Monday, April 24, 2017

የአማራን ህዝብ ሊያጠፋ የተዘጋጀውድብቁ የኢትዮጵያ ጤና ፖሊሲ ( አያሌው መንበር)



Ayalew Menber
የኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ “መከላከልን መሰረት ያደረገ” የጤና ፖሊሲ በሚል በበርካቶች ሲሞከሽ ቆይቷል።ፖሊሲው በዓላማ ደረጃ ወረቀቱ ላይ ሲታይ የሚደነቅና እንከኑ እንብዛም ነው።ወደ ትግበራውና ውስጣዊ ሴረኝነቱ ሲመጣ ግን ከጦርነት ያልተናነሰ የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ያለ ገዳይ መሳሪያ ነው ብሎ መደምደም ያስችላል።ለአንዳንዴች ይህ ድምዳሜ ጭፍንነት ይመስልልቸዋል።
ሆኖም የአማራን ህዝብ የህዝብ ቁጥር ቅነሳ፣የሚኖርበትን የኑሮ ዘይቤና የወሊድ ትግበራ፣የህፃናት አያያዝና ሞት፣የእናቶች ጤና እና ክብካቤ እንዲሁም አማካይ የውልደት መጠን፣ የጤና ተደራሽነትና የጤና ተቋማት ጥራትን ስንመለከት በአብዛኛው (90 በመቶ መለኪያዎች) ከሌሎች ክልሎች ሁሉ በታች በአንዳንዶች መጨረሻም ሆኖ ይገኛል።ቀላሉ ማነፃፀሪያ የዶናልድ ሊቨን የ1974 መረጃ መሰረትየአማራ ህዝብ 10 ሚሊዮን፣የኦሮሞ 7 ሚሊዮን ሲሆን በ1984 ደግሞ አማራ 12.05 ሚሊዬን፣ኦሮሞ 12 ሚሊዮን፣ ትግሬ 4 ሚሊዮን መሆኑን ያሳያል።ከዚህ ጀምሮ ነው እንግዲህ የአማራ ህዝብ ቁጥርና የጤና ተጋላጭነት እያሽቆለቆለ መጥቶ ከ13 ዓመት በኋላ ደግሞ ከኦሮሞ ህዝብ በ6 ሚሊዮን እንደቀነሰ የ2007 CSA ዳታ የሚያሳየው።እነዚህ ሁሉ በርካታ ምክንያቶች ይደርደሩ እንጅ ዋናው መሰረት ግን #የህወሃት_የጤና ፖሊሲ ድብቅ እቅድ በአማራ ላይ በሴረኝነት መፈፀሙ ነው።
ለዛሬው ማሳያ ይሆኑ ዘንድ ከጥር 2016 እስከ ሰኔ 2016 አምና (በጤና ጥበቃ ቢሮ ጠያቂነት) በዓለማቀፍ የጤናና ጥናት ተቋማት ተሳትፎ በCSAአማካኝነት የተደረገው የናሙና ጥናትና ለህዝብ ይፋ ያልተደረገው ውጤት የተገኘው።በጥናቱ CSA,USAID,UNFPA,UNICEF,WORLD BANK,GLOBAL FUND,HAPCO,IRISH AID,….ወዘተ በጥቅሉ 12 ድርጅቶች ተሳትፈዋል)።
በጥናቱ ውስጥ የውልደት መጠን፣የወሊድ ምጣኔ አጠቃቀም፣የህፃናት ሞት፣ ክትባት፣የእናቶች ጤና እና የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ HIV ኤድስ ግንዛቤ እና ሌሎችም ተዳሰዋል።በሁሉም መስፈርቶች የአማራ ክልል የተሻሉ ከተባሉት ውስጥ የለበትም።ይልቁንም በአንዳንዶች ከመጨረሻው (ለምሳሌ በእናቶች ሞት እጅግ አስከፊ ከሚባሉት ሶስቱን ብቻ በመቅደም መጨረሻ)፣በህፃናት ክትባት 6ኛ፣ከHIV አንፃር በኮንዶም አጠቃቀም 4ኛ፣በወሊድ ምጣኔ (ይህ በነጋቲቭ መታየት አለበት የህዝብ ቁጥሩ እንዲቀንስ ስለሚፈለግ ከአ.አ ቀጥሎ 2ኛ)፣በእናቶች የውልደት መጠን የመጨረሻ ደረጃ (እጅግ አስጊ)፣…ወዘተ ላይ ይገኛል።ይህንን በዝርዝር ስንመለከት ደግሞ ከላይ በተጠቀሱትና በሌሎችም ትግራይ ክልል ከ1 እስከ ሶስት ውጭ የሄደበት የለም።
