ፀ/ት ፂዩን ዘማርያም
ኢትዩጵያ የብር ኖቶች ለማሳተም ጨረታ አወጣች
ሴፕቴምበር 18 ቀን 2011 – እንደ ኦል አፍሪካን ዶት ኮም ዘገባ መሠረት በሴፕቴንበር 14 ቀን 2011 እኤአ (2004ዓ/ም) ዴ ላአ ሩእ፣ፋራንሰስ ቻርልስ ኦበርቱር እና ጊሰኬና ዴቨርይንት ለኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ገንዘብ ለማተም ጨረታ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡ ጨረታው መሠረት 46 ቢሊዩን ብር ዋጋ ያለው ባለ 100ብር ኖቶችና 6 ቢሊዩን ብር ዋጋ የላቸው ባለ 50 ብር ኖቶች ሲሆኑ የጨረታው አሸናፊ አዲሶቹን የብር ኖቶች በአራት ወራት ውስጥ አትሞ ማቅረብ አለበት፡፡ የብሮቹ ኖቶች አዲስ ዲዛይን ይኑራቸው አይኑራቸው አልተገለጸም፡፡
Ethiopia accepted bids to print more banknotes፡
Sep 18, 2011 09:51 AM Category: Africa
According to an article on allAfrica.com dated 14 September 2011, De La Rue, Francois-Charles Oberthur, and Giesecke & Devrient have submitted bids to the National Bank of Ethiopia for printing 46 billion birr worth of 100-birr notes and 6 billion birr worth of 50-birr notes. The winning bidder is expected to deliver the new notes within four months. No word on if the notes will be new designs.
Courtesy of Richard Miranda.
Ethiopia new date (2015) 50-birr note (B333g) and 100-birr note (B334g) confirmed:-Nov 25, 2016
09:31 AM Category:
Africa /Aug 30, 2016 08:29 AM Category:
Africa
B333g: Like B333f, but new date (2007/2015). Prefix BV.
Courtesy of Kevin Warfel.
B333g: Like B333f, but new date (2007/2015). Prefix BV.
Courtesy of Kevin Warfel.
Ethiopia seeks to print its own banknotes
The websites
allAfrica.com and
addisfortune.net report that the
National Bank of Ethiopia has issued a tender to, first, investigate if the country is capable to print its own banknotes and second, (if the answer is yes) to set up a national banknote printing facility.
“
The Bank announced a tender two weeks ago to hire an international consultancy firm to conduct a feasibility study for the printing plant on the state owned daily newspaper, The Ethiopian Herald. The main aim of planting the factory is to save the foreign currency that the country is spending to print banknotes in foreign countries. The other reason is to centralise the printing of banknotes in one place, according to a senior official from the Bank (…) Currently, NBE predominantly prints banknote in European countries, mainly in England and France. It has made an order for new banknote, as the notes that are in circulation have become worn out from use. The old notes will be collected and disposed of by burning.”
Steven Wednesday 17 December 2014 at 11:51 am |
¶ |
news |
No comments
B334g: Like B334f, but new date (2007/2015). Prefix EE.
Courtesy of Sejin Ahn.
B334g: Like B334f, but new date (2007/2015). Prefix EE.
Courtesy of Sejin Ahn.
