Monday, November 13, 2017

በኢትዮጵያ ማናቸውንም የተቃውሞ ስልፍ ማድረግ ተከለከለ

ዋዜማ ራዲዮ- የሀገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ምክር ቤት ትናንት ባደረገው ስብስባ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚስተካከል አዲስ ስልፍና ተቃውሞ የማድረግ መብትን የሚያግድ ክልከላ ጥሏል።
አዲሱ የሰልፍ ገደብን የኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ቢያቀርብበትም ከብዙ ክርክር በኋላ ስምምነት ተደርሶበታል።
በተለይ የፀጥታ ሀይሎች “እርምጃ መውሰድ እንዲችሉ” መባሉ የኦሮሚያን ክልል እንደሚያሳስበው ገልጿል።
በአዲሱ የፀጥታ ዕቅድ መሰረት ሀገሪቱን በተለያዩ ዕዞች በሚመሩ የፌደራል መከላከያ ስራዊት አመራር ስር በማድረግ ለመቆጣጠር ታቅዷል።
አደረጃጀቱ ከዚህ ቀደም የኮማንድ ፖስት በመባል የሚጠራውን መዋቅር የሚከተል መሆኑን በስብሰባው የተካፈሉና ስለ እቅዱ በቅርበት የሚያውቁ የዋዜማ ምንጭ ነግረውናል።
በተለይ የክልልና የልዩ ሀይል እንዲሁም የፌደራል የፀጥታ ሀይሎች መካከል ያለውን አለመናበብ ለማስወገድ ማናቸውም መመሪያ በፌደራሉ ዕዝ ብቻ የሚወሰን እንደሚሆን ከስምምነት ተደርሷል ብለዋል።
“አስቸኳይ አዋጅ ተብሎ ያልወጣው አለማቀፉ ማህበረሰብ ሀገሪቱ አደጋ ላይ ናት ብሎ ያስባል፣ኢንቨስትመንትና ቱሪዝምንም ያዳክማል” በሚል መሆኑን ምንጫችን ተናግረዋል።
በፌደራል ፀጥታ አካላቱና በክልል ርዕሰ መስተዳድሮች መካከል ከፍተኛ አለመግባባትና አለመተማመን መከሰቱንም ከስብሰባው የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
“ሰው በመግደል ተቃውሞን ከማባባስ በቀር መፍትሄ አይመጣም፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ ቢበጅለት የተሻለ ነው” በሚል የተከራከሩም ነበሩ።
በተለይ ብሄርን ማዕከል ባደረገ ጥቃት ከፍ ያለ አደጋ ተጋርጦብናል ያሉ ክልሎች መለዮ ለባሹ ጣልቃ ካልገባ ብዙ ጥፋት ይደርሳል ሲሉ ስጋታቸውን ገልፀዋል።
ማህበራዊ ሚዲያን በሚመለከትም ስፊ ክርክር ተደርጓል። “እንደ አስፈላጊነቱ እርምጃ እንዲወሰድ” ከስምምነት ተደርሷል።
ከምክር ቤቱ አባላት የቀረቡትን ሀሳቦች በማካተት አዳዲስ የፀጥታ እርምጃዎች በተከታታይ የሚገለፁ መሆኑን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Sunday, November 12, 2017

አንዳንድ የገዢው ፖርቲና የሼህ አላሙዲ ደጋፊዎች ሼሁ ነገ ከእስር ተፈተው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ በማለት በመዘገብ ላይ ናቸውዜናውን ከገለልተኛ ወ ገ ን ማረጋገጥ አልቻልንም!

አንዳንድ የገዢው ፖርቲና የሼህ አላሙዲ ደጋፊዎች ሼሁ ነገ ከእስር ተፈተው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ በማለት በመዘገብ ላይ ናቸው
ዜናውን ከገለልተኛ ወ ገ ን ማረጋገጥ አልቻልንም!
አልቻልንም! ይህ ዘራፊ  ወንጀለኛ ሙሰኛ ዛሬ እንኳን ቢለቀቅ ኢትዮጰያ ውስጥ ለሰራው ወንጅል ግን አንድ ቀን የህዝብ መንግስት በሚቋቋምበት ጊዜ ግን ፍርዱን ያገኛል ምንም አትጠራጠሩ አገራችን እንዲህ አይነቱን ወንጀለኛ ዘራፊ ለማስጠጋት ቦታ ሊኖራት አይገባም!

