
(ዘ-ሐበሻ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን አወዳይ ከተማ ባለፈው ዓመት 6 ህጻናት ወጣቶችን ገድሏል ተብሎ የታሰረውና ሰሞኑን ከ እስር የተፈታው የሕወሓት መንግስት ሠላይ ነበር የተባለው አብዱ እድሪስ ዛሬ በአካባቢው ነዋሪ ወጣቶች እርምጃ ተወስዶበት መገደሉ ተሰማ::
የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ በሰበር ዜናው ላይ እንዳስታወቀው ይህ የወያኔ ሰላይ 6 ህጻናት ወጣቶችን ቢገድልም ለይስሙላ በታሰሩ ወዲያውኑ ዓመት ሳይታሰር ተፈቷል:: ከተፈታ በኋላም የሟች ቤተሰቦችንና የአካባቢው ወጣቶችን ማስፈራራቱን መቀጠሉንም ዘግቧል:: መንግስት ይህን 6 ህጻናት ወጣቶችን በአወዳይ አደባባይ ላይ የገደለውን ግለስብ ከ እስር ሲፈታው ከነሙሉ ትጥቁ እንደነበር የዘገበው ኦኤምኤን በአወዳይ የሚገኙና የተደራጁት ቄሮዎች ዛሬ ገድለውታል::
እንደ ሚዲያው ዘገባ ቄሮዎቹ ወገኖቻቸውን የገደሉትንና ያስገደሉት ላይ ተመሳሳይ እርምጃዎች በተከታታይ ይወስዳሉ::
No comments:
Post a Comment