Thursday, June 15, 2017

ህወሃት በስሜንና ደቡብ ጎንደር ሕዝብ ላይ ጦርነት ለያካሂድ ዝግጅቱን አጠናቋል!! – አንተነህ ገብርየ”

June 15, 2017 20:27      


አገር መራሹ የትግራይ ወንበዴ ቡድን ለአርባ ሦስት ዓመታት ያህል አማራውን እና የትግራይን ሕዝብ ደም ሲያፋሥስ ቆይቶ  የትግራይን ሕዝብ አሁንም ከሰው በላውና ፋሽስቱ ቡድን ጐን እንዲሰለፍ እየተማፀነ ፀረ-ሕዝብ ፕሮፓጋንዳውን እያናፈሰ እንደሚገኝ ከዚያው ከሀገር ቤት የምናገኛቸው መረጃዎች ይገልፃሉ።የትግራይ ሕዝብ ከዚህ ቀደም የፈፀመውን ስህተት ላለመድገምና ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር አብሮ ለመኖር የሚያስችለውን ሁኔታ መፍጠር ያለበት አሁን ይመስለኛል።ይህ መሆን ካልቻለ የትግራይ ምድርም ሆነ በየትኛውም ምድር የሚኖር ትግሬ ቀን እንደሚጨልምበት ሊያውቅ ይገባዋል።ምክንያቶቹን በዝርዝር መግለጽ የሚያስፈልግም አይደለም ለምን ቢባል በአይን የሚታዩ በተግባር እየተፈፀሙ ያሉ ፋሽስታዊ ተግባሮች በመሆናቸው።ጊዜው አሁን ነው አሁን መሪዎቹ የሚያራግቡትን ፀረ-ሕዝብ ቅስቀሳ ማክሸፍና ክንዱን በራሱ በህወሃት ላይ ማንሳትና ህወሃትን ለማስወገድ መታገል ይኖርበታል።ይህ ሳይሆን ቢቀር ግን ለሚደርሰው ማንኛውም የሰውና የንብረት ኪሳራ ተጠያቂው ራሱ የትግራይ ሕዝብና ድርጅቱ ህወሃት እንደሚሆኑ ሊታወቅ ይገባዋል።ለምን ቢባል የትግራይ ሕዝብ ህወሃትን ተቀብሎ ከማስተናገዱ በፊት ሰከን ብሎ ማሰብና ከድርጅቱ በስተጀርባ ማን አለ?ድርጅቱ የሚታገልለት ዓላማ ለማን ይጠቅማል?በኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ላይ ሊያስከትል የሚችለው ምንድን ነው?አሁንስ ይህ እኩይ ድርጅት እየፈፀመ ያለው ምንድን ነው?የሚል አንድም ነገር ተነስቶ አልሰማንም አላየንም ከዚህ ከፍ ብሎ ከዚህ በኋላ ለሚሆነው ነገር ሁሉ ተጠያቂዎች ህወሃትና የትግራይ ሕዝብ ብቻና ብቻ ትሆናላችሁ ያልኩት ለዚህ ነው።
የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ እንዲሉ መገንጠል አለብን ብሎ የተገነጠለው ሻእብያና የኤርትራ ሕዝብም ከተገነጠሉ በኋላ በህወሃት እግር እየታከኩ የኢትዮጵያን ሕዝብ ሀብት መመዝበርና በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ ስለሆኑ ህወሃትን ከመደገፍ አልፎ መተባበርና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ በተለይም በአማራው ሕዝብ ላይ የሰነዘሩትን የጥፋት እጃቸውን በአስቸኳይ ሊያነሱ ይገባቸዋል።ካልሆነ ግን እላይ ለመጠቆም የሞከርኩት እነሱንም የአጠቃለለ ሊሆን እንደሚችል ሊገባቸው ይገባል።በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት የስንቶቹ አካል እንደጎደለ፤የሰው ሕይወት እንደጠቀጭና የሀገር ሀብት እንደወደመ የቅርብ ትውስታችንና ቁስላችንም ስለሆነ በፍፁም የምንረሳው ጉዳይ አይሆንም።ማን ተጠቃሚ እንደሆነም እየተመለክትን ነው ያም ሆኖ ደግሞ ለእልቂቱ ምክንያት የሆነው ጉዳይ እልባት ሳያገኝ እንደተንከረፈፈ ይገኛል ለምን እንደዚህ ሆነ?ቢባል የአዲስ አበባዎቹ ኤርትራውያንና የአስመራዎቹ ትግራይዋን ከጌቶቻቸው ትእዛዝ ጠብቀው የሰው ቁጥር ለመቀነስ ባልገመትነውና ባልጠበቅነው ሰአት እሣቱን እንደሚለኩሱት አንባቢዎቸ ልብ እንድትሉልኝ እጠይቃለሁ።ሌላው መጠቀስ ያለበት ጉዳይ ያኔ የጦርነቱ ጊዜ ኤርትራውያን በጣት የሚቆጠሩት ካልሆኑ በስተቀር አብዛኛዎቹ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በገፍ ታፍሰው በጭነት መኪና ወደ ኤርትራ መጓዛቸው ይታወቃል።
አሁን ላይ ያለውን ሁኔታ ስንመለከት ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፤መለስተኛ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲትዎች በኤርትራውያን ተማሪዎች ተጨናንቀው እንደሚገኙ ግልጽ ነው፤ቤት የተወረሰባቸው እየተመለሰላቸው ነው ከዚህ ስንነሳ ቀደም ሲል ታምራት ኤርትራ ሄዶ በተፈራረመው ውል መሠረት የአሰብ ወደብ ኢንሹራን፤የመንገድ ጥገና፤የመንግሥት ሠራተኞች የነበሩ ኤርትራውያን የጡረታ ክፍያ፤የንግድ እንቅስቃሴና ሌሎች ተቋማት በሙሉ ይመለሳሉ፤ኤርትራውያ ወደ ውጭ ሀገር ሲወጡ የሚጠቀሙበት ቪዛ የኢትዮጵያ ነው ጠቅለል አድርጎ ለማስቀመጥ ታምራት የተፈራረመባቸውን ውሎች አሁን ፈልጌ ባላገኛቸውም ብዛታቸው 25 ነጥቦችን ያካተተ እንደነበር አስታውሳለሁ ታዲያ እነዚህ ሁሉ ውሎች ለኢትዮጵያ አንዳችም ፋይዳ እንደአልነበራቸውና ኤርትራውያንን ለመጥቀም ሲባል የተፈፀመ ደባ ወይም ታሪካዊ ውንብድናና ክህደት ነበር።ኤርትራ ደርግ ከወደቀ በኋላ ለመቋቋሚያ ድጎማ ያገኘችው ከኢትዮጵያ ነው አውሮፕላኖች የተወሰዱትም ደርግ ከወደቀ በኋላ ነው ወደ 80ሽህ የሚጠጉ ምስኪኖች ጦርነት ውስጥ ተማግደው በእግረኛና በአየር በከባድ መሣርያና በጥይት አረር የተቆሉበት ጦርነት ውጤት ከንቱ ሆኖ ሲቀር ምናልባትም በኢትዮጵያ በኩል በ10ሽዎች የሚቆጠሩ ምርኮኞች መንግሥት የሌላቸው በመሆኑ ዛሬም በእሥራት ላይ ይገኛሉ።