የፈረንሳይ የገንዘብ ኖቶች ማተሚያ ካንፓኒ፤ ዴ ላአ ሩእ፣ፋራንሰስ ቻርልስ ኦበርቱር በፈረንሳይ አገር የሚገኝ የገንዘብ ኖቶች፣ ሚስጢራዊ ህትመት ሥራ ወዘተ የሚሠራ ሲሆን ከ1818 እኤአ ካንፓኒ ተመሠረተ፡፡ የካንፓኒውን የህትመት ሥራ ችሎታ ከካንፓኒው ድረ-ገፅ መረዳት ይቻላል፡፡ ካንፓኒው በሴፕቴምበር 18 ቀን 2011 እኤአ የባለ 100ና የባለ 50 ኢትዩጵያ የብር ኖቶች ለማተም በወጣው ጫረታ ተወዳድሮ ነበር፡፡
François-Charles Oberthür — Wikipédia, https://fr.wikipedia.org/wiki/François-Charles_Oberthür
François–
Charles Oberthür (1818, Strasbourg – 1893, Paris VI) est un imprimeur français et le … Autour des bâtiments
de la rue de Paris acquis en 1858, il installe ses usines de l’imprimerie Oberthur ( n
o 76 à 80) dont la construction remonte à …
የጀርመን የገንዘብ ኖቶች ማተሚያ ካንፓኒ፤ ጊሰኬና ዴቨርይንት የጀርመን ኮንፓኒ ሲሆን ዋና መሥሪያ ቤቱ ሙኒክ ይገኛል፣ ካንፓኒው የገንዘብ ኖቶች፣ ሚስጢራዊ ህትመት ሥራ፣ ስማርት ካርዶች፣የገንዘብ አያያዝ ስርዓት በመዘርጋት ወዘተ የሚሠራ ካንፓኒ ነው፡፡ ካንፓኒው በ1860 እኤአ ጀምሮ በዚህ የህትመት ሥራ ላይ የተሠማራ መሆኑን ከድረ–ገፁ መረዳት ይቻላል፡፡ ካንፓኒው በሴፕቴምበር 18 ቀን 2011 እኤአ የባለ 100ና የባለ 50 ኢትዩጵያ የብር ኖቶች ለማተም በወጣው ጫረታ ተወዳድሮ ነበር፡፡
Giesecke & Devrient (G&D) is a
German company headquartered in
Munich that provides
banknote and
securities printing,
smart cards, and cash handling systems. Old company advertisement of Giesecke & Devrient in Leipzig from the 1860s
ሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP)
Sudan Currency Printing Press (SCPP) is a private enterprise of limited liability established in May 1994 in accordance with the 1925 company law. The Company had started the real production at the end of 1994. የሱዳን የገንዘብ ማተሚያ ፕሬስ፤ኃላፊነቱ ተወሰነ የግል ኢንተርፕራይዝ በግንቦት 1994 እኤአ መጨረሻ ላይ በሃገረ ሱዳን የተመሰረተ የገንዘብ ማተሚያ የግል ፋብሪካ ነው፡፡ በምን መለኪያና መሥፈርት የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ የብር ኖቶችና ቼክ እንዲሁም
የአገር ግዛት ሚኒስትር መስሪያ ቤት (Ministry of Interior) ፓስፖርቶችና፣ከሃገር መውጫና መግቢያ ቪዛ፣ፓስፖርት ላይ የሚመታ የሚያብለጨልጭ የቪዛ ስቲከር ብሄራዊ ዶክመቶች፣ መታወቂያ ካርዶችና የተለያዩ የመታወቂያ ዶክመንቶች የህትመት ሥራ ለአዲስ ጀማሪው ካንፓኒ ተሠጠ፡፡ የሃገራችን ሉዓላዊነትና የህዝባችን ደህንነት በሱዳን የግል የገንዘብ ኖቶችና ፓስፖርት በሚያትም ካንፓኒ እግር ስር ወደቀ፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በሃገሪቱ ታሪክ ሆኖ የማያውቅ ሚስጢራዊ የህትመት ሥራ ለሱዳን የግል ካንፓኒ መስጠት ውሎ አድሮ ከሱዳን በተጣሉ ጊዜ ሀገራችን ከፍተኛ ኪሣራ ያስከትላል፡፡ ወያኔ የኢትዩጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች በሱዳን ምድር እንዳይገቡ ለማድረግ የሃገሪቱን መሬት፣ የግብርና ምርትና የቁም እንሰሳት፣ የወርቅ ማዕድን ኃብት ወዘተ በህገወጥ የድንበር ንግድ ከሱዳን መንግሥት ጋር አብሮ ይዘርፋል፡፡ የሱዳን የግል ካንፓኒ የኢትዩጵያ ብር ኖቶች፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ የማተም ሚስጢር ለምን ለህዝብ ይፋ አልሆነም፡፡ የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ፤ዋና ተግባራት ውስጥ፤ የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን ማሳተም፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ መስራት፣ የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ሃላፊነት በህዝብ ቃል የገባበት ሙያዊ ሥነ-ምግባር በንዋይ ፍቅር ተሸጦ ቢያዩ እውቁ የብሄራዊ ባንክ ገዥ ክቡር አቶ ተፈራ ደግፌ እውቁ ኢኮኖሚስት ፕሮፊሰር እሸቱ ጮሌ ምን ይሎችሁ፡፡ ሞት አይቀር፣ስም አይቀበር!!!
