Tuesday, June 6, 2017

ብርቱካን ሚደቅሳ-በዝምታዋም እማትረሳ። *****


በ2016 ሰኔ፣ሀምሌ እና ነሀሴ ወራቶች ውስጥ የብርቱካን ሚደቅሳ ስም በየማህበራዊ ድህረ-ገጾች ላይ ይወጣ ነበር።ወቅቱ በአገር ቤት ያለው -በኦሮሚያ፣በጎንደር እና በጎጃም ያለው ሕዝብ የህወሃት ጭቆና፣ግፍ እና አምባገነናዊ አገዛዝ በቃኝ ብሎ በመነሳት ለመብቱ እና ለነጻነቱ የሚታገልበት ነበርና ታግሎ በማታገል ታላቅ ከበሬታን፣ተደማጭነትን እና ከፍተኛ ተቀባይነትን ያተረፈችውን የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ድርጅት ምክትል ሊ/ር ብርቱካን ሚደቅሳን በእጅጉ የሚፈልጉ ሰዎች በርክተው ነበር። ሆኖም የትንታጋን ብርቱካን ድምጽ የቱንም ያህል ተናፍቆ ቢፈለግ፣ፖለቲካዊ አመራራና ህዝብንም የማስተባበር ክህሎታ ተፈልጎ ቢናፈቅ ትንታጋ ብርቱካን ግን ዝም እንዳለች በዝምታዋ ካባ ተሸፍና ሳትደመጥና ሳትታይ ቀረች።
ከአንድ ዓመት በሃላ ሰሞኑን ብርቱካን በማህበራዊ ድህረ-ገጾች ላይ ከብቸኛ ልጃ ጋር ሆና የተነሳችውን ፎቶ ተሰራጭቶ ሳይ ስለ እሳ አንድ ነገር ለማለት ወስንኩና ብእሬን አነሳሁ [ዘወትር-ከትየባ በፊት በብእር ነውና እምከትበው] ይህን የእናትና ልጅ ፎቶ አተኩሬ ተመለከትኩ-ደህንነታን እና አንድዪ የሆነችውን ልጃን በማግኘታ ከፈጠረብኝ ደስታ ይልቅ በብርቱካን ላይ የተለምዶው ልበ ሙሉነት፣ተስፋማነትን እና ጉጉነትን ገላጭ በማጣቴ የፈጠረብኝ ቅሬታ እና ቁጭት ሃይሎ ተሰማኝ። በእርግጥ ፎቶው እሳነታን እንጂ ያለችበትን ሁኔታ፣ያለችበትን አስተሳሰብ ቃላት ሆኖ አይናገር -ብሎም የተሰማኝን የቁጭት ስሜት ላይ እንዳለች አይገልጽ ይሆናል። ምናልባትም የተሰማኝ ስሜት ከእነ አካቴው በራሴው እይታና ግምት ስለ እሳ በፈጠርኩት እይታ ምክንያት የተፈጠረ እንጂ የብርቱካን ሚደቅሳ ወቅታዊ ሁኔታ በተቃራኒው ስፍራ ያለ ሊሆን እንደሚችልም መገመቱ አያስኮንነኝም።የሆነው ሆኖ -የቁጭት ስሜቴ ብርቱካንን ወደ ሃላ ተመልሼ እንድፈልጋት አስገደደኝና ወደ 1992 ዓ.ም ተወርውሬ ተመልስኩ።
**የብርቱካን ሚደቅሳ አነሳስ በ1992 ዓ.ም አዲስ-አበባ።
የግንቦቱ ምርጫ ከመካሄዱ ስድስት ወር ቀደም ብሎ በአቶ አሰፋ የሚመራው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ኮሚሽን በግዮን ሆቴል ለመንግስት ጋዜጠኞች እና ለነጻ ፕሬስ አባላት ስለ ግንቦቱ ምርጫ የአንድ ቀን ሴሚናር አዘጋጅቶ አብዛኞቻችን ታድመናል። ከጋዜጠኛ ሌላ ውስን የፓርላማ አባላት [አቶ በድሩ አደም]እና በግል ለመወዳደር ከተመዘገቡት ውስጥ ተጋብዘው ከተገኙት ውስጥ ብርቱካን ሚዴቅሳ ብቸኛዋ እንስት ተሳታፊ ነበረች። ትውውቃችን የተጀመረበት እለት ማለት ነው። በወቅቱ እሳ በዳኝነት ሙያ ምንሊክ አደባባይ በሚገኘው አራዳ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት በተዘነጋኝ [4ኛ ይሁን 6ኛ ወንጀል ችሎት]ችሎት የመሃል ዳኛ ሆና የምታገለግል ነበረች። ብዙም ስይቆይ -ምንአልባትም በየካቲት ወር ውስጥ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች -ከኦሮሚያ ክልል የመጡ በባሌ ደኖች የተነሳውን ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት