Tuesday, August 15, 2017

የአግባው ሰጠኝ ሕይወት አደጋ ውስጥ ነው



የአግባው ሰጠኝ ሕይወት አደጋ ውስጥ ነው፤
አግባው ዝዋይ ተወስዶ የደረሰበትን ድብደባ ለፍርድ ቤቱ ቤቱ ገልፆ እስር ቤቱ ለምን ይህን ድርገት እንደፈፀመ እንዲያስረዳ፣ የተፈፀመበት ድብደባ በህክምና ምርመራ እንዲ ረጋገጥለት አቤቱታ አቅርቦ የነበር ሲሆን በትናንትናው እለት መልስ ሰጥተዋል።
መልሱም በአንድ በኩል አግባው ሊያመልጥ እንደነበር የሚገልፅ ሲሆነ በሌላ በኩል ደግሞ የእርስ በእረስ ፀብ እንደነበርና አግባውም በፀቡ ተጎድቶ ሊሆን እንደሚችል በመግለፅ ለማስተባበል የሞከሩበት ነው። አግባው ነሃሴ 1 በዋለው ችሎት ልብሱን አውልቆ እንዲያሳይ ጠይቆ የተከለከለ ሲሆን ማረሚያ ቤቱ ምላሽ ከሰጠ በሁዋላ ትናንት ከማረሚያ ቤቱ ውጭ የሚገኝ የህክምና ተቋም ተመርምሮ እንዲያሳይ ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ፈቃደኛ አልሆነም።
አግባው ሰጠኝ በቂሊንጦ ቃጠሎ የተጠረጠሩ ሰዎች የታሰሩበት ዞን 5 ታሰሮ የነበር ሲሆን ከዝዋይ መልስ ይቅርታ ጠይቀው ከ ሺህ በላይ እስረኛ ከሚታሰርበት ዞን 2 አዛውረውታል። የማረሚያ ቤቱ አስተዳደሮች ይቅርታ ከጠየቁ በሁዋላ ከአቅማችን በላይ ነው ብለው ለፍርድ ቤቱ መልስ የሰጡ ሲሆን አግባው ካልቻሉ ብቻውን ወይንም እነ መቶ አለቃ ማስረሻ የታሰሩበት ዞን 4 ሊያስሩት ይችሉ እንደነበር፣ ነገር ግን ዞን 2 መቀየሩ እሱን ለማጥቃት ሊሆን እንደሚችል ስጋቱን ገልፆአል። ለህይወቱ ዋስትና እንደሌለው ገልፆአል።
ጎንደር አንድ ሰው ሲሞት እሱን መበቀል እንደሚፈልጉም ገልፆአል። ፍርድ ቤቱ በማተሚያ ቤቱ አሰራር እንደማይገባና ከዚህ በሁዋላ ምንም ሊያደርግ እንደማይችል በመግለፅ ለፍርድ ቤቱ በአግባቡ መልሰ የማይሰጡትን የማረሚያ ቤቱን አመራሮች መክሰስ እንደሚችል መፍትሄ ብሎ አቅርቦለታል።

No comments:

Post a Comment