Thursday, June 8, 2017

በውጭ አገር የሚኖሩ የጌዴኦ ተወላጆች ህብረት ማዕከላዊው የሕወሓት መንግስት 5 ዕርምጃዎችን እንዲወስድ ማሳሰቢያ ላከ

በውጭ አገር የሚኖሩ የጌዴኦ ተወላጆች ህብረት በኩል የተሰጠ የአቋም መግለጫ፣ 
አሁን   በሥልጣን ላይ ያለዉ የህወሓት   መንግስት  አገሪቱን ማስተዳደር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ  ያልሆነውን ሆነ፣ያልተደረገውን ተደረገ ወይንም ሀሰትን ከትንሽ እውነት ጋር ቀላቅሎ  ኃላፊነት በጎደለው መልኩ  የኃሰት መረጃ አደራጅቶ ለሕዝብ በማቅረብ ለማሳመን መሞከር የተለመደ ሙያዉ አድርጎታል። በዚህም ሕዝቡን ሲያደናግር ቆይቷል፣ ዛሬም ይህንኑ ተግባር አጠናክሮ ቀጥሎበታል:: በመሆኑም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተደጋጋሚ የህወኻት መንግስት በሚያቀርበው የውሸት መረጃ ምክንያት እውነቱን ከውሸት ለመለየት የተቸገረበት ጊዜ ላይ ይገኛል።
በጌድዮ ደርሶ የነበረው ውድመት (ፎቶ ከዘ-ሐበሻ ፋይል)
በተመሳሳይ መልኩ የህወሃት መንግስት በቅርቡ ራሱ ባቋቋመው የኢትዮጵያ የሠብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተብዬውና ከአናሳዉ ገዢ መደብ አንዱ በሆነው ግለሰብ  በዶክተር አድሱ ገብረእግዛብሄር  በሚመራው ተቋም በኩል የተምታታ መግለጫ አዉጥተዋል።  ሪፖርቱ ከደረጃ የወረደ፣ አራምባና ቆቦ ዓይነት የሆነ፣ፊየል ወዲህ ቅምዝምዝ ወዲያ  እንደሚሉት የሆነና ሀቅና ሸፍጥ የተቀላቀለበት ነው።በሪፖርቱ እንደተመለከተው በደቡብ ሕዝቦች ክልል በጌዴኦ ዞን፣ በአከባበው ሕዝብና በከተማ ነዋሪዎች መካከል በጥቅምት ወር መጀመሪያ ላይ ለተከሰተው ግጭት መንስዔ ናቸዉ ተብሎ የተጠቀሱት በመጠኑም ቢሆን ትክክልነት ያላቸው ሲሆን፣ለችግሩ ተጠያቂነትን በተመለከተ ግን፣ ምንም የማይመለከታቸው ተቋማትና ግለሰቦች ተጠያቂ ተደርገዋል።  እንደችግሩ መንስዔነት ከተዘረዘሩት ውስጥ የመልካም አስተዳደር እጦትና ኢ-ፍትኃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል የሚሉት ይገኝበታል። የሚገርመው ግን ለነዚህ ችግሮች ተጠያቂ ተደረገው የቀረቡት የጌዴኦ ሕዝብና የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ጌሕዴድ/ ናቸው።

በርግጥም የአስተዳደር ብልሹነት በመኖሩ ምክንያት ነዉ ለይርጋጨፌ የቡና አምራቾች ማህበር የተመራዉና በከተማ ካርታ የማህበሩ ባሌበትነት የተረጋገጠበትን ቦታ፡ የዲላ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች ከላዩ ላይ ቆርሶ ለከተማ ነጋዴዎች ለመስጠት የቻሉት። ይኼም ድርጊታቸዉ ለዘመናት ተከባብሮና ተቻችለዉ አብረው በኖሩ ሕዝቦች መካከል ቁርሾ እንድፈጠርና ግጭት እንዲነሳ ምክንያት ሆኖዋል። እንደዚሁም ኢ-ፍትኻዊ የሃብት ክፍፍልን በተመለከተ በሪፖርቱ የተገለጸዉ እዉነትነት ያለዉ ነዉ።የገዴኦ ዞን ለሀገሪቱ የውስጥ አመታዊ ጠቅላላ ገቢ ከሃያ በመቶ አስተዋፆ የሚያደርግ መሆኑ የታወቀ ቢሆንም ከዚያ ዉስጥ የሚያገኘዉ ድርሻ በጣም እምንት የሆነ ነዉ። ባለፉት ሃያ አምስት አመታት ለክልሉ የተደረገዉ ልማታዊ ሥራ ከአይን የሚገባ አይደለም፤ ወጣቱ ትምህርቱንም ቢጨርስ እንክዋን ሥራ የማግኘቱ እድል በጣም የጠበበ ነዉ፤ የሥራ አጡ ብዛት ክጊዜ ወደ ጊዜ ወደ ላይ እያሻቀበ ይገኛል፤ በዚህ ሁኔታ ተስፋዉ የጨለመበት የወጣት ሃይል ወደ አመጽ ቢጋበዝ የሚደንቅ አይሆንም።