ነገሩ ከላይ ከላይ ያጎርሳታል እንዲሉ ሆነና እሥር ላይ ያሉት የሚያስፈታቸው አጥተው የነገው ተስፈኞች ደግሞ ለነፃመት እንታገላለን በሚል ሽፋን ኤርትራ ገብተው በማንቧረቅ ብዙዎቹን ለእስራትና ሌሎች ተመሳሳይ ጥቃቶች እንዲዳረጉ ለማድረግ ሌት ተቀን ተግተው እየሰሩ ይገኛሉ።ከጅማሮው ኤርትራ ገብቸ ታግየ ኢትዮጵያን ነፃ ላወጣ ነው የሚለው ቀልድ ነው ለምን ቢባል ከዚህ ያደረሰንን ችግር ዘውር ብሎ መፈተሽ ያሻል የኢትዮጵያ ጉዳይ  ሲነሳ እንደሚያቅለሸልሻቸው የግንቦት ሰባት መሪዎች ኢሳያስ አፈወርቂ ደግሞ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ሲነሳ አይኑን ጎልጉሎ ለጥፋት እንደሚነሳ ግልጽ ነው እነ አያ ነዓምን ዘለቀም ይህን ኮርጀው እየተጠቀሙባት እንደሆነ ይታወቃል።ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ እንድምታው ሲታይ አማራውን ኢላማ ውስጥ አስገብቶ ከፊትና ከኋላ በመሆን ዘሩን ማጥፋት እንደሆነ ማጠንጠኛው መታወቅ አለበት።አንዳንዶቹ በሬ ካራጁ የሆኑ ግራ የተጋቡ አማራዎች ግንቦት ሰባት ኤርትራ መግባቱ ልክ አይደለም ተብሎ ሲተች ደማቸው የሚጨምርና ታዲያ በየት ገብተው ይታገሉ ብለው የሚሟገቱ ብዙ ናቸው ታግሎ ውጤት ካልተገኘ ምን ፋይዳ አለው?ሲታሰብ ቢውል ሻእብያ ህወሃትን ውጉ ብሎ ከኤርትራ ጦር ይሰዳል ብሎ ማሰብ ከመጃጃልም በላይ ነው።
ይህን ሁሉ መንደርደርያ እንድጽፍ ያደረገኝ ምክንያት ተስፋፊውና ፍሽስቱ ህወሃት በ1972ዓ/ም ክረምት ላይ ተከዜን በመከራ ከተሻገረ በኋላ ሌታና ቀን የጥፋት እጁን የሠነዘረው በስሜን ጎንደር በተለይም በወልቃይት፤ጥገዴ፤ ጠለምትና አርማጭሆ ሕዝብ ላይ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን።ከ1972ዓ/ም ጀምሮ ምን ያህል ሕዝብ ተገድሏል?ከቦታው ተፈናቅሏል፤ሀብት ንብረቱን ተዘርፏል የሚለውን በየድረገጹና በመጻሕፍት ተደጋግሞ የተገለፀ ስለሆነ ወደዚያ አልገባም።ይህ ሁሉ ሲሆን የእነዚያ አካባቢ ነዋሪዎች እጅ እግራቸውን አጣጥፈው ይመለከቱ ነበር ማለት አይደለም።በተናጠል በቡድን የጠላትን ኃይል መከላከልና መምታት ነበረበት የተደራጀ ባለመሆኑና በተለይም በውጭ ሰዎች የሚደረግ መገፋፋት ስለነበረበት አመርቂ ውጤት ማምጣት አልቻለም ነበር።የወልቃይትንና ጠገዴን ሕዝብ ጥያቄ ይዘው ሕገ-መንግሥቱ በሚፈቅደው መንገድ ሄደን የአማራ ማንነታችንን እናረጋግጣለን ብለው የተነሱ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱና ሌሎች ወንድሞቻችን ጉዳዩን ይፋ ካደረጉት በኋላ በርከት ባሉ አካባቢዎች ጉዳዩ የሕዝብን ትኩረት ሊስብ ቻለ።ወራሪ የህወሃት ቡድን ብዙ የአቅጣጫ ማስቀየሻ ዘዴዎችን ተጠቀመ/አማራና ቅማንት በማለት ያለ አግባብ የወገኖቻችንን ደም አፋሰሰ ግን በሕዝብ ተሳትፎ ነገሩ ቶሎ ብሎ ተቋጨ/፤በኃይል ለማንበርከክ ሞከረ የራሱን ኃይል እያስመታ እንዲያፈገፍግ ተገደደ።