Monday, August 7, 2017

ትግራይ ውስጥ ባሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰቀሉ ታፔላዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አዋጅ ተደነገገ

ኢሳት ዜና
ትግራይ ውስጥ ባሉ የንግድ ድርጅቶች የሚሰቀሉ ታፔላዎች በትግርኛ ቋንቋ ብቻ እንዲጻፉ አዋጅ ተደነገገ።
የትግራይ ክልላዊ መንግስት፤ ማንኛውም የንግድ ማስታወቂያ ታፔላና የግድግዳ ላይ ማስታወቂያ መልዕክቶች በትግርኛ ቋንቋ እንዲፃፉ የሚያዝ አስገዳጅ አዋጅ ሰሞኑን አፀድቆ በስራ ላይ መዋል መጀመሩን አስታወቀ። እንደ አድማስ ዘገባ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አዋጁን እንዲያስፈፅም ኃላፊነት እንደተሰጠው የቢሮው ኃላፊ ተናግረዋል። ኃላፊው አቶ ዳዊት ኃይሉ አዋጁ ማንኛውም የንግድ ድርጅትም ሆነ አገልግሎት ሰጪ ተቋም፤ የውጪ ተሰቃይ ማስታወቂያውን ወደ ትግርኛ እንዲለውጥ የሚያስገድድ መሆኑን ጠቁመው፤ አዋጁን ተግባራዊ ያላደረገ ድርጅቱ እንደሚታሸግበት አስታውቀዋል። ቀደም ሲል እንዲህ ያለ አስገዳጅ ህግ ባለመኖሩ፣ በክልሉ ከተሞች የሚሰቀሉ የግድግዳ ...ላይ ማስታወቂያዎችና ታፔላዎች የተዘበራረቀ ቋንቋ ይጠቀሙ እንደነበር አቶ ዳዊ አውስተዋል። ኃላፊው አክለውም ይህን የሚያስቀር አዋጅ መፅደቁ ለክልሉ ቋንቋዎች እድገት አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል። አዋጁ ገና በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ባይወጣም የመቀሌ ከተማ አብዛኞቹ የንግድ ቤቶችና ተቋማት አዋጁ መውጣቱን ተከትሎ ታፔላቸውን ወደ ትግርኛ ቋንቋ በመቀየር ተጠምደው ሰንብተዋል። በታፔላዎቹ ላይ ጎላ ተደርጎ ከሚቀመጠው ከትግርኛ ቀጥሎ ሌላ ማንኛውንም ቋንቋ መጠቀም እንደሚቻል አቶ ዳዊት አክለው ገልፀዋል፡፡ አማርኛ የፌዴራል ቋንቋ ፣ትግራይ የፌዴራል ስርዓቱ አንድ ክልል ብትሆንም አዲሱ አዋጅ ታፔላዎች ከትግርኛ ጎን ለጎን በአማርኛም ቢሆን እንዲጻፉ አይፈቅድም።

No comments:

Post a Comment