Friday, June 2, 2017

የትግራይ በልማት መጎዳት ነገር.. አሳ ጎርጓሪ… | ከሃብታሙ አሰፋ



<<ትግራይ በልማት ወደሁዋላ ቀርታለች!>> የሚለው የሰሞኑ ለቅሶ አንዳንዶች የተዘጋ ፋይል በግድ እንዲከፈት እየጎተጎቱ ይመስላል።ስርዓቱ ፍትሐዊ አይደለም ሲባል የአማራው እንግዳ ቡድንን ባህርዳር ከነማን <ካልገደልን> ብለው በአስለቃሽ ጭስ የተበተኑት የትግራይ ልጆችና በሰላማዊ የእሬቻ ሀይማኖታዊ በዓል ላይ እጃቸውን ወደ ላይ ለሰላማዊ ተቃውሞ ባመሳቀሉ ላይ ጥይት ማርከፍከፍንም ይጨምራል።ዜጎች እኩል ሊታዩ ይገባል ለማለት ነው። አንዱ አላግባብ የሚገደል መሆን የለበትም።

አልመዳ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ
የሰሞኑ የትግራይ በልማት ወደ ሁዋላ ቀርታለች፣ በፌዴራሉ መንግሰት ተበድላለች አይነት ለቅሶ በበጀት ዋዜማ መሆኑ ብዙ የተዘጉ ፋይሎች እንዲከፈቱ ያበረታታ ይመስላል። ለመሆኑ ትግራይ ከማን ጋር ተወዳድራ ነው ወደ ሁዋላ የቀረችው? ከአሜሪካ ወይስ ከስዊዘርላንድ? መቼም ከአማራ፣ከኦሮሚያ፣ከሱማሌ፣ከደቡብ ወዘተ እያላችሁ በማስረጃ እንደማትሞግቱን ተስፋ አደርጋለሁ። ትግራይን ጨምሮ ሁሉም የአገሬ ሕዝቦች የሚኖሩበት ቦታ በልማት ቢያድግ እመኛለሁ። ላለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት ትግራይ እንደ እናት ልጅ ሌላውን አንዳንዱን እንደጠላት የቀረውን እንደ እንጀራ ልጅ የሚያይ ስርዓት <<የፌደራል>> የሚል ታርጋ ስለተለጠፈለት እንውቀሰው ካላችሁ ለምን ለትግራይ ክልል አደላ በሚል ካልሆነ << ጩኸቴን ቀሙኝ>> አይነት የሰሞኑ ለቅሶ ውሃ አይቋጥርም።
የአንድ አገር ብሄራዊ ዳቦ (በጀት) ባለፉት ሃያ ስድስት ዓመታት እንዴት ሲከፋፈል እንደነበር፣ተሰርቆም፣ተለምኖም የመጣው ሁሉ በአድልዎ አንዴት ለትግራይ ክልል ቅድሚያ በሚል ይሄድ እንደነበር ብዙ ማስረጃ መዘርዘር ይቻላል።<<ይሄ ሁሉ ተግዞ የትግራይ ክልል ከሌላውም አፍ እየተቀማ ተወስዶ ያን ያህል አልተጠቀመም!>> የሚል ቅሬታ የሚያቀርብ ቢኖር ፍትሐዊ ያልሆነውን ስርዓትና አመራር መደገፉ አንድ ነገር ሆኖ ጆሮ ገብ ስሞታ ሊሆን ይችል ይሆናል።
በየዓመቱ የአገሪ በጀት ይደለደላል። የበጀት ስሌቱን ዛሬ <<ትግራይ ተደብላለች>> የሚሉት እንዴት እንደተሰራ መለስ ብለው ቢያዩት እንመክራለን።በአጭሩ ሕወሃት በሚቆጣጠረው የፌዴሬሽን ም/ቤት ከየክልሉ ለም/ቤቱ በተወከሉ ፖለቲከኞች የበጀት ድልድሉ ቀመር ይጸድቃል። ባለፉት ሃአ ስድስት ዓመታት፡ኢሄ ድራማ እንደቀጠለ ነው። መጀመሪያ በጦርነት የተጎዱ ክልሎች ልዩ ድጎማ ይሰጣቸዋል ተባለ።በዚህ ሒሳብ ከአቅሟ በላይ( በጀት ስሌቱን ይሄን ታሳቢ ያደረገ በማድረግ) ተቀም ያለ በጀት ለትግራይ ተደጋግሞ ተሰጥቷል።
ከዛሬ 13 ዓመት በፊት አንድ ቀን ለዘገባ ወደ ፓርላማ ስሄድ በአጋጣሚ በሌላ አዳራሽ የጦፈ ክረክር መኖሩን አንዱ አባል ሹክ ይለኛል። ጉዳዩን ለመስማት <<የሕዘብ ተወካዮች>>(እነሱ የሚጠሩበት ስም ስለሆነ ይቅርታ) የፓርላማ አባላት ተብዬዎቹን ስብሰባ ተውኩና በዚያው በፓርላማ ጊቢ አጠገቡ ወደሚገኘው የፌዴሬሽን ም/ቤት ገባሁ።እነዚህ ፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት በቀጥታ ከክልሉ ተወክለው የሚመጡ በመሆኑ ብዙዎቹ የየክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ናቸው። የዕለቱ ውይይት የበጀት ቀመር ስሌቱ ላይ ለመወሰን ነበር። ይሄ ደፋር ም/ቤት በአገሪቱ በጀት ስሌት ላይ ብቻ ሳይሆን በሕገ መንግስቱም ላይ ፈራጅ ነው። ዳኞች በግልጽ ለሚያዩት ሕገ መንግስቱን የጣሰ ክስም ሆነ አቤቱታ <<ይሄ ሕገመንግስታዊ አይደለም >>የሚል ቅሬታ ሲቀርብ ወዲያው ወደዚህ ም/ቤት ይልካሉ፤ይሄ ም/ቤት ከአልሆነ ሌላ ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ስልጣን የለውም። ለበጀት ድልደላው መሰረት የሆነውም ቀመር የሚወሰነው በዚህ ም/ቤት ነው:፡ ታዲያ በዚያ ዕለቱ ስብሰባ የበጀት ቀመሩን ለመወሰን የትግራይ ክልልን ወክለው ከሚገኙት፡ፌዴሬሽን ም/ቤት አባላት መካከል አቶ ሐሰን ሺፋ በጊዜው የፌዴራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ፣ዶ/ር ሰለሞን ዕንቋይ የክልሉ ሌላ ባለስልጣን መገኘታቸው ትዝይለኛል።