Friday, July 14, 2017

መለስ ዜናዊ እና ገዱ ምንድን ነዉ ልዩነታቸዉ? ጸረ አማራዉ ገዱን የአማራ መሪ ነዉ ብሎ የሚቀበል ስነልቦና ያለዉ ተቃዋሚ ሊሆን እንዴት ይችላል?



ሸንቁጥ አየለ
ሰሞኑንም ገዱ ከስልጣን ሊነሳ ነዉ የሚባል ዜና ይሁን ምን በገዱ አፍቃሪዎች እየተነዛ ነዉ::የሚያሳፍረዉ ደግሞ የገዱ ከስልጣን መነሳት የአማራን ህዝብ ጥቅም ይነካል የሚል አሳፋሪ መልዕክት ማሰራጨታቸዉ ነዉ:: እነ ገዱን ልክ የተቃዉሞዉ ጎራዎች በማድረግ እና የህዝብ መብት ተቆርቋሪዎች በማስመሰል የሚቀርበዉ ትንተና አላማዉ ግልጽ ነዉ::ህዝብ ማጃጃል ብሎም ከተቻለም ትግሉን ወደ እነ ገዱ በመቀንበብ እነገዱ የትግሉን ክር እንዲጨብጡት ማድረግ ነዉ::


ለመሆኑ ይሄ ገዱ የሚባል የአማራ ህዝብ ጠላት ስንት ጊዜ ነዉ ከቦታዉ የሚነሳዉ ጃል?
ለመሆኑ ከገዱ የተሻለ የወያኔ አሽከር የሚሆን ሰዉ ወያኔ በመላዉ አማራ ህዝብ ዉስጥ ፈልጎ ያገኝ ይሆን ወይ?
በአንድ አመት ዉስጥ እንኳን አሁን ገዱን ከስልጣን ሊያነሱት ነዉ ሲባል እኮ አስረኛ ጊዜ ነዉ::ገዱ መጀመሪያም: አሁንም ወደፊትም የአማራ ህዝብ ጠላት ነዉ::
እናም ገዱ የሚባለዉ ሙት የብአዴኖች ራስ ወያኔ እስካለ ድረስ ለዉለታዉ ሁል ጊዜም ስልጣን ያገኛል::የአማራን ህዝብ እንዲያስገድል የክልሉ ዋና : ወይም ሌላ ስልጣን ይኖረዋል::ይሄ ሰዉ መደቡ እና አገልጋይነቱ ከጠላት ወያኔ ጫማ ስር መሆኑን የሚዘነጋ ጤናማ ኢትዮጵያዊ በተለይም ጤናማ አማራ አንድም የለም:: በወያኔዎች አይን የወያኔዎችን የተንጋደደ ጫማ ያህል ዋጋ ያለዉ ሰዉ ቢሆንም መደቡ ግን ያዉ የወያኔ አሽከር ብሎም የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነዉ::
የወያኔ መሳሪያ በመሆን አማራዉን ያስገደለ : እንዲፈናቀል የተስማማ: አማራ መጤ ነዉ ሲባል አብሮ ያጨበጨበ: የኢትዮጵያ ብሄሮችን አማራ በቅኝ ገዥነት ይዟቸዉ ነበር ብሎ ህዉሃት ሲሰብክ የተስማማ ሁሉ የአማራ ህዝብ ጠላት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ነዉ::
ገዱ ደግሞ ይሄን ሁሉ አድርጓል:: አማራን የሚያህል ህዝብ ግንባር በምታክል ክልል ላይ ተወስኖ እንዲኖር: ከመላ ኢትዮጵያ እንዲፈናቀል ያደረገ ገዱ እንጂ ሌላ ማን ነዉ? አማራ በመላ ሀገሪቱ መጤ ሲባል እና ከአባቶቹ ሀገር ላይ እንዳይኖር ሲፈረድበት የተስማማ ገዱ የሚባል ጸረ አማራ እንጅ ሌላ ማን ነዉ? ገዱ በአማራ ህዝብ ላይ የሰራዉን የጠላትነት ስራ ወያኔ: ሻዕቢያ እና ኦነግ በጋራ የሰሩትን ያክላል:: ከተገለጹት የአማራ ህዝብ ጠላቶች በላይም የአማራ ህዝብ ጠላቶች አማራን አማራ መስለዉ የሚያስጠቁት ናቸዉ::
ጸረ አማራዉ ገዱን የአማራ መሪ ነዉ ብሎ የሚቀበል ስነልቦና ያለዉ ተቃዋሚ ሊሆን እንዴት ይችላል?
ከዚሁ ከገዱ ከስልጣን መነሳት ጋር በማስታከክ አቶ አያሌዉ ጎበዜ የሚባለዉን ጸረ ህዝብም አብሮ የማሞገስ አጀንዳ ተያይዞ መራገብ ጀምሯል:: ገዱ እና አያሌዉ ጎበዜ የሚባሉ ጸረ ህዝቦችን ከብአዴን የሙታን ስብስብ ዉስጥ መዞ በማዉጣት እነሱ ልዩናቸዉ ማለት ምን ማለት ነዉ? እነሱ ለክልሉ ብዙ ሰርተዋል ማለት ምን ማለት ነዉ? አማራ ክልልን በደንብ ጠንቅቀን ለምናዉቅ ሰዎች ገዱ እና አያሌዉ ጎበዜ በክልሉ ስራ ሰርተዋል ብሎ የሚያወራ ሰዉ በጣም ያናድደናል ብቻ ሳይሆን መራራ ስሜትን በዉስጣችን ያጭርብናል::
