Wednesday, July 26, 2017

በሲያትል የኢትዮጵያዊው አሟሟት እንቆቅልሽ አልተፈታም


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |


 


አድማስ ዜና፦ ከሲያትል የተሰማው ዜና አሳዛኝ ነው። ባለፈው እሁድ፣ ጁላይ 23 ንጋት ላይ ነው፣ የ 36 ዓመቱ ይትባረክ ደሞዝ፣ ለባለቤቱ፣ “ጓደኞቼን አንድ ቦታ ማድረስ አለብኝ” ይላትና ይወጣል። በምን ምክንያት እንደሆነ አይታወቅም፣ የጠቀሳቸው ሰዎችና እሱ፣ 25 ጫማ ርዝመት ባለው የይትባረክ ጀልባ ላይ ተሳፍረው ዩኒየን በተባለ ሐይቅ ላይ ነበሩ።
በመካከል ድንገት ለፖሊስ አንድ ጥሪ ይደርሳል፣ ጥሪውም ከንጋቱ 7 ሰአት አካባቢ ሲሆን፣ በዚህ በዩኒየን ሐይቅ አካባቢ ከሚገኝ ጀልባ አካባቢ ጩኸትና ግርግር ይሰማል የሚል ነበር። ፖሊስ ከስፍራው ሲደርስ፣ በርካታ ሰዎች ጀልባው ላይ ነበሩ፣ እየተጯጯሁም ከመካከላቸው አንዱ ሐይቁ ውስጥ መግባቱንና ሳይወጣ መቅረቱን ይናገራሉ። ፖሊስም ልዩ መሳሪያ በመጠቀም ገባ የተባለውን ሰው ፣ ህይወቱ አልፎ ሊያገኘው ችሏል። ያ ሰው ይትባረክ ደሞዝ ነበር።
ይትባረክ ደሞዝ የሲያትል ከተማ የረዥም ጊዜ ነዋሪ ሲሆን፣ በትራክ ኩባንያ ለረዥም ጊዜ ሰርቷል። የሁለት ልጆች አባትም ነው። በቅርብ የሚያውቁት ሁሉ አሟሟቱ እንቆቅልሽ እንደሆነባቸው ይናገራሉ። ፖሊስ አስከሬኑን እየመረመርኩ ነው፣ የምርመራውን ውጤትም በቅርቡ አሳውቃለሁ ብሏል። ዘልሎ ገብቶ ይሁን ሆን ተብሎ፣ ወይም ሌላ ምክንያት ይኑር ከምርመራው በኋላ የሚታወቅ ይሆናል። አድማስ ሬዲዮ በቅዳሜ ፕሮግራሙ የምርመራውን ውጤት ጨምሮ የሚያውቁትንም ሰዎች በማነጋገር ተጨማሪ መረጃ ይዞ ለመቅረብ ይሞክራል።
(komo news)

No comments:

Post a Comment