Friday, April 21, 2017

ቀነኒሳ በቀለ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ምን ብሎት ነበር? | የፊታችን እሁድ በለንደን ማራቶን ይፋለማሉ



የኢትዮጵያ ድንቅ አትሌቶች ቀነኒሳ በቀለና ፈይሳ ሌሊሳ የፊታችን እሁድ ኤፕሪል 23, 2017 በለንደን ማራቶን ይፋጠጣሉ:: ቀነኒሳ በቀለ በዱባይ ማራቶን ሪከርድ እንደሚሰብር ተናገሮ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ በጉዳት ምክንያት ሳይሳካለት ቀርቷል:: ሆኖም ግን የፊታችን እሁድ ከሃገሩ ልጅ ፈይሳ ሌሊሳ ጋር በሚያደርገው ፉክክር ጥሩ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ከወዲሁ እየተናገረ ነው::
ቀነኒሳና ፈይሳ ለንደን ላይ ከውድድሩ ቀድመው የተገናኙ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በተለያዩ ሚድያዎች ከተለቀቀው ፎቶ መረዳት እንደሚቻለው በልምምድ ወቅት አብረው በተነሱት ፎቶ ፈይሳ እንደለመደው እጆቹን ወደላይ አጣምሮ ፎቶውን ተነስቷል:: ቀነኒሳ ከጥቂት ወራት በፊት የፈይሳን ድርጊት አውግዞ እንደበር ባይዘነጋም ፈይሳ በፊት ለፊቱ ይህን መድገሙ እያነጋገረ ነው::

No comments:

Post a Comment