Thursday, August 3, 2017

በአዲስ አባባ የመጠጥ ዉሃ እና የኤሌክትሪክ ኅይል እጥረት ተከስቷል


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 



file photo
ይድነቃቸው ከበደ

በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የንፁህ መጠጥ ዉሃ እጥረት ተከስቷል። በከተማዋ ከሚያጋጥመዉ የመጠጥ ዉሃ መቆራረጥና መጥፋት ባሻገር የንጽህና ጉድለትም ሌላዉ አሳሳቢ ችግር ነው ።በከተማው ውስጥ የተፈጠረው የዉሃ እጥረት ችግር ተከትሎ ፤ ከመኖሪያ ቤት እረጅም እርቀት በመጓዝ ለበርካታ ስዓታት በመሰለፍ ለአንድ ጀሪካን ዉኃ እስከ 20 ብር ግዢ እየተፈጸሙ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ነዋሪ የዝናብ ዉሃ በጀረኪና እና በባልዲ በማጠራቀም የእለት ፍጆታን እንደ-አማራጭ እየተጠቀመ ነው። የዉሃ መጥፋትና መቆራረጥ በአዲስ አበባ የተለመደ ችግር ሲሆን፣ የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት የሚመለከተው አካል በአፋጣኝ ምላሽ መስጠት አልቻለም።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኤሌክትሪክ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በአብዛኛውን ግንባታቸው ተጠናቆል እየተባለ በሰፊው ቢወራም፤ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጡ ቀርቶ በመደበኛነት እስከ ሁለት እና ሦስት ቀን ድረስ በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች መብራት እየጠፋ ነው።
ሆኖም ግን በአገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ እና መጥፋት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ለጎረቤት አገር ከፍተኛ መጠን ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ እየተከናወነ ነው።በአዲስ አበባ ከተማ ያለው የመብራት ኃይል አቅርቦት ችግር በነዋሪዎች ላይ እያስከተለ ያለው ጉዳት መጠኑ እየጨመረ ሲሆን፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማት ፣በንግድ ቤቶች ፣ አነስተኛ ምርት አምራቾች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የንፁህ ውሃ መጠጥ መጥፋት እና መቆራረጥ ከፍተኛ የሆነ ችግር እየፈጠረ ነው።

No comments:

Post a Comment