እንግድህ የመልካም አስተዳደር እጦትን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆን ያለበት አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረውና በመቆጣጠር ላይ ያለዉ በሕይወሃት የሚመራው በጣም የተማከለ የአዲሳበባዉ መንግስት ነው። የአከባቢ አስተዳደሪዎች የሚባሉት ማዕከላዊ መንግስት በፈለገ ጊዜ የሚያነሳቸውና የሚበውዛቸው ግዑዛን ፍጥረቶች ናቸው። ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ብቻ በጌዴኦ ዞን አሥራ ሰባት አስተዳዳሪዎች ተፈራርቆበታል፣ የጌደኦ ሕዝብ አስተዳዳሪዎቹን የመምረጥ ወይንም ከኃላፍነት ቦታቸዉ የማንሳት መብት የለዉም። ታዲያ ሕዝቡ አስተዳደሪዎቹን በማይመርጥበት ሁኔታና እጁ በሌለበት ጉዳይ ላስተዳደራዊ ብሉሽነት እንዴት ተጠያቂ ይሆናል? ምንም አቅም የሌለዉንና እራሱ ተበዳይ የሆነዉን ሕዝብ ተጠያቂ አድርጎ ማቅረብ የአምባገነንነት ልዩ ባሕሪዉ ካልሆነ በስተቀር ምን ሊባል ይቻላል። የጌደኦ ሕዝብ ለተፈጠረዉ ችግር ከቶዉንም ተጠያቂ አይደለም። በተጨማሪም የጌደኦ ሕዝብ ከሌላ አካባቢ የመጡ ኢትዮጵያዊ ወገኖቹን የሚጠላ ሳይሆን አቅፎ ደግፎ ያኖሬና የሚያኖር ደግ ሕዝብ ነዉ።