Enterprise to Print Ethiopian Birr, Electronic Passport, Cheque:
The Ethiopian Herald (Addis Ababa), 6 March 2016፡ By Solomon Mekonnen
The Berhanena Selam Printing Enterprise (BSPE) Friday announced plan to cooperate with Sudanese Currency Printing Press to build capabilities to print Ethiopian Birr, electronic passport and cheque locally. Speaking at a Security Printing Technical Conference, Enterprise CEO Teka Abadi said: “We believe the printing of currency, electronics passport and cheque locally will have great role in saving hard currency that our country spends. It is also necessary to localize them for economic and security reasons.” According to him, the win- win relationship with Sudan Currency Printing Press and Koenig & Bauer AG (KBA) Notasys will help each party to achieve their goals. “The printing industry is rapidly growing and the world is continuously applying new technologies from time to time. This makes the competition fierce and puts our local printing houses in a very challenging situation. We need to work together with companies engaged in security printing area,” Teka said. Sudan Currency Printing Press General Manager Assistant Omer Ahmed Mokhtar on his part said that his company is committed to transfer know how through training, maintenance and development and other areas with BSPE. The two Enterprises have signed a Memorandum of Understanding to work together in the fields of technical support, training, capacity building and in areas that could help to build institutional capacities.
Copyright © 2016 The Ethiopian Herald. Distributed by AllAfrica Global Media (allAfrica.com).
የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ የሚያትም ኢንተርፕራይዝ
ኢትጵያ ሄራልድ ጋዜጣ (አዲስ አበባ) 6 ማርች 2016 በሰሎሞን መኮንን
የብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ኢንተርፕራይዝ ከሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ፤ Sudan Currency Printing Press (SCPP) ጋር በመተባበርና ችሎታ ለማዳበር ብሎም
የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ በሃገር ውስጥ ለማተም ስምምነት ተደርጎል፡፡ የደህንነት ህትመትና የቴክኒካል ኮንፍረንስ ስብሰባ ላይ ቺፍ ኤክስኪዩቲፍ ኦፊሰር ተካ አባዲ በተናገሩት መሠረት ‹‹ የኢትዩጵያ ብር ኖቶች ማተም፣ ኤሌክትሮኒክ ፓስፖርትና ቼክ በሃገር ውስጥ ማተም ውጪ ምንዛሪ ወጪን ለማዳንና ለኢኮኖሚ እድገትና ለሃገር ሉዓላዊነት ደህንነት በጣም አስፈላጊ ምክንያት ናቸው፡፡›› ከሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ እና ኮኒግና ባወር ኤጂ ኢንተርፕራዞች ጋር ተባብሮ መስራት ዓላማችንን ለማሳካት ይጠቅማል፡፡
የሱዳን ከረንሲ ፕሪንቲንግ ፕሬስ ምክትል ጀነራል ማነጀር ኡመር አህመድ ሙክታር የህትመት ካንፓኒያቸው ከ
ብርሃነ ሰላም ማተሚያ ቤት ኢንተርፕራይዝ ጋር እውቀት ለማጋራት፣ በስልጠና ክህሎት ለማዳበር፣ ጥገናና የልማት ሥራዎች፣ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ፣ የሰው ኃይል ግንባታ ክህሎት ለማሳደግና በሌሎች የህትመት ዘርፎች አብሮ በጋራ ለመስራትና ግዳጃቸውን እንደሚወጡ በስምምነቱ ላይ ገልፀዋል፡፡
የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ የኢትዩጵያ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረቱ በሃገሪቱ ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ማለትም በግብርና፣በኢንዱስትሪና የአገልግሎት ዘርፎች ውስጥ አስፈላጊውን የኢኮኖሚ ፖሊሲ በመተግበር ለህዝብ ብልፅግናና ለኢኮኖሚ እድገት የሚሆን ፖሊሲ መንደፍ ነው፡፡ የኢኮኖሚ ፖሊሲው ስርዓት በግብርና ታክስ፣ በመንግሥት በጀት፣ በገንዘብ አቅርቦት፣ የወለድ መጠን፣ እንዲሁም የሠራተኛ /የጉልበት ገበያ፣ ብሄራዊ ኃብትና
ሌሎች ኢኮኖሚ ዘርፎች በማበልፀግ እንዲሁም የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ ከፍተኛውን ሚና እንዲጫወት በማድረግ፣ የመንግስት ጣልቃ ገብነት በተወሰኑ የኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም በማዕድን ዘርፍ (በወርቅ ፣ታንታለም፣ ፖታሽ ወዘተ) ውስጥ ብቻ እንዲወሰን ማድረግ አስፈላጊ ነበር፡፡ ሆኖም የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት በመንግሥታዊ ድርጅቶች (አየር መንገድ፣ ቴሌኮም፣ ባቡር፣ መርከብ፣ መብራት ኃይል፣ ስኮር ኮርፖሬሽን ወዘተ) በመፈልፈልና የፓርቲ የንግድ ካንፓኒዎችን (ኢፈርት፣ ሜቴክ፣ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ወዘተ) የግሉ ዘርፍ ኢኮኖሚ እንዳይሰራ በሩን ዘግተውበታል፡፡ የአንድ አገር መንግሥት የኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ዘርፈ ብዙ ፈርጆች በሁለት ሊከፈሉ ይችላሉ፤ እነሱም ፊሲካል ፖሊሲና ሞኒተሪ ፖሊሲ በመባል ይታወቃሉ፡፡
ፊሲካል ፖሊሲ፤(Fiscal Policy) የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት የግብርና ታክስ እንዲሁም የመንግሥትን ወጪ ሥርዓትን አፈፃፀም ፖሊሲን ያሳያል፡፡ የመንግሥትን ገቢና ወጪና የበጀት ጉድለትና ትርፍ ያሰላል፡፡ የመንግስትና የታክስና የግብር ገቢ አሰባሰብ ሥርዓትና ፖሊሲን እንዲሁም የመንግሥታዊ ዘርፍ ወጪን ይቆጣጠራል፡፡ የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥትና የብሄራዊ ባንክ ፊሲካል ፖሊሲ፤የግብርና ታክስ ስርዓት ፍትሃዊ ባለመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ ያስከተለውን ህዝባዊ አመፅ መመልከት ብቻ በቂ ነው፡፡
ሞኒተሪ ፖሊሲ፤(Monetary Policy) የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥትና ብሄራዊ ባንክ በሃገሪቱ ውስጥ ያለውን የገንዘብ ዝውውር፣ገንዘብ ፍላጎትና አቅርቦት በመቆጣጠር የዋጋ ግሽበት መከላከልና የወለድ መጠን በመወሰን የገንዘብ ሥርዓት የሚቆጣጠርበት ሲሆን ከዓለም ዓቀፍ ኢንስቲቲውሽን ማለትም ከዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ድርጅት፣ ከዓለም ባንክ እንዲሁም የሃገራቱን የፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና የማህበረሰብ ልማት ፖሊሲዎች ጋር አዛምዶ መስራት ያካትታል፡፡ ሞኒተሪ ፖሊሲ ከሚያካትታቸው ውስጥ፤የገቢ ፖሊስ፣የሸቀጣ ሸቀጦችና ምርት የዋጋ ቁጥጥርና የውጪ ምንዛሪ መጠባበቂያ ገንዘብ ክምችትን ያካትታል፡፡
‹‹የዓለም ባንክ የኢትዩጵያን ብር የማርከስ እሰጥ አገባና የአሥራ አንደኛው ሰዓት ንስሐ››
1 በሚለው ጥናታዊ ፁሁፉ አቶ ጌታቸው አሰፋው በሪፖርተር ጋዜጣ የብሄራዊ ባንክ ሥራና ሃላፊነትን ተንትኖ ከማስረጃ ጋር ያቀረበውን ፅሁፍ በመጥቀስ አንባቢዎች በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፡፡ ‹‹የብሔራዊ ኢኮኖሚ ፖሊሲዎች የሚያጠነጥኑት በሁለት ዓይነት የፖሊሲ መሣሪያዎች በመንግሥት ገቢና ወጪ የበጀት ፖሊሲና በጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ፖሊሲ ላይ ነው፡፡›› የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ ‹‹አስፋፊ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ (Expansionary Monetary Policy) በሕግ ገደብ (By the Rule of the Law) ካልተገደበ፣በልክ ካልተመጠነና በዘፈቀደ (By Discreation) ካደገ በአጭር ግዜ ውስጥ ምርትንም ቢያሳድግ፣በረጅም ጊዜ ግን ውጤቱ ዋጋን ማናርና ጥሬ ገንዘቡን ዋጋ በማሳጣት የብራችንን የምንዛሪ መጣኝ ማርከስ ነው፡፡›› በባንክ ሁለት ዓይነት የገንዘብ ኃብቶች አሉ እነሱም አንደኛው የውጭ ምንዛሪ ኃብት ሲሆን ሁለተኛው የአገር ውስጥ ብድር ኃብት ናቸው፡፡
የበጀት አመት________የውጭ ምንዛሪ ኃብት(1)____________የአገር ውስጥ ብድር ኃብት(2) ____ በመቶኛ(1/2×100)