የአፋር እና የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንቶችም ነበሩ። የሆነው ሆኖ ውስጥ ውስጡን ሲብላላ የነበረው ከበጀቱ በህዝበ ብዛት ስሌት ለመቶኛ ሲካፈል በዚያም በዚህም እየተባለ ዛሬ ተጎዳች የተባለችው ከአገሪቱ ህዝብ 6 በመቶውን ምትኢዘው ትግራይ ያለ ማጋነን በአካፋ ይዛቅላታል። የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል ሆኖባቸው ነው መሰል አንዳንድ ክልሎች የበጀት ስሌቱ ቀመር አግባብ አይደለም የሚል ስሞታ በዜያ ስብሰባ ላይ ያነሳሉ።ሕወሓት ይህ መሰሉ ጥአቄ አንዳንዴ በተለያዩ ክልሎች ሲነሳ <<የትግራይ ሕዝብ ደመኞች>> እያለ በማሸማቀቅ ጥአቄውን ሲያዳፍን ቆይቷል። በዕለቱ የቤንሻንጉሉ የጊዜው ፕሬዝዳንት ያረጋል አይሸሹም እየደጋገመ በተለይ ትግራይና ቤንሻንጉልን ጨምሮ አነስተኛ ሕዝብ ያላቸው ክልሎች ለቀመሩ የሕዝብ ብዛት በመቶኛ ከፍ ብሎ ከተሰጠ እንደሚጎዱ በማስታወስ ሰፋ ያለ ዲስኩር እንዲያደርግ ተደረገ:፡ በተናገረ ቁጥር እነ ሐሰን ሺፋን እየደጋገመ ዞሮ ማየቱ ሰውዬው ከሁዋላ በሱ በኩል ሆን ተብሎ እንዲነሳ የተፈለገ አጀንዳ ለመኖሩ ግልጽ ነው። ሕወሓት እንደልቡ ከሚጨፍርባቸው ሰዎች አንዱ ያረጋል ነው። እንደልቡ ከሚጋልብበባው ክልሎች ቤንሻንጉል ክልል አንዱ ነው:፡ ቁጥር የገባቸው በመጠኑ ለማስረዳት ሞከሩ። አንዳንዶች ፈራ ተባ እያሉ የሕዝብ ብዛት በቀመር ስሌቱ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ፣መሰረተ ልማት ወደሁዋላ መቅረቱን ቁጥር እያስደገፉ ለማስረዳት ሞከሩ። አጠር አጠር ያለ አስተያየት ሲሰጥ የቆየው ሐሰን ሺፋ ቆጣም ከረርም እያለ በምክር ቤቱ ያሉትን ለማሸማቀቅ እሱ የትግራይ ሕዝብ ደመኞች ያላቸውን እየጠቀሰ የቀረበውን ለሕዝብ ብዛት የበለጠ ይሰጥ የሚለውን አጣጣለ። ሕዝብ ብዛት እየተባለ ቅድሚያ የበጀት ቀመሩ ከፍተኛ ድርሻ ከያዘ በጦርነት ተጎዳችው ትግራይ ተጠቃሚ እነደማትሆን ዘረዘረ። ለይስሙላ የተደረገው ውይይት ሐሰን ሺፋ ያስረገጠበትን ሀሳብ መሰረት ያደረገ ውሳኔ ተላለፈና ተዘጋ።በዚህ ቀመር ስሌት በጀት ይመደብና <<ፓርላማው>> ሰኔ 30 ለእረፍት ከመዘጋቱ በፊት አጸደቀው ይባላል፡:
የበጀቱን ጉዳይ ያነሳሁት በአገሪቱ ሕዝብ ስም የተገኘ ገቢ፣ከብድርና ከዕርዳታ ከሚመጣው ማን የአንበሳውን ድርሻ ሲቀረጥፍ እንደኖረ በግልጽ ያሳያል ብዬ ነው። ከዚህ በተረፈ በእነ ኢፈርት ስም ከዚህ በጀት ጨምሮ ከየባንኩ የተዘረፈው፣ የመሰረተ ልማት፣የፋብሪካዎች አይነትና ቁጥር ፣በሰበዓዊነት ተግባር የመጡ መንግስታዊ ድርጅቶች ሳይቀር በአማራ፣በኦሮሞ፣በሶማሌ ሆነ በሌላ ክልል ለመስራት ያመጡትን ፕሮጀክት አጥፈው ዛሬ ተበደለች ወደተባለው ትግራይ ካላዞሩ ፈቃድ እንደማይሰጣቸው እየተነገራቸው አንዳንዶች ያንን ሲፈጽሙ ጥቂቶች እየጣሉ ወጥተዋል፡፡በዚህ አድሎዋዊ ሆን ተብሎ በተሰራበት ፖሊሲ ሳቢያ ህብረተሰቡን በልማት ተጠቃሚ ሊያደርጉ የሚችሉ ፕሮጀክቶች ወደ አንድ አካባቢ(ትግራይ) በብዛት እንደሚገፉ ተደጋግሞ የተዘገበ ነው:፡ በእርግጥ በአማራ ክልል ዕድሜያቸው ያልደረሱ ህጻናትን ለማምከን ዘመቻ ጭምር እተደረገ የ10 ዓመት ህጻናት ሳይቀር ወሊድ መከላከያ ከለፍላጎታቸው በክንዳቸው እየተቀበረ መካን እነዲሆኑ ተፈርዶባቸዋል። ህጻናት በጊዜ ክትባት አጥተው ከተወለዱት በስንት መቶኛ አንደሚሞቱ ይህም ቁጥር ከትግራይ በስተቀር በተለይ በአማራና በኦሮሚያ ክልል ብዙ መሆኑን ባለፈው ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖምን ለመቃወም የራሱ ስርዓቱ ያሰራጨወን ማስረጃ ይፋ ያደረገው የአማራ ባለሙያዎች ጥናት ያሳያል።

