Friday, April 21, 2017

አማራ እና ኦሮሞ በኢኮኖሚ አቅማቸው እንዲዳብር አይፈለግም




ከቬሮኒካ መላኩ 
የኦህዴድ የኢኮኖሚ አቢዮት ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። አቢዮቱ እንደ ጉም ብን ብሎ እንደ ማለዳ ጤዛ ረግፎ ተረት ሊሆን ትንሽ ነው የቀረው። በዚህም ምክንያት የኦህዴድ የኢኮኖሚ አቢዮት አይዶሎግ ነው ብዬ የማምነው ደረጄ ገረፋ ቱሉ ከፍተኛ ድባቴ (Depression) ውስጥ ገብቷል። አንዳንድየ በብስጭት እንደ ፌንጣ እየዘለለ ነው ። ደረጄ ድንኳን ጥሎ ሃዘን ቢቀመጥ አልፈርድበትም ይሄን የተረት አቢዮት እውን ለማድረግ ጊዜውንም ገንዘቡንም አባክኗል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ሁለቱ ትልልቅ ብሄሮች አማራ እና ኦሮሞ በኢኮኖሚ አቅማቸው እንድዳብር አይፈለግም ። ይሄ አጠቃላይ እና በጥብቅ የሚፈፀም የህውሃት ፖሊሲ ነው ። የኢኮኖሚ አቅማቸው ዳበረ ማለት ፖለቲካን ተቆጣጥረው ውህዳን የሆነውን ህውሃትን ከጨዋታ ውጭ ለማድረግ ድፍረቱን ያገኛሉ ተብሎ ይፈራል። ሁለቱ ታላላቅ ብሄሮች የክልላቸውን ሃብት ተቆጣጠሩ ማለት ለህውሃት የኢኮኖሚ ኢምፓየር የሃብት ምንጭ የሆነው የኦሮሚያና የአማራ የተፈጥሮ ሃብት በኦሮሞና በአማራ ከተያዘ ኢፈርት አደጋ ውስጥ እንደሚገባ ያውቁታል ። ስለዚህ ህውሃት ይሄ እንደሆነ ፈፅሞ አትፈቅድም።

እውነት ለመናገር የኦህዴድ የኢኮኖሚ አቢዮት በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተስፋ አጭሮ ነበር ። ህውሃት በመጀመሪያም ለእነ ለማ መገርሳ የኢኮኖሚ አቢዮት አረንጓዴ መብራት ያሳየችው አስጊ የነበረውን የእነ ጃዋርን የፖለቲካ አቢዮት ለመቆጣጠር ነው እንጅ ከዛ አልፎ ቀና ቀና እንድሉ አልነበረም ። በጊዜያዊነት ህውሃት በለማ መገርሳ በኩል የጠነሰሰችው የኢኮኖሚ አቢዮት የእነ ጃዋርን አቢዮት ሰከን እንድል አድርጓል ። በዚህም መሰረት ሚሽኑን ስለጨረሰ ይሳካል የተባለውን አቢዮት ህውሃት በተላላኪዋ ሃይለማሪያም ደሳለኝ በኩል ” ምንም የማይታወቅ የኢኮኖሚ አቢዮት ነው ” አስብላ በርሜል ሙሉ ውሃ ቸለሰችበት ።

አሁን ለማ መገርሳና ካቢኔው በባዶ አዳራሽ ህዝብ ሰብስበው እየፎከሩ ነው ። ለማ መገርሳ በአባ ዱላ ኔትወርክ ውስጥ ያለ ሰው ነው። ህውሃት ለማ መገርሳን መኮርኮም ወይም “ተበገስ ” ማለት ከፈለገች አባዱላን ጠርታ ቡችላህን ቀዝቀዝ እንድል አድርገው ብላ ማዘዝ ይበቃታል ። አባዱላም የታዘዘውን ለመፈፀም አይኑን የሚያሽ ሰው አይደለም ። ይሄ ሁሉ ሆኖ ለማ መገርሳ አላድብ ካለ ግን ከዚህ በኋላ የሚበላውን ምግብና የሚጠጣውን ውሃ በጥንቃቄ መጠበቅ አለበት።


አለማየሁ አቶምሳነን ያየ ከአባዱላ እና ከህውት ጋር ቼዝ ልጫወት አይልም !!!

No comments:

Post a Comment