Thursday, April 20, 2017

አርበኞች ግንቦት 7 ሁለት የፖሊስ አባላትን አፍኜ ወሰድኩ አለ



የአርበኞች ግንቦት 7 ሠራዊት (ፎቶ ፋይል)
አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሚያዚያ 8 ቀን 2009 ዓም በትክል ድንጋይ እና በወገራ መሃል ልዩ ስሙ ጭጋሳ ቀበሌ ላይ ሳጅን ያለውቀን አበበ እና ኮንስታብል ሙሉጌታ የተባሉትን የፖሊስ አባላትን አፍኖ መውሰዱን ለኢሳት በላከው መረጃ አስታውቋል።
ስለታፈኑት ፖሊሶች የአካባቢውን ባለስልጣናት ለማናገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። በሌላ በኩል ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የጸጥታ ስራ ለመስራት ለክልሉ ፖሊሶችና ለክልሉ ልዩ ሃይል አባላት ተሰጥቶ የነበረው ስልጣን በኮማንድ ፖስቱ እንዲወሰድ ከተደረገ በሁዋላ የክልሉ የጸጥታ አካላት አመኔታ አጥተው ከጥቅም ውጭ መደረጋቸውንና ማንኛውም ውሳኔ በህወሃት በሚመራው ኮማንድ ፖስት እንደሚሰጥ የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል።

___________________________


No comments:

Post a Comment