Thursday, June 15, 2017

ሰበር ዜና: በሁመራና አርማጭሆ የተደረገው የእርቅ ሙከራ ከሸፈ | ወያኔ በወልቃይት ባህረሰላም ሃይል አንቀሳቀሰ | ዘጠኝ የሱዳን ወታደሮች ተገደሉ


Filed under      


ከሙሉነህ ዮሐንስ
(ሰኔ 7 2009) በኢትዮጵያና በሱዳን ድንበር በሁመራ መስመር ከወያኔ መሬታችንን ለመረከብ የገቡ 9 የሱዳን ወታደሮች በጎበዝ አለቆች እርምጃ ተወሰደባቸው። በወያኔ አጀብ በሁመራ መስመር የገባው የሱዳን ሃይል ተበታትኗል።
በወልቃይት ባህረ ሰላም በኩል ደግሞ ወያኔ ወደ ኢትዮጵያ በኩል ሰራዊት እያንቀሳቀሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ያልተለመደ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በቀጠናው እንደሰፈነ ኗሪዎች ጋልፀዋል። ይህ አካባቢ ወደ ኤርትራ ድንበር ጥግ ነው።

ወያኔ ሁመራና አርማጭሆ ላይ ያደረገው ላሞኛቹህ የእርቅ ሙከራ ከሸፈ። ሸማግሌዎች የተባሉት ብዛት 16 ሲሆኑ አብራሃጅራ ላይ አሰማራዉ መኮነን የተባለ የወያኔ ተላላኪ፣ አብደራፊ ላይ ዋኘዉ አብሃይ፣ ፋሲል አሻግሬ፣ አድምጠዉ ታደሰ፣ ሲሆኑ ዳንሻ ላይ የወያኔ አሽከር የሆነ በገዘብ ትግሬ ነኝ የሚል ካሰይ ሐብቱ ከ1986 ጀምሮ የወልቃይትና የጠገዴ ተወላጆች በገዘብ እየተገዛ ካሰገደለ በኋላ እነሱ የቀጠሩት ነው። እሱ እና ሌላው ሹምየ የተባሉት በሃገሬው ህዝብ ተከዜ ወዲህ ቤት እዳትሰሩ ተብለዉ የተወገዙ በመሆኑ ትግራይ ሄደው ቤት የሰሩ ናቸዉ። የጎንደርን ሕዝብ ወክለው በምንም መልኩ ከትግሬወች ጋር ሊነጋገሩ አይችሉም።
ይልቅ የአርማጭሆ ህዝብ ለምትገሏቸው ወንድሞቻችን ሃላፊነት ውሰዱ፣ የአሰራቹሃቸውን ወገኖቻችንን ኮለኔል ደመቀን ከወልቃይት ኮሚቴወች በሙሉ ፍቱ፣ መሬታችንን ልቀቁ፣ ማንነታችንን አክብሩ ብለው እቅጩን ነግረዋቸዋል።
ሁመራ ላይ በተደረገው የእርቅ ድራማ ደግሞ የተገኙት በሙሉ የትግራይ ተወላጆችና ወልቃይቴወች አልተገኙም። የስብሰባው መሪ የሆነው የወያኔ ሹም ህዝቡ ከወልቃይቴወችና ጠገድቸወች ጋር የማለሳለስ ስራ እንድትሰሩ ሲላቸው በአንድ ወላጁ ግማሽ ወልቃይቴ የሆነ ወጣት መንግስት የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ እሮሮ መስማት ሲገባቹህ የእናንተ አፈና ነው ይህን ችግር ያመጣው ብሎ በድፍረት ተናግሯል። በአጠቃላይ ወያኔ በእርቅ ስም የህዝቡን ትግል ለመቀልበስ የሞከረው ሙከራ ከሽፏል።
የጎንደር ህዝብ ወልቃይት ላይ ከ1972 ጀምሮ ከዛ ቆላማው ወገራ ከ1974 ጀምሮ እስከ ዳባት ላይ ደግሞ 1977 ጀምሮ አብዛኛው የጎንደር ቦታ ላይ እስከ 1983 ከወያኔ ጋር እጅግ ዘግናኝ ጦርነት ሲያደርግ ኖሯል። አሁን ደግሞ ፀረ ወያኔ ትግሉ ስልቱን እየቀያየረ ጎንደር ላይ ሳይቋረጥ ከሃምሌ 5 2008 ከጀመረ ድፍን አንድ አመት ሞላው።

No comments:

Post a Comment