

(ዘ-ሐበሻ) ከባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጀምሮ በተለያዩ ከተሞች እየተደረገ ያለው የሥራ ማቆም አድማ አዲስ አበባ ደረሰ:: ዛሬ በአዲስ አበባ በኮልፌ እፎይታ ፣ አጠና ተራና ሳሊተ ማርያም አካባቢ ሙሉ በሙሉ የንግድ ሱቆች ተዘግተው ውለዋል::
ሕወሓት የሚመራው መንግስት በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነውን አግባብ ያልሆነ ግብር በመቃወም ሕዝቡ በተለያዩ አካባቢዎች እንቅስቃሰዎችን እያደረገ ነው::
እንደምንጮቻችን ገለጻ ሳሊተ ማርያም አካባቢም እንዲሁ ሱቆች ተዘጋግተው የሥራ ማቆም አድማ ተደርጓል::
በአዲስ አበባ ሳሊተ ማሪያም ቤተክርስቲያን አካባቢ ያሉ ሱቆች በመዘጋት ላይ ናቸው:: አካባቢውን ፌደራል ፓሊስ ወሮታል:
የሕወሓት መንግስት ተላላኪዎች ነጋዴዎች ሱቆቻቸውን እንዲከፍቱ የሚያስገድዱ መ ል እክቶችን ቢያስተላልፉም ነጋዴዎች እምቢታን መርጠዋል::
No comments:
Post a Comment