እንደዚሁም የተቃዋሚ ኃይሎችን በተለያዩ መንግዶችና ዘይቤዎች በማዳከም በኩል የተካነው ወያኔ ተሳክቶለት የጌዴኦ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅትን /ጌሕዴድን/ ጨርሶ ከሥራ ውጭ ካደረገው ዓመታት አልፎታል። ጌሕዴድ ተዳክሞ ደብዛው ከማይታይበት ደረጃ ላይ ያለ የፖለቲካ ድርጅት ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ ያለውን ድርጅት እንግዲህ ተጠያቂ አድርጎ በሪፖርቱ ማቅረቡ አጭበርባሪነትን ከማንጸባረቅ ውጭ ምን ሊባል ይቻላል። ወይንም ያዉ እንደተለመደዉ አንገታቸዉን ደፍተዉና ተደብቀዉ ያሉትን የጌሕዴድ አመራርና የተረፉ አባላትን አሳድዶ እስር ቤት ለማጎር ተወጥኖ ካልሆነ በስተቀር። ለነገሩማ “አያ ጅቦ ሳታማኻኝ ብላኝ” ያለችዉ የአህያ ተረት ካልሆነ በስተቀር ለወያኔ መንግስት ማንንም ለማሰር ምንም አይነት ምክንያት አያስፈልገዉም።
በጌድዮ ደርሶ የነበረው ውድመት (ፎቶ ከዘ-ሐበሻ ፋይል)
ከላይ በዝርዝር እንደተቀመጠዉ በኮሚሽኑ ሪፖርት እንደ ችግሩ መንሰኤ ሆነዉ የቀረቡትና ለችግሩ በተጠያቂነት እንዲፈረጁ የተጠቆመዉ ፈጽሞ የማይገናኙ ጉዳዮች ናቸዉ። ስለሆነም ነው ሀቅን ከሸፍጥ ጋር መደባለቅ መፍትኼ ሊሆን አይችልም የምንለዉ። በኛ እምነት መፍትሔ ሊሆን የሚችለው ለችግሩ መንስዔ ናቸው ተብለዉ የተጠቆሙትን ለይቶ በማውጣት ችግሮቹን ከሥረ መሠረቱ ለመፍታት ጥረት ማድረጉ ነዉ። በዚህም መሰረት በአከባቢው ሕዝብና በከተማ ነወሪዎች መካከል ደግመኛ ግጭት እንዳይነሳ ለማድረግ ከሁለቱም ወገን የተወጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች ዘላቂ የሆነ ዕርቅ እንዲፈጥሩና፣ በሕዝቦች መካከል የነበሩ ግንኙነቶች ቀድሞ ወደነበሩበት እንዲመለሱ ሁነታዎችን ማመቻቸት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን። እኛም በውጭ የምንኖር የጌዴኦ ተወላጆች አቅማችን በሚፈቅደው መጠን በህዝቦች መካከል የነበረው ወዳጅነት፣መከባበርና መቻቻል ከዚህ ቀደም ወደ ነበረበት ቦታ እንዲመለስ ጥረት የምናደርግ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
ማዕከላዊዉ የህወሃት  መንግስት በበኩሉ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲገኝ የሚሻ ከሆነ ከዘህ በታች ያሉትን ዕርምጃዎችን እንዲወስድ እናሳስባለን።
አንደኛ፣ ያለአግባብና ያለጥፋታቸው በዘፈቀደ ተለቅመው ያለፍርድ በእሥር ቤት የሚንገላቱ ግለሠቦች በአስቸክዋይ እንዲፈቱ፤
ሁለተኛ፣ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመው በሕዝቦች መካከል ግጭት እንዲቀሰቀስ ምክንያት የሆኑ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡ፤
ሶስተኛ፣ ጥፋተኝነታቸው ሳይረጋገጥና በሕግ ፊት ቀርበው ውሳኔ ሳያገኙ በጸጥታ ኃይሎች የተገደሉ ግለሰቦች ተለይተው ከታወቁ በኋላ ለቤተሰቦቻቸው የካሣ ክፍያ እንዲደረግ፣
አራተኛ፣ በግጭቱ ምክንያት ቤታቸውን ላጡና ንብረታቸው ለወደመባቸው የከተማ ነዋሪዎች በአግባቡ የካሳ ክፍያ እንዲፈፀም፣
አምስተኛ፣ የይርጋጨፌ ቡና አምራቾች ማህበር በዲላ ከተማ የተመራዉን ቦታና በካርታ ላይ የተቀመጠውን በመግመስ ለሌሎች ነጋዴዎች እንደገና አሳልፎ መስጠቱ አግባብነት የሌለውና አስተዳደራዊ በደል ስለሆነ፣ ባለቤትነቱ መሉ በሙሉ ለማህበሩ እንዲመለስና ያለአግባቡ ያታሠሩ የማሕበሩ መሪዎች እንዲፈቱ፣
ከዚህ በላይ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች የችግሩን መንስዔዎች ቀርፈው በሁለቱ ሕዝቦች መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ከሥር መሠረቱ ይፈታሉ የሚል ዕምነት አለን። የችግሮቹ መንስኤ ናቸው ከተባሉት ጉዳዮች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ግለሠቦች ወይንም ተቋም ተጠያቂ ማድረግና ብሎም ሀቅንና ሸፍጥን በመቀላቀል ለማደናገር መሞከር መፍትኼ ሊሆን የማይችል መሆኑን በሥልጣን ላይ ላለዉ መንግሥት ለማስገንዘብ እንወዳለን።
ሠላምና ፍትህ ለጌደኦ ሕዝብ!!
በዉጭ አገር የሚኖሩ የጌዴኦ ተወላጆች ህብረት
በግጭቱ ምክንያት ቤታቸውን ንብረታቸው ለወደመባቸው የከተማ ነዋሪዎች በአግባቡ
ክፍያ መፈጸም፣
5 ኛY-                    የይርጋጨፌ ቡና አምራቾች ማህበር በዲላ ከተማ የተመራዉን ቦታና በካርታ ላይ
ተቀመጠውን በመግመስ ለሌሎች ነጋዴዎች እንደገና አሳልፎ መስጠቱ አግባብነት የሌለውና
አስተዳደራዊ በደል ስለሆነ፣ ባለቤትነቱ መሉ በሙሉ ለማህበሩ እንዲመለስና ያለአግባቡ
ያታሠሩ የማሕበሩ መሪዎች እንዲፈቱ ማድረግ ተገቢ ነው እንላለንYY
ከዚህ በላይ የተቀመጡ የመፍትሔ ሃሳቦች የችግሩን መንስዔዎች ቀርፈው በሁለቱ ሕዝቦች
መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ከሥር መሠረቱ ይፈታሉ የሚል ዕምነት አለንYY የችግሮቹ
መንስኤ ናቸው ከተባሉት ጉዳዮች ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸውን ግለሠቦች ወይንም
ተቋም ተጠያቂ ማድረግና ብሎም ሀቅንና ሸፍጥን ለመቀላቀል መሞከር መፍ

No comments:

Post a Comment