Friday, July 21, 2017

በአዲስ አበባ የሕወሓት ተቋም በሆነ የሰላም ባስ ጋራዥ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ


Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |




File Photo
(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ (ሐሙስ) በአዲስ አበባ ትላልቅ የመገበያያ ሥፍራዎች አካባቢ የሥራ ማቆም አድማ ሲደረግ ከዋለ በኋላ ማምሻውን የሰላም ባስ ንብረት የሆነው የአውቶቡስ ጋራዥ ውስጥ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙን ምንጮች አስታወቁ::
በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች በሚደረጉ ተቃውሞዎች ላይ ሲሰበርና ሲቃጠል የቆየው የሕወሓት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ዛሬ ምሽት ላይ የአዲስ አበባው ጋራዥ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቃት ደርሶበታል::

የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ ሰላም ባስ ጋራዥ ውስጥ 3 ጊዜ የቦምብ ፍንዳታ ተሰምቷል:: ከዚያም በኋላ የተኩስ ልውውጦች እንደነበሩ ታውቋል::
ይህን የቦምብ ፍንዳታ ማን እንዳደረሰው ኃለፊነቱን የወሰደ አካል ባይኖርም ሰላም ባስ ጋራዥ አካባቢ ማምሻውን የሕወሓት መንግስት ወታደሮች መስፈራቸውና በአካባቢው ፍተሻዎች እየተደረጉ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ሰላም ባስ በትግራይ ልማት ማህበር አካማኝነት በ1996 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን የትግራይ ልማት ማህበር በትግራይ ሕዝብ ገንዘብ ይሰበስባል እንጂ ለደሃው ሕዝብ ያደረገው ነገር የለም እየተባለ በትግራይ አክቲቭስቶች ዘንድ በስፋት ይተቻል::
ሰላም ባስ በአዲስ አበባ፣ ድሬደዋ፣ ሐረር፣ ጅጅጋ፣ ጅማ፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ መቀሌ፣ ሽሬ፣ አሶሳ፣ አርባምንጭና ሞያሌ ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል::

No comments:

Post a Comment