ሼክ መሐመድ አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረከት ስምዖን ጀርባ ሰርተውታል ተብሎ የሚጠረጠሩበት የሙስና ወንጀሎች
ሼህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ በሙስና ተጠርጥረው መታሰራቸው እየተነገረ ነው:: የተለያዩ የአረብኛ ሚዲያዎችን ጨምሮ ኒው ዮርክ ታይምስና ሬውተርስ የአላሙዲንን የመታሰር ዘገባው አውጥተዋል:: በኛ በኩል ዜናውን ለማጣታራት እየሞከርንነው::
በአረቢኛ ቋንቋ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ በወጣው ዘገባ መሰረት አል አሙዲንን ጨምሮ በርካታ ሰዎች በሳኡዲ መንግስት በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል። ከአላሙዲን በተጨማሪም የኦሳማ ቢላደን ወንድምም እንደታሰረ ተዘግቧል::
ሳዑዲ በሙስና ዘብጥያ ካወረደቻቸው መካከል 11 ልኡላን እና ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም ቢሊየነር ነጋዴዎች ከታሳሪዎቹ ውስጥ ተካተዋል። ከታሳሪዎች መካከል የሚከተሉት ስም ዝርዝሮች በኒውዮርክ ታይምስ እና ሬውተርስ ዘገባ ላይ ተጠቅሰዋል::
ልኡል አልዋሌድ ቢን አብዱላህ
ልኡል አልዋሌድ ቢን ታላል
ልኡል ሚተብ ቢን አብዱላህ
ልኡል ቱርኪ ቢን አብዱላህ
ካሊድ አል ትዋይጂሪ
አደል ፋኬህ
ኢብራሂም አል አሳፍ
አብዱላህ አል ሱልጣን
ባክር ቢን ላደን
መሀመድ አል ቶባሺ
አምር አል ዳባግ
መሀመድ አል አሙዲ
በፎቶግራፍ ወጥተው መታሰራቸው ተገልጿል::
አላሙዲ በኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መሸጥ ከጀመረበት ከ1997 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ከሸጣቸው 370 ድርጅቶች መካከል ሼህ አልአሙዲወደ 30 የሚጠጉትንና እጅግ አትራፊ የሆኑ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ መሰብሰብ መቻላቸው ስርአቱ ለተዘፈቀበት ሙስና ማሳያ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ሲገልጹ ቆይተዋል::
ሼሁ የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን በአሁኑ ወቅት ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያ እየተባለ የሚታወቀውን በ1989 ዓ.ም በብር 1 ቢሊዮን 128 ሚሊዮን 543 ሺ ከ28 ሳንቲም በመግዛት በእጃቸው አስገብተዋል፡፡ ኩባንያው በ2006 በጀት ዓመት ብቻከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ በማስገባቱ ምክንያት ባለፈው ወር የኢትዮጽያ ንግድ ባንክ ሸልሞታል፡፡ ለኢህአዴግ ከፍተኛ ጥቂት አመራሮች ባላቸው ቅርበት የሚታወቁት ሼህ አልአሙዲ ባለፉት 17 ዓመታት በፕራይቬታይዜሽን ስምበይስሙላ በሚወጡ ጨረታዎች ወሳኝ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችንና የእርሻ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ በእጃቸው ማስገባት እንደቻሉ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ምንጮች ይገልጻሉ::
ከነዚህ ድርጅቶች መካከል በቀድሞ ስማቸው የሚታወቁትን ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካዎች፣ ድል ቀለም ፋብሪካ ፣ዋንዛ የእንጨት ውጤቶች ድርጅት፣ ዪኒቨርሳል እና አዋሽ ቆዳ ሁለት ፋብሪካዎች፣ ጎንደር፣ ድሬዳዋ እና ኮምቦልቻ ሶስት የሥጋ ውጤቶችፋብሪካዎች፣ ለገደንቢ ወርቅ ፋብሪካ፣ አዲስ ጎማ (ሆራይዘን) ፋብሪካ፣ ደብረዘይት ሆራ ራስሆቴል፣ ውሽውሽ ጉመሮ ሻይ ልማትና ገበያ ድርጅት ፣ጎ ጃም፣ጎንደር፣ የላይኛውና የታችኛው ብር ሸለቆ እርሻ ልማት፣ጎጀብ እርሻ ልማት፣ ጥቁር አባይጫማ ፋብሪካ እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ሼህ አላሙዲን በተለይ ደብረዘይት ሆራ ራስ ሆቴልን እጅግ ርካሽ በሚባል በ9 ሚሊየን ብር በ1990 ዓ.ም ቢገዙም እስከአሁን ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ አጥረው ከማስቀመጥ ውጪ ሊሰሩበት አልቻሉም፡፡
ሼህ አልአሙዲን በተለይ እንደእነአቶ በረከት ስምኦን የመሳሰሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በመቀራረብ የግልና የቤተሰቦቻቸውን የህክምናና መዝናኛ እንዲሁም አንዳንድ ወጪዎችን በመሸፈን፣ እንደቤትና መኪና የመሳሰሉ ውድ ስጦታዎችንበመስጠት ግልጽ የሆነ ሙስና እንደሚፈጽሙ፣ለዚህ ወሮታቸውም የጠየቁትን የህዝብ ሐብት ያለአንዳች ችግር እንዲወስዱ እንደሚደረግ ምንቾች ገልጸዋል። ሼክ አላሙዲ ከ12 አመት በፊት ኢህአዴግን በመደገፍ በምርጫ ቅስቀሳ መሳተፋቸውይታወቃል።
No comments:
Post a Comment