Thursday, April 27, 2017

የተጋድሎው አይዲዮሎጅ ምን እንደሆነ ይነገረን! በተለይ ለአርበኞች ግንቦት ሰባት


መስቀሉ አየለ
አንድ ድርጅት ምንነቱ የሚመዘነው አንድም ድርጅቱ በተቋቋመበት አላማ፣ ድርጅቱን በሚመሩት የሰዎች አይነት፣ሰዎቹ የድርጅቱን አለማ ወደ ጫፍ ለማድረስ ያላቸው ቁርጠኝነት እና ይኽ ድርጅቱ ከራሱም ባሻገር ከሌሎች መሰል ተቋማትም ሆነ እታገልለታለሁ ከሚለው ማህብረሰብ ጋር ያለው ቀጥተኛ ግንኙነት ጭምር ነው።

ወያኔ በዚህ ስሌት ሲመዘን የድርጅቱ ጠንሳሽና አንኳር ናቸው የሚባሉቱ ሰዎች በዘመን እርዝመት የማይጠግግ በጸረ ኢትዮያዊነት ይልቁንም በጸረ አማራና ኦርቶዶክስ ሽንት ተቦክተው የተጋገሩ ናቸው።ይኽን አላማ ዳር ለማረስ የሚያስችል ደግሞ በቂ ጥላቻ አላቸው። በአስራ ዘጠኝ ስልሳ ስምንት የተጻፈው የደደቢቱ ማኔፌስቶ እስከ አሁን ያልተሰረዘው ለዚህ ነው። ጠንካራ ጎናቸው ነው ከተባለ የወያኔ ጠንካራ ጎን ይኼው ጠላቴ ብሎ ባሳመረው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያለውን አቋም ዛሬም ከአራት አስርተ አመታት ቦሃላ እንኳን ሳይቀር በጥርሱ ነክሶ እንደያዘ መቆየት መቻሉ ነው።ይኽ ማለት ትሃት ወያኔ፣ ኢህ አዴግ ብሄር-ብሄረሰቦች፣ ቦናፓርቲዝም፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲና ህዳሴው ሽህ አይነት ስም ይሰጠው እንጅ በመርህ ደረጃ የወያኔ አይዲዮሎጅ አማራን ብሎም ኢትዮጵያን ማጥፋት መሆ ዛሬ ለማንም ጠርቶ የወጣ እውነት ሆኗልና ለክርክር የሚጠፋ ጉልበት የለም::
በሌላ በኩል ይህን ሰይጣናዊ አላማ ተፈጻሚ ለማድረግ ከፊት የተሰለፉት እነዚህ የስርአቱ ጉምቱዎች ከድቁርና፣ ከበታችነት ስሜት፤ ከጥላቻና ከችጋር ሰቀቀን የወጡ መሆናቸው፣ በታሪክ አጋጣሚ አንድ ግዜ እጃቸው ላይ ከገባው ስልጣን ውጭ ሌላ ነገን የማየት አቅም ማጣታቸው ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቢወጡ ሌላ ሊሆኑ የሚችሉት ምንም አይነት ማንነት የሌላቸው፤ ከጸጋ በታች እራቁታቸውን የተወለዱ መሆናቸው ነው። እንዲህ አይነት ሰዎች ደግሞ ከስልጣን ወንበራቸው ላይ ተጣብቆ ለመሞት ካላቸው እልህ የተነሳ ዛሬ በምናየው ደረጃም ሆነ ነገ በሚገለጠው የከፋው ማንነታቸው ቢከሰቱ ሊደንቀን አይገባም።

የሰላማዊ ትግል ክሽፈት

ባለፉት እሩብ ምዕተ አመታት ለውጥ ለማምጣት በአገራችን ውስጥ የተደረጉት ሰላማዊ ትግሎች በሙሉ ጸሃይ እንደገላመጠው ጉም በነው የጠፉትበት ምክንያቱ ዛሬም ይህንን አጀንዳ መኖሪያ ያደረጉት የጆሊ ባር አካባቢ ፖለቲከኞች እንደሚሉት “ሰላማዊ ትግሉ በሚገባ ስላልተፈተሸ” አይደለም። መሰረታዊ ችግሩ ከላይ በደምሳሳው የተቀመጠው የወያኔ ባህሪ ነው። ከሰብአዊ መብት ተሟጋች እስከ ነጻው ፕሬስ ጋዜጠኛ፣ ከዋልድባ ምናኔ እስከ ተዋዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ሁሉም ያልተቻሉባት፣ ይልቁንም አገሩን መግዛት ከጀመሩ ከሁለት አስርተ አመታት ቦሃላ ሳይቀር 99.82 ፐርሰንት የፓርላማ ወንበር ይዘው አንድ ግርማ ሰይፉ ጸጉረ ልውጥ ሆኖ ስለገባባቸው የተፈጠረባቸውን ስጋት ታዝበናል; የሰላም ትግል ብሎ ብሎም ቀሪ የተስፋ ጭላንጭል እንደማይታሰብ አረጋግጠናል።ይልቁንም የፖለቲካ ፓርቲዎችን ምርጫ “ካልኩሌቲቭ ሪስክ” ነው ብሎ የደመደመ፣ “በምርጫ ስልጣን ለመያዝ የሚያስቡ ካሉ እግር እስኪያወጡ መጠበቅና ጠብቆ በመቁረጥ ስሌት የምንሄድ መሆኑን ይወቁት” ብሎ ግልጥ ባለ አማርኛ የድጅቱን እውነተኛ ባህሪ “ከውስጥ ከፍቶ ያሳየው” የስርዓቱ አፈ ሊቅ ተክሎት የሄደው የመርዝ ሰንኮፋ ዛሬም ከአራት ኪሎ አልወጣምና በሽታው እስካልተነቀለ ድረስ ቁስሉ ሲመረቅዝ መኖሩ የግድ ነው።

No comments:

Post a Comment