2003ዓ/ም በጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 55.5 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 135.5 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 41.0%
2004ዓ/ም በጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 39.8 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 189.1 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 21.0%
2005ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 45.6 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 233.4 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 19.5%
2006ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 56.1 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 299.7 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 18.7%
2007ዓ/ምየበጀት አመት፤ የውጭ ምንዛሪ ኃብት 37.5 ቢሊዩን ብር፣ የአገር ውስጥ ብድር ኃብት 393.5 ቢሊዩን ብር፣ በመቶኛ 9.5%
‹‹ከ2003 እስከ 2007 ዓ/ም የባንክ የውጭ ምንዛሪ ሀብት ከአገር ውስጥ ብድር ሀብት ጋር ሲነፃፀር፣በ2003 ዓ/ም ከነበረበት 41 በመቶ በየዓመቱ ቀንሶ በ2007ዓ/ም ዘጠኝ ነጥብ አምስት በመቶ ብቻ ሆኖል፡፡››…
‹‹ይህ የውጭ ምንዛሪ ሃብትና የአገር ውስጥ ብድር ሀብት ንፅፅር ሁኔታ በብር የውጭ ምንዛሪ መጣኝ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የአገሪቱ ቁልል የውጭ ዕዳ ክምችትም (Outstanding Debt Stock) ይጨምራል፡፡›› ብዙ ሰዎች ስለ ጥሬ ገንዘብ ሲነገር በገበያ ውስጥ የሚዘዋወርን ጥሬ ብር ማለት ሊመስላቸው ይችላል ነገር ግን በንግድ ባንኮች ቆጣቢዎች የሚያስቀምጡት ተቀማጭ ወይም ንግድ ባንኮች በተቀማጩ ላይ ተመርኩዘው ተቀማጩን አርብተው በማበደር የሚፈጥሩት ብድርም ጥሬ ገንዘቦች ናቸው፡፡
ብሔራዊ ባንክ ለመንግሥትና ለንግድ ባንኮች የሚሰጠውን ብድር ከመቆጣጠርም በላይ፣በጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱትን የንግድ ባንኮችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር ይገባዋል፡፡ በኢትዩጵያ ለጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ያደረገው በብሔራዊ ባንክ የቀረበው በገበያ ውስጥ የሚዘዋወረው ጥሬ ብር መሆኑን በሚከተለው ቀላል አገላለጽ ማስተዋል ይቻላል፡፡
የንግድ ባንኮች ተቀማጭ
{1} 2003 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 32.6 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 112.8 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 145.4 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 32.6/112.8 X100=29.0%
{2} 2004 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 38.5 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 151.0 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 189.5 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 38.5/151.0 X100=26.0%
{3} 2005 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 45.7 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 189.6 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 235.3 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 45.7/189.6 X100=24.0%
{4} 2006 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 53.2 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 244.5 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 297.7 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 53.2/244.5 X100=22.0%