የትግራይ ተሟጋቾች ይሄ ማለት እያንዳንዱ የትግራይ ሕዝብ ተጠቀመ ማለት ነው ተብሏል ብለው አጀንዳ ለማስቀየር ወይ ለማደናቆር ሲሞክሩ ይገርመኛል።ዛሬም ድንጋይ ላይ ተቀምጠው የሚማሩ ህጻናት ኢትዮጵያውያንን እያየን፤ በበጀቱ ዋዜማ <<በተቃዋሚ ታጋዮቹ>> አንደበት የሚደለቀው የባቡሩና በልማት ወደ ሁዋላ መቅረት ዜማ ሌላው ቀርቶ የድሬዳዋን ከተማ ሕዝብ መከራና ድህነት ያየ አይታዘባችሁም? ዛሬም በሰው ጫንቃ በምጥ የተያዘች እናት ብዙ ኪሎ ሜትሮች እየተጓዘቸ መንገድ ላይ ሕይወቱዋ በሚያልፍበት አገር፣ዜጎች በገፍ ስራ አጥ ሆነው የብሔራዊ ዳቦ ድርሻቸው በአድልዎ እየተቀማ፤ ከቆሻሻ ላይ እስከመብላት ሲደርሱ፣ቆሻሻ ላይ ኖረው በቆሻሻ ተቀብረው ሲሞቱ ይሄን ስርዓት ያቆመ ሕወሓት በበላይነት እያስተዳደረ <<ባቡር…በልማት ቀረን ተበደልን….>> ስትሉ አታፍሩም? ባይሆን ሲታደግም ፍትሀዊ በሆነ መንገድ በአገሪቱ ሀብትና በእዳ ከመጣ ሀብት እኩል ካልሆነ ሌላው የበይ ተመልካች የሚሆንበት ስርዓት ለአገር አደገኛ መሆኑ እንዴት አይገለጥላችሁም? ዘንድሮ እናቱ የሞተችበትም ውሃ የወረደችበትም እኩል ያለቅሳል ሆኖ እንጂ በእውኑ በልማት የተጎዳችው ትግራይ ከየትኛው ክልል ጋር ተወዳድራ ነው? መቼም እዛ ሰፈር ማፈር ከቀረ 26 ዓመቱን አክብሯልና ዓለም አቀፉ የሒሳብ ስሌት እኛ ሳናውቀው ተቀየረ እንዴ? በሉ አንግዲህ አሳ ጎርጉዋሪ አይደል ከነተረቱ ሁሉም እንዴት እየተጎዱ እንደኖሩ ያቅሙን ይጸፍ።ፈርዶብናል እነሱ ከረሱት ማስታወስ ምን ይከፋል።

No comments:

Post a Comment