Thursday, November 9, 2017

በኢትዮጵያ የተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ


Filed under:   
      
ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተው የውጭ ምንዛሪ እጥረት ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ፡፡ በአሁን ሰዓት በመንግስት ካዝና ውስጥ ያለው የውጭ ምንዛሪ አንድ ግለሰብ ባለሀብት ካለው ገንዘብ ጋር እንኳን የማይወዳደርበት ደረጃ ላይ መድረሱን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡ በዚህም የተነሳ አገዛዙ ለመስራት አቀድኳቸው ካላቸው ፕሮጀክቶች መካከል አብዛኞቹ ቀጥ ብለው መቆማቸው ታውቋል፡፡ ጉዳዩ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነም፣ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ አስደንጋጭ ነገር ሊከሰት እንደሚችል የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ የተከሰተው ከባድ የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጥላውን ካጠላባቸው የመንግስት ተቋማት አንዱ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮም፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረቱ የተነሳ ከፊል ስራውን ማቆሙም ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም ተቋሙ ከውጭ የተበደረውን ገንዘብ መክፈል አቅቶት፣ የአበዳሪዎቹ ዓይን እየገረፈው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ተቋሙ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ለመስራት አቅዶት የነበረው ዕቅድ በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ሳይሳካ መቅረቱን የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ ተናግረዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው እንዳሉት፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ የተቋሙ አጠቃላይ የስራ መዋቅር አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
‹‹የካፒታል ወጪያችን አፈጻጸም ዝቅተኛ ነው፡፡›› ያሉት ዶ/ር አንዱዓለም፣ ቀጠል አድርገው ‹‹በአሁኑ ጊዜ አብዛኛዎቹ ግዥዎቻችን በውጭ ምንዛሪ እጥረት ምክንያት ተይዘው ነው የተቀመጡት፡፡  ግዥዎቻችን የሚከናወኑት ከውጭ ገበያ ነው፡፡ እነዚህን ዕቃዎች ለማስገባት የውጭ ምንዛሪ ይጠይቃሉ፡፡ ነገር ግን የእነዚህ ዕቃዎች ግዥዎች ባንክ ውስጥ ሠልፍ ላይ ነው ያሉት፡፡›› በማለት በሀገሪቱ ውስጥ ምን ያህል የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደተከሰተ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከውጭ ተገዝተው የመጡ የባቡር ሐዲዶች በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሀገር ቤት ሳይገቡ ቀርተዋል፡፡ አሁን ደግሞ ኢትዮ ቴሌኮም በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ስራውን መስራት እንዳልቻለ ያማረረ ሲሆን፣ በሌሎች የመንግስት ተቋማት ያለው የውጭ ምንዛሪ እጥረትም የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ወደኋላ እየጎተተው እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ብሔራዊ ባንክ በጥቅምት ወር መጀመሪያ የአንድ ዶላር ዋጋ በ27 የኢትዮጵያ ብር እንዲመዘነር አዲስ ህግ ካወጣ በኋላ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ሙሉ በሙሉ መቃወሱን መረጃዎች እየጠቆሙ ናቸው፡፡
ከመንግስት ተቋማት በተጨማሪ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ የተሰማሩ የግል ባለሀብቶች፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረት የተነሳ ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ እንዳልሆነ በመናገር ላይ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ ከተሰማሩ ሰዎች አንዱ የሆነው አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ ከሶስት ሳምንት በፊት ከሀገር ውስጥ ሚዲያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፣ ከባንክ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት ያለው ውጣ ወረድ እና ሰልፍ አሰልቺ መሆኑን በምሬት ተናግሮ ነበር፡፡ ኃይሌ ‹‹በዚህ ሁኔታ ስራ መስራት ይከብዳል›› ሲልም ተማሮ ተናግሮ ነበር፡፡
BBN News November 9, 2017