የዛሬ ዓመት ገደማ የአማራ ማንነት ጉዳይ አስፈፃሚዎችን የአማራ ክልል ተብየዎች ሳያሳውቁና ሳይናገሩ ተመሳሳይ ዩኒፎርም በማልበስ የአማራ ልዩ ኃይል አስመስሎ አፋኝ ወደ ጎንደር ከተማ አስገብቶ አፈና ተጀመረ 4የሚሆኑት የመታፈን አጋጣሚ ሲደርስባቸው 5ኛው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ለማፈን የሄዱት በጨለማ እጅህን ስጥ ሲሉት እኔ በጨለማ እጀን አልሰጥም ሲል ጥቃት ሰንዝረው ቤቱን በቦንብ መትተው ሊገድሉት ሲሞክሩ የአልሞት ባይ ተጋዳይ ሆኖ ራሱን እየከላከለ እንዳለ የጎንደር ከተማና የአካባቢው ሕዝብ ፈጥኖ በመድረስ ከታፈነው እንዲወጣ ሲደረግ ሌሎች የሕይወት መሰእዋትነት ከፍለዋል እሱም ብዙ ሳይቆይ ወህኒ ቤት ገብቶ ዛሬ በሕሊና እስረኝነት ላይ ይገኛል።ያች የሐምሌ 5/2008ዓ/ም ጎንደር ላይ የፈነዳች ጥይት ምን እንዳስከተለች አገር ያወቀው ጉዳይ ነው።እንግዲህ ጅራፍ ራሷ ገርፋ ራሷ ትጮሃለች ሆነና ነገሩ ወራሪውና ተስፋፊው የህወሃት ቡድን ለምለም ሣርና መሬት ባየ ቁጥር ማራቁን ማዝረብረቡ የተለመደ ስለሆነ እኛ ስለወልቃይትና ጠገዴ ጠለምትና አርማጭሆ ጉዳይ እያወራን እነሱ ጠቅላላውን ሰሜን ጎንደርን መውሰድ አለብን በማለት በስሜንና ደቡብ ጎንደር ሕዝብ ላይ በየወሩ የጦርነት አዋጅ ያውጃሉ አሁን ደግሞ ያለ የሌለ ኃይላቸውን በመሳብ ወደ ጎንደር በማከማቸት ላይ እንዳሉ ይህንም ገዱ አንዳርጋቸው ታማኝ ባለመሆኑ አዲሱ ለገሰና በረከት ስምኦ እያማከሉ እንዲመሩትና የአማራውን የዘር ማጥፋትና ማጽዳት ለማሳለጥ ወደ ባህር ዳር በመሄድ የእልቂቱ ፊታውራሪዎች ተብለው ተሰይመዋል።
“”ስለዚህ አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ””በሚለው ብሂል የአማራ ሕዝብ ወንዝ ተራራ ሳይገድብህ በጎንደር እንዲቀጣጠል የተፈለገውን ሕዝብ የሚጨርስ የጦርነት አዋጅ በተባበረ ክንድ ለመመከት መዘጋጀት አስፈላጊ ነው ጊዜ መውሰድና ድርጊቱን አቅልሎ መመልከት በፍጹም መታሰብ የለበትም።በተለይ ከላይ የጠቀስኳቸው ሁለት ጅቦች ከኢህአፓ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ የአማራውን ሕዝብ እያስፈጁ የዘለቁና ሎሌነታቸውን ያስመሰከሩ ፀረ-አማራ ግለሰቦች ህወሃት ባህርዳር ላይ ወስዶ ማስቀመጡ የሰውን ስም በነቂስ ከቀበሌ እስከ ወረዳ ስለሚያውቁት ግጭቱ ከተከሰተ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት እያንዳንዱን የሚሰነዘር ጥቃት በጥበብ ለመመከት እንዲቻል ይታሰበበት።እያልኩ በውጭ የምንኖር አማራዎችና የአማራ ወገን የሆናችሁ በሙሉ ከሕዝቡ ጎን በመቆም የሚቻለውን ድጋፍና ትብብር እንዳንነፍገው እያልኩ ወገናዊ ጥሬየን አስተላልፋለሁ።

  • አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!!!።
“ አንተነህ ገብርየ”

No comments:

Post a Comment