በደቡብ ወሎ ኩታበር የወረዳ መሥሪያ ቤቶች ተቃጠሉ፤
Muluken Tesfaw
በደቡብ ወሎ ዞን ኩታበር ወረዳ በአንድ ግቢ ውስጥ የሚገኙት የወረዳው ምክር ቤት፣ ማዘጋጃ ቤትና የብአዴን ጽ/ቤቶች የእሳት ቃጠሎ ደርሶባቸዋል፡፡ መጋቢት 26 ለ27 ሌሊት 2009 ዓ.ም ሦስቱም በአንድ ግቢ ውስጥ ያሉ መሥሪያ ቤቶች እንዲቃጠሉ መደረጋቸውን የተናገሩት ምንጮች ሁሉም በጋራ የሚጠቀሙበት መዝገብ ቤቱ ሙሉ በሙሉ መውደሙን አሰምተውናል፡፡
ይህን ተከትሎ በኩታበር ከፍተኛ ውጥረትና መደናገጥ የተፈጠረ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው ግለሰቦች በጥርጣሬ መታሰራቸውን ከቦታው የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በአብዛኛው የወሎ አካባቢዎች ወጣቱን ማሳደድ ካልቆመ ብሎም የዐማራ ሕዝብ ሕጋዊ ጥያቄዎች መልስ እስካልተሰጣቸው ድረስ የተለያዩ ጥቃቶች በየቦታው መሠንሰራቸው የማይቀር እንደሆነ የመረጃ ምንጮችን በአጽንኦት ተነናግረዋል፡፡

No comments:
Post a Comment