Saturday, July 22, 2017

የኤፈርት የነግድ እና እንድስትሪ ድርጅቶች ለመቀሌና ወልዋሎ እግር ኳስ ክለቦች በገንዘብ መደገፋቸው ለምን ኣላማ ነው ??

 

  
By ሳተናውJuly 21, 2017 22:27
  

ከኣስገደ  ገብረስላሴ ፡
መጀመርያ በህዝብ  ነጻ  ተሳትፎ እነዚ  ክለቦች የእግር  ኳስ  ስፖርት   40  ኣመት   በላይ   ነበረ እየተባለ     በትግራይ  ጠቅላይ  ግዛት     እንደታሪክ  ሲነገርለት  የነበረ   ሂወት ሊፈጥር  እና  የኳስ እስፖርት   በትግራይ  ትንሳኤ  ሙውታን ኣድርገው እንዲንሰራራ  ማድረጋቸው   ለእስፓርቶኞችም  ፣ለእስፓርት ኣፍቃሪ  ህዝብም   እንኳን ደስ ኣለን ።  እነዚህ ክለቦች ካሁን በፊት የነበሩ  ትራንስ ኢትዮጱያ  እና  ጉና
የስፖርት ክለቦች   የህወሓት ፓለቲካ ጣልቃ መግባት ( ኣባታውነት ) ይዞዋቸው የወደቀው  ጥገኝነት  ሰብረው  የህዝብ  ተሳትፎ እንደማእበል  የተሳተፈበት  ሞራል ሰንቀው  የፖለቲካ ጥገኝነት  እና  ኣባታውነት  ወደ ጎን  በመተው   ነጻነታቸውን ይዘው  ለድል  መጎናጸፋቸው  ሌላ ተጨማሪ ድል ነው ።ኣሁንም እንኳን  ለስፖርቶኞችና ለእስፖርት  ኣፍቃሪ  ማህበረሰብ  እንካን ደስ  ኣለን ።
ሌላው ድል   ደግሞ   እነዚህ  ክለቦች በሃገር ደረጃ   ተወዳዳሪ  ሆነው  መቅረባቸውና ለወደፊትም  ከውስጣቸው  ሃገራችን   በእግር ኳስ እድትታወቅ ሊያደርጉ  የሚችሉ  እስፖርቶኞች የሚመልሉባቸው  ክለቦች   ለመሆን  የሚያስችል  እና  እንደ ቡዱንም በኣፍሪካና  በኣለም መድረኮች  የሚሳተፉበትም  ብሩህ  ተስፋ ኣሳይተዋል ።  ይህ  ሁሉ ድል  ታቅቦና  እንደ  እሴት ሆኖ  ሊዘልቅ ከሆነ  ለፓለቲኮኞች ጣልቃ ለመግባት ቀዳዳ ሳይፈጥር   የህዝብ የድጋፍ  ማእበሉ  ሳይለየው የሙቆቱ ዲግሪ ወደ ላይ እየገፋ ስሄድ ብቻ  ነው ።  ይህ ደግሞ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች  ወጣቱ ፣ ሙሁሩ ፣ተማሪው ፣ ነጋዴዎች ፣ ባለሃብቶች ፣   የመንግስት  ሰራተኞች ወዘተ በመሉ  ከተሳተፉበት ፣1ኛ ክለቦቹ  ነጻነታቸው ጠብቀው ጥገኝነት ኣስወግደው በህዝብ በመተማመን ማንም  ሳጎበድድባቸው ይኖራሉ 2ኛ ትግራይ የእግር ኳስ እስፖርቶኞች  መፈልፈያ  ትሆን ኣለች ።
የቢሌኖሩ የኤፈርት የንግድና  የእንድስትሪ  ድርጅቶች   ኣሁን  ለመቀሌ   እና  ለወልዋሎ የእግር ኳስ  ስፖርቶኞች  የመበራቻቻ ሽልማትስ  ምን ግምት  ላይ  ያስገባ ነው   ??  የስፖርት ክለቦች በቅንነት ለመበረታታት ? ወይ የህዝብ ማእበሉ  ድንገት ስለኣገረሸበት  ወደ ፖለቲካ እንዳይ ቀዬር  ታሳቢ በማድረግ ?   ነውን ? ምክንያቱም  በጋ ሙሉ የነበረው  የኢኮናሚ  ውጣውረድ ጰ ሲያጋጥም  የት ከረሙ ?