ጉዳዩን በዝርዝር ለመመልከት ያህል ከቤተሰብ ምጣኔ ብንጀምር (የህዝብ ቁጥር እድገት እንደ አብዛኛው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ አምራች ከሆነ በበጎው የሚታይ ነው።እንደ ኢትዮጵያ 70 በመቶ ወጣት በመሆኑ የህዝብ ቁጥር እድገትን በአንድ ክልል ብቻ መግታት እድገት ሆን ብሎ እንደመቀማት ይቆጠራል)
እንደ ናሙናው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በሀገራቀፍ ደረጃ የወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ባገቡ ሴቶች 36 በመቶ፣ባላገቡት ደግሞ 58 በመቶ ነው።በዚህ መሰረት ወደ ክልሎች ሲከፋፈል
ክልል…… የወሊድ አጠቃቀም ደረጃ
አዲስ አበባ…56%……………………..1ኛ
አማራ……..47%………………………..2ኛ
ደቡብ…….39%………………………….4ኛ
ሌሌች ደግሞ ትግራይ 36%፣ ኦሮሞ፣28 በመቶ….ሶማሊ 1.5% ናች0ው
ይህ እንግዲህ በአማራ ክልል ምን ያህል ዜጎች የወሊድ መቆጣጠሪይ እንዲጠቀሙ እንደሚደረጉ ያሳያል።መቸም ይህንን ያህል ልዩነት በህዝቡ ፍላጎት የተደረገ ነው ማለት ህዝብን ማታለል ይሆናል።ለዚህ ማሳያ የሚሆነው የአማራ እናቶች የትምህርት ደረጃ ዝቅተኛ መሆኑንም መረጃው ያሳያል።በአጠቃላይ የአንድ እናት በሀገር ደረጃ ልጅ የመውለድ ምጣኔዋ (Total fertility rate) በ15 ዓመት ውስጥ እንደ ሀገር ከ5.5 ወደ 4.6 በጥቅሉ በ0.7 በመቶ ሲቀንስ የአማራ ክልል ግን በ1.4 በመቶ በመቀነስ እጅግ አስከፊው ተብሎ ተለይቷል።
የሌሎችን ስንመለከት የትግራይ ከአማካይም በታች 0.4 ብቻ ሲሆን የደቡብ ደግሞ የሀገሪቱን በመያዝ የቀነሰው በ0.7 ነው።ይህንን ዳታ እጅግ አሳሳቢ የሚያደርገው ደግሞ ወደፊትም የአማራ እናቶችን መካን ለማድረግ የቀረበው የጥናቱ ውጤት ነው።የወሊድ ምጣኔ አጠቃቀሙ ከፍተኛ ሆኖ እያለ አሁንም ደግሞ ገና የወሊድ መከላከያ ይፍልጋሉ ተብለው ከተለዩት ውስጥ የአማራ ክልል ከአዲስ አበባ ጋር እኩል ነው የተቀመጠው።ጥናቱ ምንም አይነት የማስተካከያ ሀሳብ ሳያቀርብ ይልቁንም የፍላጎትና የአቅርቦት ምጣኔን በመተንተን ይቀጥላል።እዚህ ላይ ባለፉት 30 ዓመታት የዘር ማጥፋትና ማፅዳት የተፈፀመበት የአማራ ህዝብ በቀጣይዎቹ ዓመታት እጅግ አደገኛ እና አስከፊ የጭፍጨፋ እቅድ እየወጣለት መሆኑን መገመት አያዳህልግትም።በየትኛውም ዘርፍ ያለ አማራ ሀይማኖት ፖለቲካ ዘር ሳይለየው በአንድነት በመቆም ይህንን ማስቆም ካልቻለ በዘመናዊ የመንግስታዊ ፖሊሲ እቅድ መሰረት የመጥፊያ ጊዚያችን እየተቃረበ መሆኑ መዘንጋት የለበትም።