በእንዝመት አትዘምቱም ጸብ ከስርዓቱ የጽጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት መፍጠሩ ወሬ ደረሰን። በግጭቱም ተማሪዎቹ ታፍሰው መታሰራቸውን እና ብሎም አራዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ወጣት በሆነች የመሃል ዳኛ ቁርጥ ውሳኔ በመንግስት ተከሰው የቀረቡትን ተማሪዎች በሙሉ በነጻ መለቀቃቸው ዜና ደረሰኝ። አፍታም ሳይወስድብኝ ሩጫዪን ወደ አራዳ ፍርድ ቤት አደረኩ።የዚህ ውሳኔ ሰጪ ዳኛ ከወራት በፊት በግዮን ሆቴል እጩ በግል ተወዳዳሪ መሆናን የገለጸችልን ዳኛ ብርቱካን መሆናን ሳይ አግራሞቴ ጨምሮ ለአጭር ቆይታ ሰዓታን ተሻምቼ ክፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ ይዣት ወጣሁ።
በእለቱም ሆነ ከዚያ በሃላም ተከታታይ ወራቶች ዘወትር ከስራ በሃላ አራት ኪሎ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ጀርባ ባለው ካፍቴሪያ እየተገናኘን ስለ የኢትዮጵያ ሁኔታ-በተለይም ስለ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፖሊሲ-ስለ ተቃዋሚው ክፍል ስለ ኤሊቱ የህብረተሰብ ክፍል ንቃትና ተሳትፎ ያደረግናቸውን ረዥም ሰዓታትን የፈጁ ውይይቶች አንዳንዴም ክርክሮችን መቼም ቢሆን የምረሳቸው አይደሉም።
አንዳንዴ እንደ ማቹ ጋዜጠኛ ደበበ ዱፌራ፣ የክልል 14 የፋይናንስ ሃላፊ በመሆን ህወሃት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በሃላ ለአጭር ግዜ ሰርቶ የነበረው ሙሉጌታ በውይይታችን ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑበት አጋጣሚ ነበር። ብርቱካን በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ የታወቀችበትን በፓርቲያቸው አሳሪነት ታስረውና ተከሰው የነበሩትን አቶ ስዪ አብርሃን ጉዳይ መርምራ በነጻ ያሰናበተችበት የ1993 ችሎት በፊት በርከት ያሉ ግን በመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ያልተሰጣቸውን ተመሳሳይ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ በነጻው ፕሬስ መንደር በደንብ እውቅናን ያተረፈች ስትሆን-ጎልቶ የታየላት እና የታወቀላት ውሳኔዋ ግን በአቶ ስዪ አብርሃ ላይ በወሰነችው ውሳኔዋ ነበር። የሚገርመው ያው ውሳኔዋ በኢትዮጵያ ውስጥ በዳኝነት ሙያ የመንግስት ተቀጣሪ ሆና እንዳትቀጥል የወሰነባት ሆኖ መገኘቱ ነበር።
በዳኞች ውስጥ ባሉት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬ ባለሙያዎች እና የበላዮቻ የሚደርስባትን ሙያዋን ፈታኝ አሸማቃቂና አስበርጋጊ ተጽእኖዎችን በጸጋ ተቀብላ እንደ አብዛኞቹ ፍትህን እያዛቡ እንደሚዳኙት “ዳኞች” የስርዓቱ መጠቀሚያ ከመሆን እምቢ ታማኝነቴ ለፍትህ ተገዢነቴም ለእውነት ነው በሚል አስተሳሰባ እና አቃማ የዳኝነት ሙያዋን በማስከበር ትንታግ የሆነች ዳኛ ነበረች።
