Wednesday, July 19, 2017

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በመድፍ የታጀበ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ ነው | ተዋጊ ጀቶች በባህርዳር በኩል ወደ ሰሜን ሄዱ


       




(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያና ኤርትራ ድንበር በተለይም በኢሮብ ወረዳ ማጭዓ ከሚባል አከባቢ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ:: ሕወሓት መራሹ የኢትዮጵያም ሆነ የኤርትራ መንግስታት ስለተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምን ያወጡት መረጃ ባይኖርም ከሕወሓት መራሹ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል ተዋጊ ጀቶች በባህር ዳር በኩል ወደ ሰሜን ሲሄዱ እንደተመለከቱ የዓይን እማኞች ገልጸዋል::
በኢሮብ የተጀመረው የተኩስ ልውውጥ በመድፍ ጭምር የታገዘ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች የገለጹ ሲሆን ምን ያህል ሰው እንደተጎዳና መነሻው ምን እንደሆነ ለማረጋገጥ ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም::
የኤርትራ ሠራዊት ከማጭዓ ምብላዕ ሓኽለ እስከ እንዳ ማካኤል ቤተክርስቲያን ድረስ በመግባት ምሽጎችን መቆፈሩን የሚገልጹት የመረጃ ምንጮች የኤርትራ ሠራዊት ድንበር ጥሶ በመግባት ምሽግ እስከሚቆፍር ድረስ የድንበር ጠባቂዎች የት ነበሩ? የሚል ጥያቄን አስነስቷል::

ሕወሓት መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ድንበር ሠራዊቱን እያስጠጋ ሲሆን ከትናንት ማምሻውን ጀምሮ በጎንደር ዳባት አቅጣጫ ወደ ሰሜን መስመር በኦራል መኪኖች የተጫኑ ሠራዊቶች ሲሄዱ መታየታቸውን የዓይን እማኞች ገልጸውልኛል ሲል አክቲቭስት ሙሉነህ ዮሐንስ ዘግቧል::
ዜናውን ተከታትለን እንዘግባለን::

No comments:

Post a Comment