{5} 2007 ዓ/ም በጀት አመት፤ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር 60.5 ቢሊዩን ብር+ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ (ተንቀሳቃሽ፣የቁጠባና የጊዜ ተቀማጮች) 310.7 ቢሊዩን ብር = ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 371.2 ቢሊዩን ብር፡፡ የጥሬ ብርና የተቀማጭ ንፅፅር በመቶኛ 60.5/310.7 X100=20.0%
- በብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ ፖሊሲ የተዛባ በመሆኑ ምክንያት በሃገሪቱ የውጪ ምንዛሪ እጥረት ተከስቶል፡፡ ባንኩ በሃገሪቱ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት መጠን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ማድረጉን ከገላጭ ሠንጠረዡ ላይ ማስተዋል ይቻላል፡፡ በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር በ2003 ዓ/ም 32.6 ቢሊዩን ብር ሲያቀርብ፣በ2007 ዓ/ም 60.5 ቢሊዩን ብር ማለትም 54 በመቶ ሞቅ አድርጎ በገበያው ውስጥ ዘርቶታል፡፡
- በብሔራዊ ባንክ አቅራቢነት በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ጥሬ ብር አቅርቦት የምንዛሪ መጣኙን አዛብቶታል፡፡ በዓለም ታላላቅ ከተሞች እንካን ባልታየ ዓይነት በአዲስ አበባ የአንድ ካሬ ሜትር መሬት ዋጋ ሥስት መቶ ሃምሳ አምስት ሽህ ብር ደርሳል፡፡ በካንትሪ ክለብ፣ የአንድ ቪላ ቤት ዋጋ 10 ሚሊዩን ብር ደርሶል፡፡ የአንድ እንቁላል ዋጋ 3 ብር ከሰባ አምስት፣ አንድ ኪሎ ሙዝ፣ብርቱካን ዋጋ 25 ብር፣ አንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 150 እስከ 300 ብር ወዘተ በአጠቃላይ ምርት ሳያድግ ብር ማተም፣ ብር ወረቀት እየሆነ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡ ህዝቡ ለዳቦ፣ለዘይት፣ለስኳር ይሰለፋል!፣ ህዝቡ ለታክሲ፣ለባቡር፣ለነዳጅ ይሰለፋል! ህዝቡ ለስድት፣ ለሞት ይሰለፋል!!! የኢትዩጵያ ሕዝብ በአንድ ድምፅ ሁላችንንም ሁሌም ማታለል አይቻልም ይላል፡፡ በዚህም የተነሳ በሃገሪቱ ውስጥ ምን እንደተከተለ ለማወቅ ስለ ጥሬ ገንዘብ ፅንሰ-ሃሳብ እንመርምር ይለናል ጸሀፊው በመቀጠልም፡፡
{ሀ} ‹‹ጥሬ ገንዘብ የተፈጠረው የምርት ኢኮኖሚውን ለማገበያየትና ለመለካት እስከሆነ ድረስ የምርት ዋጋ አመልካች ከመሆን አልፎ የራሱ ዋጋ የለውም፡፡ የጥሬ ገንዘብ ዋጋ የሚተመነው ሊገዛ በሚችለው ምርት መጠን ነው፡፡ ስለዚህ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን ማብዛት የምርቱን ዋጋ መጣል ነው፡፡ ለዚህ ነው በብሔራዊ ኢኮኖሚ ደረጃ የውጭ ሸቀጥ ለመግዛት ከሚያስችለው የውጭ ምንዛሪ በቀር የአገር ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ለአገር ሀብትን ይለካል እንጂ ሀብት አይደለም የሚባለው፡፡››
Federal Democratic Republic of Ethiopian Passport
{ለ} ‹‹የአገር ውስጥ ምንዛሪ (
currency) ከሌላ አገር ምንዛሪ ጋር በመገበያያ ዋጋ የሚለካው በእርግጠኛ መመነዛዘሪያ መጣኝ፣ የአንድ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅሙ ከሌላ ተገበያይ አገር ምንዛሪ ሸቀጦችን በመግዛት አቅም ጋር ሲወዳደር፣ወይም ከጊዜ ወደ ጊዜ በተመናዛሪዎቹ አገሮች ውስጥ ያለውን የዋጋ ንረት ልዩነት ከግምት ባስገባ የመመነዛዘሪያ መጣኝ ነው፡፡›› በ2003 ዓ/ም አንድ የአሜሪካ ዶላር 14.06 ብር ነበር፣ 2004ዓ/ም (18.65ብር)፣ 2005ዓ/ም (18.65 ብር)፣ 2006ዓ/ም (19.65ብር)፣ 2007ዓ/ም (19.85 ብር)፣2008ዓ/ም (21.83ብር)፣በ2009ዓ/ም (23.23 ብር) የብር የመመንዘሪያ መጣኝ ከዓመት ዓመት እየረከሰ በመሄዱ ከውጭ ሸቀጣ ሸቆችና ኮፒታል ጉድስ መለትም (ማሽነሪዎች፣ መኪኖች፣ ትራንስፎርመር፣ ወዘተ) የመግዛት አቅማችን የመነመነ ለመሆን ችሎል፡፡ የሃገራችን የውጪ ንግድ ገቢ እያሽቆለቆለ በመሆዱ የታሰበው እድገት ውሃ በልቶታል፡፡
{ሐ} የብር ምንዛሪ ማርከስ(
Devaluation of currency) የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ ምርቱ ሳይኖር ጥሬ ገንዘቡን በማብዛት በሃገር ውስጥ ገበያ ገንዘብ በማሰራጨቱ የምርቱን ዋጋ መጨመር አስከተለ፡፡ የሃገሪቱም የብር የመግዛት አቅም በመውደቁ ምክንያት የሃገር ውስጥ ምርቶችን የመግዛት አቅሙ ተዳከመ፡፡ ለዚህ ሁሉ ምክንያቱ ብሔራዊ ባንክ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን ከልኩ በላይ በሃገሪቱ ገበያ ውስጥ በማሰራጨቱ ነው፡፡
