Thursday, June 8, 2017

ግንቦት 29 ቀን 2009 የኮ/ል ደመቀ የፍርድ ቤት ውሎ








ቀጠሮዉ ተይዞ የነበረዉ
1. የዐ/ህግ ምስክሮች ሲቀርቡ ለመስማት
2.ተከሳሽ ከሰበዓዊ አያያዝ ጋር በተገናኘ ያቀረበዉን ቅሬታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ፍ/ቤተ ቀርቦ እንዲያስረዳ ነበር
በዚህም መሰረት
- ዐ/ህግ ሁሉም ምስክሮች አልቀረቡልኝም እና በተለዋጭ ቀጠሮ አቅርቤ ላሰማ በማለት አሳሰቧል
- የተከሳሽ ጠበቆችም አብዛኛዎቹ ምስክሮች የፀጥታ ሰራተኞች ከመሆናቸዉ አንፃር በአድራሻቸዉ በቀላሉ ማግኘት ስለሚቻል በዛሬዉ ቀጠሮ ምስክሮቹን አቅርቦ ማሰማት ነበረበት ፡፡ በመሆኑም በዐ/ህግ ቸልተኝነት ምክንያት ምስክሮቹ ማለት ስለሚችል ምስክር የማሰማት መብቱ እንዲታይልን በማለት አሳስበዋል ፡፡
ፍ/ቤቱም በዐ/ህግ በኩል ቸልትኝነት ያለ እና ተገቢዉ ክትትል በማድረግ ለማቅረብ ያለመሞከር መሆኑን ግንዛቤ ከወሰደ በኋላ ነገር ግን የመጀመሪያ ቀጠሮ ከመሆኑ አንፃር አንድ ተለዋጭ ቀጠሮ ለዐ/ህግ እንዲሰጠዉ ፍ/ቤቱ አምኗል በሚል ምክንያት የዐ/ህግ ምስክሮች ለመስማት ከሐምሌ 3-5 /2009 ቀጠሮ ሰጥቷል ፡፡
የሰብዓዊ መብት አያያዝን በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ኃላፊ ጀማል ሰዒድ ኮማንድ ፓስት ስላዘዘኝ ነዉ ተከሳሽ አሁን በተያዘበት ሁኔታ የተያዘዉ በማለት ያሳሰበ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ኮ/ልደመቀ ለብቻቸዉ ሁነዉ ተገቢዉን ጥበቃ እየተደረገላቸዉ እንደማንኛዉም ታራሚ መብታቸዉን የጠበቀ አያያዝ እንዲደረግ አዟል ፡፡ Muluken Tesfaw

No comments:

Post a Comment