ክፍል ሁለት….የእናቶች እና ህፃናት ሞት፣HIV ኤድስ፣ክትባት ወዘተ ይቀጥላል።
በዚህ መሰረትም አሁንም የወሊድ ምጣኔ ይፍለጋሉ እና የተሟላላቸው፣ ያልተሟላላቸው ያላቸውንም ይህ ጥናት ይዘረዝራል።
#አማራን_ሊያጠፋ_የተዘጋጀው_የጤና_ፖሊሲ (ክፍል ሁለት)
( አያሌው መንበር)
በክፍል አንድ ዳሰሳችን የአማራን ህዝብ የወሊድ መከላከያ አጠቃቀምና እና በአስገራሚ ሁኔታ የቀነሰውን የእናቶች ወሊድ መጠን ተመልክተናል።በዚህ መረጃ መሰረት የአማራ ክልል የወሊድ ምጣኔ አጠቃቀምም 47 በመቶ ደርሷል።ይህም ወደ ግማሽ የሚሆኑ እናቶች ወይ አይወልዱም አልያም የሚኖራቸው ልጅ ቁጥር ጥቂት ነው ማለት ነው።(Fertility Rate የሀገሩቱ በ0.7 ሲቀንስ የአማራ በ1.4 ቀንሷል፤ ይህ ማለት አንዲት እናት ትወልድ ከነበረው ቢያንስ ሁለቱን አትወልድም ማለት ነው)
በዚህ ክፍል ደግሞ የአማራን የህፃናት ክትባት፣ የእናቶች ሞት፣ የእናቶች ወሊድ እና እንክብካቤ ከሌሎች ክልሎች አንፃር ምን እንደሚመስል የጤና ሚኒስቴር የናሙና ጥናት ውጤትን መሰረት አድርገን እንመለከታለን።
#ከእናቶች_ጤናና ወሊድ አንፃር
በ2016ቱ ናሙና መሰረት በኢትዮጵያ #በከተማ_ከሚኖሩ እናቶች ውስጥ #በሰለጠኑ_ባለሙያዎች የሚታገዙ እናቶች 80 በመቶ ሲሆኑ 79 በመቶዎቹም #በጤና_ተቋም ይወልዳሉ።
ይህ አሃዝ በገጠሩ በኩል ሲታይ 21% በመቶ ብቻ ናቸው በሰለጠነ የጤና ባለሙያ ክትትል የሚደረግላቸው።በጤና ጣቢያ የሚወልዱት እናቶች ደግሞ 20 በመቶ ብቻ ናቸው።ይህ አሃዝ ወደ ክልሎች ሲከፋፈል
በጤና ባለሙያ የሚደገፉ..በጤና ጣቢያ የሚወልዱት
1.አዲስ አበባ….97%………98%
2.ትግራይ…..59%…………..57%
3.ድሬዳዋ….57%…………56%
.
8-አማራ…..27%…………..27%
ይህንን የCSA የ2016 ጥናት ስንመለከት የአማራ እናቶች ስቃይ እጅግ ያሳስባል።የአማራ እና የትግራይ እናቶችን የጤና ባለሙያ ክትትል እና በጤና ጣቢያ መውለድ ስንመለከት የትግራይ ወደ ስልሳ ሲጠጋ የአማራው ግማሹን እንኳን መሆን አልቻለም።(((ከመቶዎቹ የአማራ እናቶች ውስጥ በጤና ባለሙያ የሚጎበኙና በጤና ባለሙያ ድጋፍ የሚወልዱት 27ቱ ብቻ ናቸው።ይህ አሃዝ በገዥው ፓርቲ የኢኮኖሚ፣ፖለቲካና ማህበራዊ ዘርፍ ማዕከል ትግራይ ሲታይ ግን የአማራን እጥፍ 57 በመቶ ወላዶች በህክምና ባለሙያ ክብካቤ ያገኛሉ፣በጤና ተቋምም ይወልዳሉ)))።
አማራ በዚህ ዘርፍ ከመጨረሻዎቹ ሶስት ክልሎችን አስከትሎ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ነው።በመሆኑም በአማራ ከወሊድ ጋር በተያያዘ በሁለቱም (በህፃናት እና በእናቶችም ሞት ከፍተኛ ነው ማለት ነው)።በእናቶች ሞት የአማራ ክልል እጅግ አሳሳቢ ከሚባሉት ክልሎች ውስጥ ከጋንቤላ ቀጥሎ በሁለተኛነት የተቀመጠ ነው።