ያለፉት ዓመታት የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት ዕድገት
የበጀት አመት________ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ (በቢሊዩን ብር)
____________የመጠን ልዩነት
____ እድገት
በመቶኛ
2002ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 104.0 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት — ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ –%
2003ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 145.4 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 41 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 39.0%
2004ዓ/ም በጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 189.5 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 44 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 30.0%
2005ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 235.3 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 46 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 24.0%
2006ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 297.7 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 63 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 27.0%
2007ዓ/ምየበጀት አመት፤ ጠቅላላ ለገበያ የቀረበ ጥሬ ገንዘብ 371.2 ቢሊዩን ብር፣ የመጠን ልዩነት 73 ቢሊዩን ብር፣ እድገት በመቶኛ 25.0%
2002ዓ/ም እስከ 2007ዓ/ምየበጀት አመት፤የአምስት ኣመት እድገት አማካይ እድገት በመቶኛ 29.0%
‹‹የጥሬ ገንዘብ አቅርቦቱን እድገት መጣኝ ቢመጣም በአካፋዩ መነሻ መተለቅ ምክንያት እንጂ፣የአቅርቦቱ መጠን እየጨመረ እንደመጣ እናያለን፡፡ የእርግጠኛ ጥቅል የአገር ውስጥ ምርት ዕድገትን በየአመቱ 11 በመቶ ይሁን ብለን ተቀብለን እንካ፣ ከአምስቱ አመት አማካይ የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እድገት 29 በመቶ ውስጥ 11 በመቶው ለምርት ዕድገት ዋለ ብንል ቀሪው 18 በመቶ የዋለው ለዋጋ ንረት ነው፡፡››
በ2008 ዓ/ም የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በኢትዩጵያ የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር ሲሆን በአንጻሩ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር ነው፡፡ በሌላ በኩል የመንግሥትና የግል ባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር አካባቢ ነው ያላቸው፡፡ ከህዝብ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብን ከባንኮች ተቀማጭ ካፒታል ስናቀናንሰው (670 ሲቀነስ 30 ቢሊዩን ብር) 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነው፡፡
- የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ቢሊዩን ብር
- የመንግስትና የግል ባንኮች፣ ለደንበኞች የሠጡት ብድር መጠን 480 ቢሊዩን ብር
- የግል ባንኮች፣ ባለ አክሲኖች ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር
- የመንግስትና የግል ባንኮች፣ በቁጠባ የሠበሰቡት ተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ670 ሲቀነስ ተቀማጭ ካፒታል ደግሞ ወደ 30 ቢሊዩን ብር 640 ቢሊዩን ብር ከህዝብ የተሠበሰበ ተቀማጭ ገንዘብ የህዝብ ኃብት ነው፡፡
- በ2003 ዓ/ም 680 የቅርንጫፎች ባንኮች ቁጥር የነበረ ሲሆን፣ በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይ 2800 ደርሶል፡፡ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ወደ 3900 ደርሶል፡፡ የማይክሮ ፋይናንስ ተቆማትም 1600 ቅርንጫፎች መድረስ ችለዋል፡፡ ከባንክ ቅርንጫፎች ከ3900 ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆነው የግል ባንኮች ናቸው፡፡ 18 ሽህ የነበረው የባንክ ሠራተኛ አሁን ከ20 ሽህ በላይ ሆኖል፡፡