በፖለቲካው ዙሪያ ክርክራችን ላይ ብርቱካን “ለምንድነው የኢትዮጵያ ምሁራን እንደነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣አቶ ክቡር ገናን የመሳሰሉት -በህብረተሰቡ ውስጥ ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች በፖለቲካው ውስጥ እማይሳተፉት? ለምንድነው ሕዝቡን ከመቀስቀስ ይልቅ እራሳቸው ድርጅት ፈጥረውና ተደራጅተው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን እማይታገሉት” እያለች አዘውትራ ትናገረኝ ነበር። በእርግጥ ብርቱካን ይህን በምትናገርበት ወቅት-በአቶ ክቡር ገና የሚመራው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት “ምረጥ አዲስ” በሚል መፈክር የአዲስ አበባ ህዝብ በግንቦቱ [የ1992ዓ.ም ማለቴ ነው]አገር አቀፍ ምርጫ ላይ ይጠቅመኛል ብሎ የሚያምንበትን እጩ ለመምረጥ ከአሁኑ በመራጭነት ተመዝግቦ እንዲሳተፍ የቅስቀሳ ዘመቻ እያካሄዳ የነበረበት ወቅት ሲሆን በአብዛኛው ህዝባዊ ውይይት መድረኮች ላይ እየተጋበዙ ንግግርና ማብራሪያ ከሚሰጡት ውስጥ የኢሰመጉው ሊ/ር ፕ/ር መስፍን ወልደማሪያም እና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚስቶች ባለሙያ ማህበር ፕ/ት ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ነበሩ። ይህ ምረጥ አዲስ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት በህዳር ወር 1992 ዓ.ም ላይ በአቶ ልደቱ አያሌው የተመሰረተው ኢ.ዴ.ፓ ምንም ዓይነት ህዝባዊ ተቀባይነት የሌለው ጮርቃ ድርጅት ከመሆኑም ባሻገር የድርጅቱ መስራችና መሪም አቶ ልደቱ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ተክተው አገር ለመምራት የሚያበቃ አቅምና ብቃት ስለሌላቸው-ብሎም በፕ/ር አስራት ወልደየስ የተመሰረተው መ.ዐ.ህ.ድ መሪ የ75 ዓመት አዛውንቱ ቀኝ አዝማች ነቅዓጥበብም ይህንን ክፍተት መሙላት የሚችሉ ስላልሆኑ እና በአንጻሩም ጠንካራና ብቁ ከሚባሉት ውስጥ እንደ ዶ/ር ታዪ ወልደሰማያት በእስር ቤት የፕ/ር አስራት ወልደየስ ምክትል የነበሩት ኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ድርጅታቸውን ለቀው በመውጣት በጀርመን ይኖሩ ስለነበረ ነው ብርቱካን ለምንድነው እንደነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣አቶ ክቡር ገና እና አቶ ብርሃነ መዋን የመሳሰሉት በፖለቲካው ውስጥ ገብተው እማያሳተፉት እያለች ስትሞግተኝ የነበረው። በእርግጥ ሁለቱም ምሁራን ፕ/ር መስፍን እና ዶ/ር ብርሃኑ በወቅቱ በምረጥ አዲስ ዘመቻ በየመድረኩ እየተገኙ በምርጫ የመሳተፍን እጅግ አስፈላጊነት፣ጠቃሚነት እና ወሳኝነት በህረበተሰቡ ንቃተ ግንዛቤ ደረጃ በሚገባ ሲገልጹ እና ሲተነትኑ እንደነበረ የሚረሳ አይደለም።
ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ በ1987 ዓ.ም ህግ-መንግስቱን ካጸደቀ ባሃላ ለማካሄድ ባሰበው የ1992ቱ አገር አቀፍ ምርጫ ላይ አዲስ ህግ በተቃዋሚ ድርጅቶች ላይ አውጥቶ ነበር። ህጉ በሁለት ምርጫ ላይ ሳይወዳደር እራሱን ያገለለ የተቃዋሚ ድርጅት ፍቃድ ተነጥቆ ይታገዳል የሚል በመሆኑ በ1987ቱ ምርጫ ላይ ያልተሳተፉት እንደነ መ.ዐ.ህ.