችግር በሰላም እንዲፈታ የቻሉትን ሁሉ አድርገዋል። ለትግሉ ትልቅ ዋጋ ከፍለዋል።፡ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ አመሰግናቸዋለሁ።
አገር ቤት ያሉት ተቃዋሚዎች አንዱ ሊሰሩት የሚችሉት የነበረው ነገር በድርድር ለዉጦችን ማምጣት ነበር። ያንን ሞክሩ ግን ያን በር ሕወሃት ዘጋው። መቼም በአንድ ብቻ አይጨበጨብም። አገዛዙ የአገርን ችግር በንግግርር ለመፍታት ፍቃደኛ ካለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ የሆነው አገዛዙ ራሱ ይሆናል።
ሴማያዊ/ኢዴፓ/መኢአድ መድረክ ጽ/ቤቶቻቸውን ዘግተው ወደ ግል ኑሯቸው ይሂዱ አልልም።፡ምንም መንቀሳቀስ ባይችሉም፣ ራሳቸውን ከራዳር አስወጥተው ሊሰሩት የሚችሉት ነገር ካለ (በግሌ ሁሉንም ነገር ታፍኖ ይሄን ሊስሩ ይችላሉ የምለው የለም) ስራቸውን ይቀጥሉ። ወደፊት ነገሮች ከተለወጡና ከተስተካከሉ ብዙ ሊሰሩ የሚችሉ ነገሮች ስለሚኖር ባይበታተኑ ጥሩ ነው።
አገር ቤት ያሉ ሰላማዊና ሕጋዊ ድርጅቶች እነርሱ ማድረግ ያአለባቸዉን አድርገዋል። ሆኖም ግን ሕጋዊ ያልሆኑ እጅግ በጣም በርካታ ድርጅቶች አሉ። አሁን እነርሱ መንቀሣቀሥ አለባቸው።የሚያደርጉት ትግል ትልቅ reconfiguration ያስፈልገዋል። አገር ቤት ያለው ሕጋዊና ሰላማዊ ትግልን መቼም ቢሆን የተጨበጠ ስራ ለመስራት ዝግጁነትና አቅም ካለው (አሁን ባለው ሁኔታ አይኖረውም) መደገፍ ያለበት ትግል ነው። ሆኖም ግን ለሁሉም ጊዜ አለው እንደሚባለው፣ አሁን አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች መሸከም ከሚችሉት በላይ የሆነባቸው መሰለኝ። ስለዚህ ትግል የዱላ ቅብብሎሽ ነዉና፣ ዱላዉን ሌሎች መረከብ አለባቸው። ወደ ሰላማዊ ግን ሕጋዊ ወዳልሆነ፣ የእምቢተኝነት ትግል መኬድ አለበት።

No comments:
Post a Comment