በአጠቃላይ ሃገሪቱ ያላት ሃብት ከግዜ ወደ ግዜ እየመነመነ፣ወደ ባህር ማዶ የውጭ ምንዛሪያችን እየኮበለለ፣የገንዘባችን የመግዛት አቅም በዲቨሊዌሽን እየቀነሰ መምጣትን ያሳያል፡፡ በአዲስአበባ ለአንድ ካሬ ሜትር መሬት 355 ሽህ ብር የሊዝ መጫረቻ ዋጋ መቅረቡ አመላካች የኢኮኖሚ ውድቀት መሆኑንና የብራችን እሴት ወደ ወረቀትነት መቀየርን እንደሚያሳይ የምጣኔ ኃብት ጠበብት ይገልፃሉ፡፡ በተጨማሪም የሉዓላዊ ቦንድ የቃል ኪዳን ሰነድ አንድ ቢሊዩን ዩኤስ ዶላር ብድር በአጠቃላይ ሦስቱም የኢኮኖሚ ዘርፎች ምሦሶ መወላለቃቸውን ያሳያል፡፡
በ2009 ዓ/ም የመንግስት ባንኮች፣ የመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ስንታየሁ ወልደሚካኤል፣ የሚከታተላቸውን የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ፣ የኢትጵያ ልማት ባንክና የኢትዩጵያ መድን ድርጅት የ2009 ዓ/ም የዕቅድና አፈፃፀም
ጠቅላላ ሀብት፤በሶስቱ የመንግሥት የፋይናንስ ተቆማት የ2009 ሂሳብ ዓመት ክንውን መሠረት የ523 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት መመዝገቡን ሲገለፅ፣ ከታቀደው የ517 ቢሊዩን ብር አኮያ ከ100 በመቶ በላይ ጭማሪ መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡ በ2008 ዓ/ም ከነበረው የ440.4 ቢሊዩን ብር ጠቅላላ ሀብት አኮያ የ82.6 በመቶ ጭማሪ ተመዝግቦል፡፡ ከጠቅላላው ሀብት ውስጥ በጥሬ ገንዘብ የተመዘገበው 60 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱም ታውቆል፡፡ ከዚህ ውስጥ በብድር መልክ የተመዘገበው ሃብት 184 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በኢንቨስትመንት መልክ ከ269 ቢሊዩን ብር በላይ ነው፡፡
አጠቃላይ የዕዳ መጠን፤ በሦስቱ ተቆማት በ2009ዓ/ም ያስመዘገበት አጠቃላይ የዕዳ መጠን 490 ቢሊዩን ብር ሲሆን፣ በ2008ዓ/ም የነበራቸው የእዳ መጠን 415 ቢሊዩን ብር ነበር፡፡ በዚህም መሠረት የፋይናንስ ተቆማቱ ካፒታል መጠባበቂያ ክምችታቸውን ጨምሮ 33 ቢሊዩን ብር መመዝገቡን ኤጀንሲው አስታውቆል፡፡
በብድር ሥርጭት፤በሦስቱ ተቆማት በብድር ሥርጭት ረገድ ድርጅቶቹ 124 ቢሊዩን ብር ብድር (የብድር ቦንድ ኩፖን ታክሎበት) ማሠራጨታቸው ሲገለፅ፣አብዛኛው ድርሻ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ መሆኑ ተመልክቶል፡፡ባንኩ 94.5 ቢሊዩን ብር ብድር መሰጠቱ፣54 ቢሊዩን ብር ገደማ ብድር መሰብሰቡንና የብድር ክምችቱም በቦንድ የሰጠውን ጨምሮ 420 ቢሊዩን ብር ገደማ መድረሱ ታውቆል፡፡
የተበላሸ የብድር፤ በሦስቱ ተቆማት የተበላሸ የብድር መጠኑ ከጠቅላላው ብድር ውስጥ 2.8 በመቶ መሆኑ ሲገለፅ፣የኢትዩጵያ ብሄራዊ ባንክ ካስቀመጠው የአምስት በመቶ የተበላሹ ብድሮች ጣሪያ አኮያ ዝቅተኛ ሆኖል፡፡ ከዚህም በላይ 14.6 ቢሊዩን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን፣ ከ2008ዓ/ም መጠንም የ5.2 በመቶ ብልጫ እንዳለው ታውቆል፡፡
‹‹የኢትዩጵያ መንግሥታዊ ባንኮች የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ››
የኢትዩጵያ ብሔራዊ ባንክ ኃላፊነቱን ያልተወጣ ተቆም ነው፡፡ በሃገሪቱ ለተፈጠረው የፋይናንስ ዘርፍ ቀውስ፣ የገንዘብ አቅርቦት መመጠንና መቆጣጠር አለመቻሉ፣ የገንዘብ ወጪና ብድርን መወሰንና መጠበቅ አለመቻሉ፣ የሃገሪቱን የዓለም ዓቀፍ ተቀማጭና መጠባበቂያ ገንዘብ መቆጣጠርና ማስተዳደር ደካማነቱ፣ ለባንኮች ፍቃድ መስጠት፣መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ አቅመቢስነቱ፣ የንግድ ባንኮች ተቀማጭ መያዝ፣እንዲሁም ለንግድ ባንኮች ገንዘብ ማበደር፣ የንግድ ባንኮችን ብድር መቆጣጠርና ክትትል ማድረግ እንዲሁም የወለድ መጠንን መወሰን ጣልቃ ገብነቱ፣ እንደ መንግሥት ወኪል ሆኖ በመስራትና የውጭ ምንዛሪ ምጣኔን መወሰንና መቆጣጠር ተስኖቸዋል፡፡ የባንክ ሙያተኞች በሙስና ተዘፍቀው ከሹማምንቶቹ ጋር ተመሳጥረው የሃገር ሃብት መዝብረዋል፡፡ በሱዳን የግል ካንፓኒ፣የብር ኖቶችንና ሣንቲሞችን በማሳተም የሃገሪቱን የብር ኖቶችን እንደወረቀት በማሳተም የሃገር ሉዓላዊነትንና የህዝቡን ደህንነት ለባዕድ አገር አሳልፈው የሰጡ የብሄራዊ ባንክ ገዥዎችና የህወኃት የጦር አበጋዞች መንግሥት ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም፡፡
ብር ወረቀት፣ ወረቀት ብር፣ የብር ወረቀት፣ የወረቀት ብር (ይቀጥላል)