ድ አይነቶቹ ድርጅቶች ሳይወዱ በግድ [ላለመታሸግና ላለመታገድ]የ1992ቱን ምርጫ ላይ መሳተፍ እንዳለባቸው በታወቀበት ግዜ በአቶ ክቡር ገና የሚመራው የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ምሁራንን ተሳታፊ ያደረገ “ምረጥ አዲስ” ዘመቻን ከፍቶ የምርጫን ምንነት እና በምርጫው የመሳተፍና ያለመሳተፍን ጥቅምና ጉዳት በመግለጽ ስራ ሲጠመድ ዋና ተዋናዩቹ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ነበሩ።
ብርቱካን ሚደቅሳ በ1992ቱ አገር አቀፍ ምርጫ በፈረንሳይ ለጋሲዮን የምርጫ ወረዳ በግል ተወዳዳሪነት ለመሳተፍ እጩነታን ስትገልጽ ብርቱ ተፎካካሪዋ እንደሚሆኑ የገመትናቸው በግል የፖርላማ አባል የሆኑት ሻለቃ አድማሴን ነበር። የማሸነፊያዋን ፕላን ከማውጣት ጀምሮ በአጠቃላይ በምርጡኝ ዘመቻዋ እለት ተእለት የጋሪዮሽ እንቅስቃሴያችን ወቅት የብርቱካንን ለዓላማዋ ማችነት፣ብርቱ የሆነ በራስ ታማኝነት እና የነበራትን ጥርት ያለ አገራዊ ህልምና ምኞት በጥልቀት እንድረዳ ችያለሁ። ለመጀመሪያ ግዜ በፈረንሳይ ለጋሲዮን በተከራየነው ታክሲ በየጉራንጉሩ እየዞርን የምረጡኝን ቅስቀሳ በራሳ በብርቱካን አንደበት በማይክራፎን በምትቀሰቅስበት ወቅት-እማይረሰኝ ነገር-ማይክራፎኑን ይዤ የምረጣትን ቅስቀሳ ላሰማ ስል ..”ወንዴ ተወዳዳሪው እኔ እንጂ አንተ አይደለህም። በአንተ የቅስቀሳ እርዳታ ባሸንፍ የምሰራው ግን እኔ እንጂ አንተ አይደለህም” የሚል ትእዛዝም በሉት ትሁት አስተያየት ነው የተሰጠኝ።በቃ ከዚያች ደቂቃ በሃላ ከጎና ሆኜ በማዳመጥና በመከተል ብቻ የምረጡኝን የቅስቀሳ ዘመቻዋን ልንፈጽም ችለናል፡፣
በፖርላማ ውስጥ በደፋር ተናጋሪነታቸው እና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ዘረኝነት፣ጸረ-አገርነት ብሎም የጠ/ሚር ታምራት ላይኔን በህዝብ ተጠሊነት በይፋ በመናገርና መንግስትን በማብጠልጠል የታወቁት ሻለቃ አድማሴ በ1992ቱ ምርጫ ብርቱካን ሚደቅሳን በትንሽ ድምጽ ብልጫ በልጠው በማሸነፋቸው ጥረታችን በውቅቱ ያለድል ሊደመደም ቻለ።
ሆኖም- ከ5 ዓመት በሃላ እኔ በአገር በሌለሁበት ብርቱካን “በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለምን አይሳተፉም።አገራችን እጅግ ትፈልጋቸዋለች” ስትላቸው ከነበሩት ምሁራን ውስጥ ከፕ/ር መስፍን ወልደማርያም እና ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር በመሆን ቀስተ ደመና የተሰኘውን ፖርቲ በማቃቃም ቅንጅቱን በመፍጠር የኢንጂነር ሃይሉ ሻውል ምክትል በመሆን ህወሃትን ከስሩ መንቅሎ ለመጣል ያስቻለን ህዝባዊና አገራዊ ስራ መስራታን መስማትም ሆነ ማየትን ቻልኩ።
የ1997ቱ የቅንጅት ውጤት የ1992ቱ በአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት አዘጋጅነት በእነ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም እና በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ መሪ ተዋናይነት መሰረት የተጣለለት የመምረጥና አለመምረጥ ትምህርት ውጤት እንደሆነ ይታያል።
ብርቱካን በመጀመሪያው ዙር እስር ማለትም በ1998 እስከ

No comments:

Post a Comment