Thursday, July 13, 2017

ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሐገራቸዉ ከመመለስ ይልቅ «የመጣዉን ለመጋፈጥ» እንዲወስኑ ያስገደዳቸዉ የመጓጓዣ ዋጋ ብቻ አይደለም



ከሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያዉያን

 ከተመለሱት የሚያገኙት መረጃ ከሁለቱ መጥፎ፤ «የተሻለ» የሚሉትን  መጥፎ እንዲመርጡ ሳያስገድዳቸዉ አልቀረም።በዚሕ መሐል ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መጠቃት፤ አንዳዶቹ መደፈር፤ ሐብት ንብረታቸዉ መዘረፉንም ተናግረዋል።
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ከሐገሩ እንዲወጡ የደነገባበቸዉ ኢትዮጵያዉን አሁንም ወደ ሐገራቸዉ ለመመለስ እያቅማሙ መሆኑ ተነገረ። ጉዳዩን የሚከታተሉ ጋዜጠኛና የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ መሪዎች እንደሚሉት «ሕገ-ወጥ» የተባሉት ኢትዮጵያዉያን ወደ ሐገራቸዉ እንዲመለሱ የተሰጣቸዉ ተጨማሪ ቀነ-ገደብ ቢጋመስም አብዛኞቹ የመመለስ ፍላጎት ያላቸዉ አይመስሉም። ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉን ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ዜጎች መጠቃት፤ መደፈርና መዘረፋቸዉን ይናገራሉ። ነጋሽ መሐመድ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
አንዳንድ ዘገቦች እንደሚጠቁሙት ሳዑዲ አረቢያ ዉስጥ ያለ ሕጋዊ መኖሪያ ፈቃድ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ እስከ አራት መቶ ሺሕ ይደርሳል።
Saudi Arabien Äthiopien Rückkehrer (DW/S. Shiberu)
የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ኢትዮጵያዉያኑን ጨምሮ «ሕገ-ወጥ» የሚላቸዉ የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ በሰጠዉ የሰወስት ወር የጊዜ ገደብ ሐገሩ የገባዉ ኢትዮጵያዊ ቁጥር ግን መቶ ሺሕ እንኳን አይሞላም።
የመመለሻዉ ጊዜ ባንድ ወር ሲራዘም ደግሞ፤ ጂዳ የሚኖረዉ ጋዜጠኛ ነቢዩ ሲራክ እንደሚለዉö የሚመለስ ሰዉ ጠፋ። ከብዙዎቹ ምክንያቶች አንዱ መመለስ የፈለገዉ ኢትዮጵያዊ መንገላታቱ ነዉ። ሁለተኛዉ የአዉሮፕላን ትኬት ዋጋ መናር።
በሪያድ የኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ሊቀመንበር አቶ ሻዉል ጌታሁን «እንግልት» መባሉን አይቀበሉትም። የቲኬቱን ዋጋ መናር ግን አላስተባበሉም።
ኢትዮጵያዉያኑ ወደ ሐገራቸዉ ከመመለስ ይልቅ «የመጣዉን ለመጋፈጥ» እንዲወስኑ ያስገደዳቸዉ የመጓጓዣ ዋጋ ብቻ አይደለም። ከተመለሱት የሚያገኙት መረጃ ከሁለቱ መጥፎ፤ «የተሻለ» የሚሉትን
Saudi-Arabien Abschiebung illegaler äthiopischer Arbeitsmigranten (DW/S. Shibru)
መጥፎ እንዲመርጡ ሳያስገድዳቸዉ አልቀረም።በዚሕ መሐል ሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን መጠቃት፤ አንዳዶቹ መደፈር፤ ሐብት ንብረታቸዉ መዘረፉንም ተናግረዋል። የሪያዱ የኢትዮጵያዉያን ማሕበረሰብ መሪ አቶ ሻዉል ጌታሁን አቤቱታዉ ደርሷቸዋል።
ጋዜጠኛ ነብዩም መረጃ አለዉ።በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፤ በጂዳ የኢትዮጵያ ቆስላ፤ አዲስ አበባ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ባለሥልጣናትን ለማነጋገር ዛሬ ቀኑን ሙሉ ደዉለን ነበር። ካንድ ሰዉ በስተቀር ሥልኩን የመለሰ አንኳን አልነበረም። የመለሱት «ስብሰባ ላይነኝ አሉ» በቃ።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ

No comments:

Post a Comment