አማራ ክልል ላይ ምንም የተሰራ ስራ የለም::ሰዉ ከመግደል እና ከማሳረድ በቀር::ገዱ ልዩ : አያሌዉ ጎበዜ ልዩ የህዝብ ወገን ናቸዉ ብሎ መናገር ምን የሚሉት ህዝብ የማሞኘት ስልት ነዉ::
ሌላዉ ቀርቶ አማራ ክልል ላይ የተራቡ ሰዎች እንኳን እርዳታ አግኝተዉ በልትዉ ነብሳቸዉ እንዳይተርፍ ቀጥተኛ መመሪያ የሚሰጠዉ ልዩ ሰዉ የተባሉት ገዱ እና አያሌዉ ጎበዜ ናቸዉ::ሲጀምር የባንዳ ልዩ የለዉም::ሁሉም ባንዶች ስነልቦናቸዉ አንድ ነዉ::ወያኔን ሊያገለግል የገባ: የኢትዮጵያ ታሪክ መቶ አመት ነዉ ሲባል የተስማማ: አማራ ወራሪ ነዉ ሌላዉን ኢትዮጵያዊ ቅኝ ገዝቷል ሲባል የተስማማ: የኢትዮጵያን ህዝብ በጎሳ ለማባላት አብሮ ከወያኔ ጋር የሮጠ ሁሉ ጸረ ህዝብ ነዉ::
ምንም የተለዬ ነገር የለዉም:: በወያኔ የደም መርዝ አብሮ ጭብጦዉን አብኩቶ በስልጣን ወንበር ላይ ፊጥ ብሎ በዉስኪ እየተራጨ ህዝብን በርሃብ: በስደት: በልዩነት: በጥላቻ: በፍትህ እጦት የገደለ እና ያስገደለ ሁሉ ባንዳ ነዉ::ጸረ ህዝብ ነዉ:: ገዱ የለ: አያሌዉ ጎበዜ የለ እንቶኔ የለ::ሁሉም አንድ ነዉ::እነዚህ ናቸዉ አይደለም ኤርትራን ቆርሰዉ የሸጡት? እነዚህ ናቸዉ አይደለም ኢትዮጵያዉያንን እርስ በርስ የሚያባሉት? እነዚህ ናቸዉ አይደለም አማራ ህዝብ ጫንቃ ላይ ተቀምጠዉ የዘር ማጥፋት የሚፈጽሙበት? እነዚህ ናቸዉ አይደል የቀደሙ ኢትዮጵያዉያን አባቶቻችን የሰሩትን ሁሉ የናዱት?
እነዚህ ናቸዉ አይደለም እንዴ በመላዉ ኢትዮጵያ የሰበአዊነት ረገጣ ሲደረግ እና ህዝብ ሲታረድ እየወጡ ህዝብ አልተገፋም እያሉ መግለጫ የሚሰጡይት? እነዚህ ጠላት ካልተባሉ ማን ሊባል ነዉ? ታዲያ አማራ ህዝብ ላይ ጣሊያን መጥቶ የዘር ማጥፋት አልፈጸመበት::ወይም ወያኔ አማራን ብቻዉን አለ ብአዴን ሙታን ሰዎች ድጋፍ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ አላደርገዉ:: እኮ ታዲያ ወያኔ እና ብአዴን ምንድን ነዉ ልዩነታቸዉ? አንዱ በትግሬ ስም መነገዱ ሌላዉ በአማራ ስም መነገዱ መሆኑ ነዉ ልዩነታቸዉ? መለስ ዜናዊ እና ገዱ ምንድን ነዉ ልዩነታቸዉ? እነዚህ ሁሉ ጸረ ህዝብ ናቸዉ:: ጸረ ኢትዮጵያዉያን: ጸረ አማራ በአጠቃላይ ጸረ የሰዉ ልጅ::
ወያኔ በትግሬ ስም ብአዴን የሚባለዉ ሙት ደግሞ በአማራ ስም መነገዳቸዉ ወይም ተደራጀን ማለታቸዉ ምንም ልዩነት የለዉም::ቁም ነገሩ ከሚሰሩት ስራ ላይ ነዉ:: አንድ ቡድን ወይም አንድ አካል ምን ይሰራል ? ወይም ምን ሰራ ነዉ ጥያቄዉ? እዉነትና ፍትህን ያራምዳል ወይስ ሀሰት: ሸፍጥ: ተንኮል: እና ጥላቻን ይፈጽማል?ግፍን: ኢሰበአዊነትን እና ኢዲሞክራሲያዊነትን ይሰራል ወይስ ሲሰራ ይተባበራል ነዉ ጥያቄዉ:: የስራም የተባበረም ያዉ ነዉ::ግፈኛ እና ጸረ ህዝብ ነዉ::
መለስ ዜናዊ ኢትዮጵያ ትዉደም የሚል መጽሀፍ ሲጽፍ: ወይም አማራ ይታረድ የሚል መመሪያ ሲያስተላለፍ በዋናነት አንጋች እና ጎታች ሆነዉ ፈጻሚ እና አስፈጻሚ ሆነዉ የሚሰለፉት እነ አያሌዉ ጎበዜ እና እነ ገዱ ብሎም እነሱ የሚመሩት ብአዴን የሚባለዉ ስብስብ ከመለስ ዜናዊ በምን ይለያሉ? በምንም አይለዩም:: በህዝብ ላይ መቀለድ ይቁም::ገዱም : መለስም አንድ ናቸዉ::ጸረ ህዝብ ነዉ ካምፓቸዉ::ጸረ ህዝብ ነዉ ጎራቸዉ::የጸረ ህዝብ ልዩ የለዉም::ምድቡ እዚያዉ ጸረ ህዝብ ነዉ::

No comments:

Post a Comment