በእኔ እምነት  እና ህወሓት  እንደማውቀው  ከበጎ  ኣቅጣጫ ተነስቶ  ያደረገው ኣይመስለኝም ። በስተጀርባ  ፖለቲካ  ተልእኮ  እንዳለው ነው የሚገባኝ ።
ምክንያቱም  የህወሓት ኣማራር  ይዞት የመጣ እና  እነኣባይ ጸሃዬ ፣   መለስ  ዜናዊ  ኣለምሰገድ ገብረኣምላክ  ሌሎችም በየፖለቲካዊ ፣ተምህርት ቤቱ እያስተማሩበትና እየሰሩበት  የመጡ ። ይላሉ ፣
የሆነ  የሃይማኖት ፣ የማህበራት ፣ የስፖርት  ቡዱኖች  የሙያ  ማህበራት እንደ  የመማሃራን ፣የተማሪዎች ፣ የሰራተኛ  ማህበራት   ወ  ዘ ተ  ቡዙ ህዝብ  የሚሰበሰቡበት  ተቃም  በቀጥታ  ይሁን  በተዘዋዋሪ   የራስህ  ሰዎች  ገብተው  መምራት  ኣለባቸው   ይሉ ነበር ።  ይህ የኣማራር  ኣቅጣጫ  በኣላማቸውና በተግባራቸው   ተነስተው በህዝብ  ላይ ኣመኔታ  የለላቸው  ኣፋኝ  ስርኣቶች  የሚሰሩ ሴራ ነው ።
ለዚሁ ሃቅ  የህወሓት  መሪዎች  ታግለን ስልጣን  ካወጣናቸው  ወደዚህ  26 ኣመት  ሙሉ  የተከተሉትም  በበረሃ ሲነጉሩን የቆዩ  ኣሰራር  ነው ።  ይህም በክልልና በሃገር  ደረጃ  ንግድ  ምክርቤት ፣የመማህራን  ማህበር ፣  የሙያ እና ሰራተኛ ማህበር ፣ የሴቶች ማህበር ፣ የወጣት ማህበር ፣ የተማሪዎች ማህበር ፣ ሌላ ቀርቶ  ከኣንደኛ ደረጃ እስከ ዩንቨርሲቲ ያሉ ዳሪክቶሮች ፕረዝዳንቶች    ወጣቱ  በህወሓት  ተቀፍድዶ እንዲያዝ  በኣማራር የሚያስቀሙጣቸው  የተማሪዎች እና የኣስተማሪዎች  ነጻ እንቅስቃሴ ቀፍደው  ይዘው  መፋናፈኛ የሚያሳጡዋቸው ሰዎች ነው የሚያስቀምጡት ።
በሌላ በኩል ይህ  መንግስት ከመጣ   ጀምሮም የኢትዮጱያ   የሃገራችን ስፓርትና ኣትለቲክ ፈደረሽኖች  እየተመራ   የመጣ   በካድሬዎች  ነው   በትግራይ የቆዬ  ኣሰራር  ብንመለከትም  የስፖርት
ክለቦች ይሁኑ ፈደረሽኑ በካድሬዎች እየተመራ  ነው የመጣ        የነበሩ  ነጻ  የኳስ ክለብ ቡዱኖችም  በውስጣቸው  የነበሩ ቡቁ ተጫዋቾች በገንዘብ እየደለሉ ወደ ትራንስና ጉና ክለቦች እየሳቡ   በዋናነት  ቢሌኖሩ  ትእምት በትግራይ ነጻ  የእስፖርት ክለቦች   እንዳይበቅሉ  መጦፎ ሚና ተጫውተዋል ። ሲደጉማሟቸው  የነበሩ ክለቦችም  ህዝባዊ  መሰረት  ያለው የህዝብ  ማእበል    ስሌላቸው ወድቀው ቀሩ ። እነዚህ  ሰዎች በሃገር  ደረጃ   ለክለቦች የቤትና የዳር  ልጆች በማድረግ   ስብሃት ነጋና  ጀነራል ሳሞራ  የኑስ  የበላይ ጠባቂዎች በመሆን    የሚሞሩት  ደደቢት  የስፖርት  ክለብ   በመፍጠር  በሃገራችን  የስፖርት ክሎቦች ኣዲስ መደብ  ፈጥረዋል ።
ባለፈው  ሁለት ኣመት  የነበሩ  የእግሪ   ኳስ ክለቦችም  ሆን  ተብሎ  ለዘረኝነት  መቀስቀሻ  ነው  የተጠቀሙበት   ። ለዚሁም  የትግራይና  የኣማራ ክል ክለቦች   የተፈጠረው  የዘር ግጭት ሆን ተብሎ በህወሓትና  በባኣዴን መሪዎች  ለዘረኝነት  ግጭት  ፍላጎታቸው  ለማርካት በመሳሪያነት ወይ ግጭቱ  ወደ ስለታም ጫፍ ሊደርስ   ተጠቅመውበታል  ።
