Wednesday, June 7, 2017

ላም ባልዋለበት ኩበት የሚለቅመው ግንቦት ሰባት አንደ ድርጅት ከነአባሎቹ እየዋዠቀ እየተንቀዥቀዠ ነው። (ቆንጂት ስጦታው)


    

ላም ባልዋለበት ኩበት የሚለቅመው ግንቦት ሰባት አንደ ድርጅት ከነአባሎቹ እየዋዠቀ እየተንቀዥቀዠ ነው። (ቆንጂት ስጦታው)
የዘመነ ካሴን ከኤርትራ መልቀቅ ወደ አውሮፓ መግባት ተከትሎ ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት እየዋዥቀ እየተንቀዥቀዥ ነው፣ አስመራ ያለው ጉዱ አደባባይ ላይ ከወጣ ጉድጓድ እንደሚገባ የሚያውቀው ግንቦት ሰባት የተባለው ድርጅት በዚህ ሳምንት የሚይዘው የሚጨብጠው አጥቶ በየሔደበት እየባነነ ነው። የድርጅቱ አመራሮች በውሸትና ገንዘብ ለመሰብሰብ በማፍጠጥ እየቀፈሉ ይገኛሉ።
ዶክተር ብርሃኑ ነጋና የድርጅቱ አመራሮች በዲያስፖራው ሰፈር ሲዞሩ የግንቦት ሰባት ሚዲያና የማህበራዊ ድረገጽ አንድ የለመደው ዘገባ አለ። አሱም ማረክን ገደልን እየተዋጋን ነው የሚል የማጭበርበሪያ ደውል። ይህ ደውል የሚሰማው የግንቦት ሰባት አመራሮች በተለይ ብርሃኑ ነጋ በየውጪው አገር የገንዘብ ማሰባሰብ በሚሉት ስብሰባቸው ላይ ነው። ብርሃኑ ነጋ አሊያም አመራሮች ስብሰባዎች ሲጨርሱ የገደልን የማረክን የተኮስን ወሬም አብሮ ይቆማል።ይህ የግንቦት ሰባት ውሸትም ለወያኔ በር ከፍቶለታል ስልጣኑን ለማስረዘም እንቅፋት ናቸው ያላቸውን በተለይ በዓማራ ክልል የሚገኙ ዜጎችን በግንቦት ሰባት ስም ይፈጃቸውል። ግንቦት ሰባት ለወያኔ ምቹ የዓገዛዝ ዘመን ዋና ሚና ከሚጫወቱ ድርጅቶች አንዱ ሆኗል።
ዲያስፖራው በውሸት የታወረ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ። ዲያስፖራው የታወረው በይሉኝታ ነው። ኪሱ ሲራገፍ ሲበዘበዝ በቃኝ ያለ ቀን ግን ጉድ ይፈላል። የግንቦት ሰባት አመራሮች ውሸት በዚህ ሳምንት ብቻ ይሰቀጥጥ ነበር። በታጋይ ዘመና ካሴ ጉዳይ ትራንስፖርት ከፍለን የጉዞ ፕሮሰሱን ጨርሰን ወደ አውሮፓ ያሻገርነው እኛ ነን ያሉት ብርሃኑ ነጋ የተናገሩበትን አፋቸውን ሳይዘጉ ዘመነ ካሴ የረዱትን ሰውች ከመናገሩም በላይ ግንቦት ሰባትን እንደ ድርጅት አላመሰገነም። ረድቶኛልም አላለም። እነ አዲሃን ን አና የኤርትራ መንግስት ሲያመሰግን ግንቦት ሰባትን እንደ ድርጅት ሳይሆን ያመሰገነው አመራሮቹ ባገለሉት ሰዓት ሰው ሲርበው አብረውት የነበሩትን ታጋዮች ነው ሲባርክ ያዳመጥነው።ለዘመነ ካሴ ህክምና ወጭ በሚሰበሰበው እርዳታ ዙሪያም በመጀመሪያ ተቃውሞ ያሰሙት የታወቁ የግንቦት 7 ሰዎች ነበሩ። አሁን እንደሰማነው “gofundme “እርዳታ መሰብሰቡን አቋርጦታል። የግንቦት 7 አርበኞች ስራቸው ይሄው ነው። አብሯቸው ለወደቀ ለተነሳ ጓዳቸው እንኳ እርህራሄ የላቸውም።
ታጋይ ተፈሪ ካሣሁን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ (አዴሃን) ሊቀ መንበርና ዘመነ ካሴ
ዘመነ ካሴን ለመርዳት በተደረገ የገንዘብ ማሰባሰብ ላይ ጎፈንድሚን ማዘጋት ምን ያህል ግንቦት ሰባት እንደከሰረ እንደተዋረደ ያሳያል። ግንቦት ሰባት በቁሙ መሞቱን የሚያረጋግጠው የድርጅቶቹ አባላት በስድብ ላይ የተሰማሩ ድርጅታዊ ዲሲፕሊን ያሌላቸው ባለጌዎች ሲሆኑ በዘመነ ካሴ ስም አስመሳይ አቋም ይዘው ሊነግዱ ይፈልጋል። የዘመነ ካሴን ሕክምና ለመርዳት የተከፈተውን መስመር ያዘጉት የግንቦት ሰባት ሰዎች መሆናቸው ሙሉ በሙሉ ተረጋግጧል። ይህ ትልቅ ብልግና ሲሆን ምን ያህል ደደቦች እንደሆኑ ሲያመለክት ለወያኔ ሰዎችና ለማይረቡ ፖለቲከኞች ግን ገንዘብ በግንባር ቀደምትነት ሲያሰባስቡ የነበሩት ግንቦት ሰባቶች ነበሩ ። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ “ዘመነ ካሴን ሙሉ ወጭውን ሸፍነን ከኤርትራ ያስወጣነው እኛ ነን ” ያሉባት ላንቃቸው ሳትዘጋ… ዘመነ ካሴ ከኤርትራ ለመውጣት የረዱትን አካላት ሲዘረዝር ግንቦት 7 ከዝርዝሩ ውስጥ እንደሌለ ተረጋግጧል። ትልቁ ሰውዬ አይን ያወጣ ውሸት ሲዋሹ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል! ዘመነ ካሴ ገና የሚዘከዝከው ብዙ ጉድ እንዳለም ፍንጭ ሰጥቷል።ግንቦት ሰባት ሕወሓትን እየተዋጋሁ ነው ብሎ ከሚያጭበረብር ድርጅቱ ራሱ ተሃድሶ ያድርግ ።

2 comments:

  1. Betam tigermaleh anncj ezih kuch bileshi tera propoganda likeki AG7 meret werdo tilk sira eyesera new ye weyane kitregnoch (hodamoch) tiglu eyemerere simeta eyayachihu frhatu enkilf nestoachihual mehon yemigebaw kemehon ayikerim enantem bandoch awru ag7 sirawun yisira dil le ethiopia hizib mot lezeregnagn ena kitiregnoch ethiopia lezelalem tinur::

    ReplyDelete
  2. Betam tigermaleh anncj ezih kuch bileshi tera propoganda likeki AG7 meret werdo tilk sira eyesera new ye weyane kitregnoch (hodamoch) tiglu eyemerere simeta eyayachihu frhatu enkilf nestoachihual mehon yemigebaw kemehon ayikerim enantem bandoch awru ag7 sirawun yisira dil le ethiopia hizib mot lezeregnagn ena kitiregnoch ethiopia lezelalem tinur::

    ReplyDelete