Sunday, April 2, 2017

Breaking: በጎንደር ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል ቦምብ ፈነዳ


  


 2  1184  1186


(ዘ-ሐበሻ) በጎንደር ከተማ ማራኪ ካምፓስ አቅራቢያ የሚገኘው ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል በፈነዳ ቦምብ የተነሳ ጎንደር ከተማ ስትታመስ ማምሸቷ ተሰማ::
የዘ-ሐበሻ የዜና ምንጮች እንዳደረሱን መረጃ ከሆነ በሆቴሉ ቦምቦ የፈነዳው 3:30 አካባቢ ነው:: በፍንዳታው በሰውና በንብረት ላይ የደረሰውን አደጋ ለማጣራት ዘ-ሐበሻ እየሞከረች ሲሆን በኔትወርክ መቆራረጥ ምክንያት መረጃውን ወዲያው ለማግኘት አልቻልንም::
እንደምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ የሕወሓት መራሹ መንግስት ወታደሮች ከተማዋን ሲያምሱት የዋሉ ሲሆን ከሆቴሉ ፊት ለፊት በሚገኘው ኡስማን መስጊድ በመገባትም ብርበራ ማድረጋቸው ተሰምቷል::
ፍሎሪዳ ኢንተርናሽናል ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽና የተሟላ ሬስቶራንትን የያዘ ነው::
ለቦንቡ ጥቃት ኃላፊነቱን የወሰደ ኃይል እስካሁን ባይኖርም ሰሞኑን በተደጋጋሚ በባህርዳርና ጎንደር ተመሳሳይ አደጋዎች እየደረሱ መሆኑን ዘ-ሐበሻ አስቀድማ መዘገቧ አይዘነጋም:
ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን::

No comments:

Post a Comment