ኣሁንም  የህወሓት  መሪዎች   የግሊ ኪስ  የሆነው ቢልየኖሩ  ትእምት  በሱር ኮንስትራክሽንና  በመስፍን  እንጅነር  ኣድርጎ   ለመቀሌና  ለወልዋሎ  የእግር  ኳስ  ክለቦች   ያደረገው  ስጦታ ፣በኣንድ በኩል  ለገዜው  የስፖርቶኞች   የተወሰነ  ችግር  የሚቀርፍ ቢሆንም  በረጅም  ኣላማ  ሲታይ  ግን ፣
1ኛ   ስ ጦታው ህወሓት  በክልሉ  ለሚኖር  የስፖርት  እድገት  የሚደግፍና  ለእስፖርቱ  ፍቅር ያለው መስሎ ለመታየት ቢሞክርም ፣ በዘንድሮ  የሁለቱ ቡዱኖች  የህዝብ  ማእበላዊ  ድጋፍ  በማግኘታቸው    በውስጡ ያለው ህብረት እና በጨወታ ጊዜ በኳስ ሜዳ  ኣዳራሾች  የሚሰሙ  የህዝብ  የዲሞክራሲያዊ  ፍላጎት  የሚያንጻባርቁ   ማጉረምረም  እጅጉን  የበረታ በሞኖሩ  በዚሁ ጨዋታ ቡዙ ሙሁር  ተማሪ የከተማው ወጣት ፣ነጋዴው ፣ የመንግስት  ሰራተኛ  ወታደሮች የተሰባሰቡበት  ሰለነበረ  ፣እዛ የሚነሱ ቃላቶች ለተሰበሰበው  ማህበረሰብ  በሙሉ  ተጽእኖ   እንዲያሳርፍ በማድረጉ  ። በዛ የነበሩ ሽኩሽኩቻ    ለህወሓት  መሪዎች  ትልቅ  ስጋት  የሚፈጥር በመሆኑ ፣ራስ ምታት  ስለሆነባቸው  ከማያልቀው  የቢሌኖሩ ኤፈርት  ትንሽ ገንዘብ  ወጭ    እርጥባን በማድረግ   የማእበሉ ኣቅጣጫ  የሆነ  ድለላ ኣድርገው  መቀልበሱ  የግድ  ስለሆነባቸው  ያወጡት  ስጦታ ነው ። እንጅ የህወሓት መሪዎች  ለትግራይ  ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ  ድጋፍ  ሊያደርጉ  የህዝብ  ፍቅር  ቢኖራቸው  ንሮ በህዝብ  ስም  የሚነግዱበት የትግራይ   ህዝብ  3 (4)  ቢሊዮን  ብር    ከዛ በላይ ቢሌን ወጭ ኣድርገው  በየጎደናው  ያለው  ኣካል ጉዳተኛ ፣ የሰደት ተፈናቃዮች ፣ ስራ ኣጥ  ሙሁራን እና ወጣቶች ስራ በፈጠሩ ነበር ።
በመሆነም  የኣሁን ለክለቦች የተደረገው  ለክሎቦች  የገንዘብ  ስጦታ  ሆንተቡሎ  የእስፖርት  ማህበረሰብ  ለመቆጣጠርና  በትግራይ  ያሉ የእስፖርት ክለቦች  ለመከፋፈል  የተደረ  ሴራ  ነው ።
እነዚህ ሰዎች  ሃቀኛና  ቅንነት ያለው  ስራ ለመስራት ከተፈለገ  ለግለ  ተጫዋቾች  በግላቸው  ከመስጠት  ለምን በክሎቦች  ኣማራር ኣድርጎ  ለተጫዋቾ  በእጃቸው እንዲደርስ  ኣይደረግም??
ስለዚህ ለክሎቦች  የገንዘብ  ስጠታው መደረጉ  ልዩ ነገር  ሆኖ  ሳይሆን   መስጠቱ ግዴታቸው  እና  ጥሩ  ነገር   ሆኖ ። ስጦታው  በስተጀርባው  ክለቦቹ  የህወሓት  ፓርቲ  ጥገኛ  እንዳይሆን እጠረጥራለሁ ።
የፖለቲካ ተጽእኖ  የሌላቸው ክለቦች ያቡቡ!!!!!
ውድቀት  ለኣባታውያን እና ኣዳናጋሪዎች !!!
ከኣስገደ  ገብረስላሴ ፡
7  / 21 / 2009

No comments:

Post a Comment