ልብ በሉ አንድ ወንድ ልጅ ወይም ሴት ልጅ እናቱ ሌላ እህት ወይም ወንድም ትወልድልኛለች ብሎ ሲጠባበቅ እናቱንም ሲያጣ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ የሚየውቀው የደረሰበት ነው።የአማራ እናት ወልዳ የመሳም እድሏ ከመመንመኑ በላይ እርሷ እራሷ በህይወት የመኖር እድሏ ከሌሎች እናቶች አንፃር እንኳን ሲታይ እጅግ ጠባብ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ጥቅል የዜጎችን በህይወት የመኖር ጣራ (Life expectancy) ከሀገሪቱ ዳታ ስንመለከትም ይኸው ያልታደለ ክልል ከሀገሪቱ አማካይ ዝቅ ብሎ እናገኘዋለን።በlife expectancy አንድ አመት እንኳን ለውጡ ቀላል አይደለም።ስለሆነም የኢትዮጵያውያን አማካይ በህይወት የመኖር እድል እ.ኤ.አ በ2013 የወጣው ሌላ መረጃ እንደሚያሳየው 62.2 በመቶ ሲሆን የአማራ ግን 58 በመቶ ላይ ነው።በእነርሱ አጠራር “የአንደኛ ደረጃ ዜጎች ወይም የወርቅ ዘሮች” የእድሜ ጣራ ደግሞ ከሀረር እና አ.አ ቀጥሎ በሶስተኛ ደረጃ ላይ በ61 ተቀምጧል።
#የህፃናት_ጤናን በተመለከተ
ከህፃናት ጤና ጋር ተያይዞ የሚነሳው እናቶች በቅድመ ወሊድ በጤና ባለሙያ የሚያደርጉት ክትትል ቀደም ብለን ያየነው) እና ድህረ ወሊድ (ክትባት፣አመጋገብ ወዘተ ) ከፍተኛ ድርሻ ይይዛል።በዚህ ረገድ የህፃናት ሞት ክልላዊ ይዘቱን ባይገልፅም እንደ ሀገር ቅናሽ አሳይቷል። ባለፉት አምስት ዓመታት ከ5 ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ሞት ጥቅል ሁኔታ ስንመለከት ቅናሽ አሳይቷል።በ2000 እ.ኤ.አ ከ1ሺህ ህፃናት 116ቱ ይሞቱ ነበር።ይህ አሃዝ በ2016 ወደ 67 ዝቅ ብሏል።
#የህፃናት_ክትባትን ስንመለከት ደግሞ የአማራ ህፃናት የክትባት ድርሻ ከእናቶች የጤና ድጋፍ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እናገኘዋለን።
በዚህም መሰረት በሀገራቀፍ ደረጃ የክትባት ሽፋን በከተማ 65 በመቶ በገጠር 35 በመቶ ሲሆን የአማራ ግን ……
ክልል ክትባት ያገኙ ህፃናት
1ኛ.አዲስ አበባ……..89 በመቶ
2ኛ.ድሬ ዳዋ…………75 በመቶ
3ኛ.ትግራይ……67 በመቶ
#6ኛ #አማራ…..46 በመቶ ነው።
ከዚህ ከጤና ሚኒስትር ዳታ እንደምንመለከተው በአማራ ክልል ከወሊድ መቆጣጠሪያ አምልጠው ከተወደሉት (የእናቶች የወሊድ ምጣኔ በሀገራቀፍ ደረጃ በ0.7 ሲቀንስ በአማራ ክልል በ1.4 መቀነሱ ይታወሳል) ውስጥ ክትባት ማግኘት የሚችሉት ከግማሽ በታች 46 በመቶ ብቻ ናቸው ማለት ነው።በትግራይ ከሚወለዱት 100 ህፃናት ውስጥ ደግሞ ቢያንስ 67 የክትባት አገልግሎት ተጠቃሚ ናቸው።
ክፍል ሶስት የጤና ተቋም ተደራሽነት፣ጥራትና የአማራ የወደፊት እጣፋንታ ይዳሰስበታል።

No comments:

Post a Comment