ሳውዲ በሙስና ካለአግባብ የባከነው ገንዘብ 100 ቢሊየን ዶላር መሆኑን አጋለጠች ።

ኢሳት ዜና–ጥቅምት 30/2010) በሳውዲ አረቢያ እየተካሄደ ያለው ጸረ ሙስና ዘመቻ ምርመራ ካለአግባብ የባከነው ገንዘብ 100 ቢሊየን ዶላር መሆኑን አጋለጠ። በሌብነት ተጠርጥረው የተያዙት ሰዎች ቁጥርም 199 መድረሱን የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታውቋል። ባለፈው ቅዳሜ ምሽት የተጀመረው ተጠርጣሪ ልኡላንን፣ሚኒስትሮችንና ነጋዴዎችን ኢላማ ያደረገው የጸረ ሙስናው ዘመቻው በ32 አመቱ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሳልማን የተመራ ነው። በዘመቻው ተጠርጥረው ከተያዙት ውስጥ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የሆኑት ሼህ መሀመድ አላሙዲን እንደሚገኙበት ይታወቃል። ጠቅላይ አቃቢ ሕጉ ሼህ ሳውድ አል ሞጀብን ጠቅሶ ቢቢሲ እንደዘገበው 100 ቢሊየን ዶላር የሚሆን ገንዘብ በሀገሪቱ በተደራጀ መንገድ በተፈጸመ ዝርፊያ ባለፉት ጥቂት አስርት አመታት ባክኗል ብለዋል። ዝርፊያ ስለመፈጸሙ...ም ጠንካራና አስተማማኝ መረጃ አለን ብለዋል። በዝርፊያው የተጠረጠሩት የንጉሳዊ ቤተሰቦችና ባለስልጣናት በቁጥጥር ስር መዋላቸው በሀገሪቱ ያለውን የዕለት ተዕለት የንግድ እንቅስቃሴ እንዳላወከው አስታውቀዋል። የተጠርጣሪዎቹ የግል የባንክ ተቀማጭ ሂሳብ መዘጋቱንም ተናግረዋል። እስካሁን 1700 የባንክ ተቀማጭ የሂሳቦች መዘጋታቸውም ታውቋል። የጸረ ሙስና ኮሚቴውም ወደ ሚቀጥለው የምርመራ ደረጃ ለመንቀሳቀስ ሕጋዊ ፍቃድ እንዳለው ተናግረዋል። አቃቢ ሕጉ አክለውም እስካሁን 208 የሚሆኑ ሰዎች ለጥያቄ መቅረባቸውንና ሰባቱ ሳይከሰሱ በነጻ መለቀቃቸውን አስታውቀዋል። በሐገሪቱ ንጉስ ትዕዛዝ የተዋቀረው የጸረ ሙስና ኮሚቴም ስራውን በተቀላጠፈ ሁኔታ እያካሄደ መሆኑን አስታውቀዋል። ባለፉት ሶስት አመታት በተካሄደው ምርመራም 100 ቢሊየን ዶላር በተደራጀ ዘረፋ መባከኑን የሀገሪቱ አቃቢ ህግ ጨምረው ገልጸዋል። የተጠርጣሪዎቹን የሕግ መብት ለመጠበቅ ሲባልም በግለሰብ ደረጃ እያንዳንዳቸው ፈጽመውታል ተብሎ የሚጠረጠረውን ወንጀል ግን ከመግለጽ እንቆጠባለን ሲሉ ተናግረዋል አቃቢ ሕጉ። ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት አንዱ የሆኑት የሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲ ጉዳይ በኢትዮጵያ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ሲቀጥል የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ዝምታን መርተዋል። የሕወሃት ድምጽ የሆነው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ግን ጉዳዩን በተመለከተ ዘገባዎችን ሲያወጣ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ለመንግስትና ለገዢው ፓርቲ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ መንግስት ጉዳዩን በተመለከተ በዲፕሎማሲ መንገድ የሚመጡ መረጃዎችን እየተከታተለ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ከዚህ ውጪ ግን ሳውዳረቢያ ሉአላዊ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሌላ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር እንደሌለ ተናግረዋል።

መረጃ በጨፌ ዶንሳ ው ተቃውሞ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በቃጠሎ ወድመዋል።

መረጃ
በጨፌ ዶንሳ ተቃውሞው ዛሬም ቀጥሎ ውሎአል። በርካታ ትምህርት ቤቶች፣ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና የመንግስት መስሪያ ቤቶች በቃጠሎ ወድመዋል። እስከ 15 የሚደርሱ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ከከተማዋ በ500 ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው ሚሳኤል ምድብ እየተባለ የሚጠራው የአየር መቃወሚያን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች የተከማቹበት ቦታ፣ በልዩ ሁኔታ እየተጠበቀ ነው። ተቃውሞው ነገም ይቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

Wednesday, November 8, 2017

ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ለአደጋ የተጋለጠው የባለሀብቶቹ ንብረት 33 ቢሊየን ዶላር መሆኑ ተመልክቷል።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010)የሳውዲ አረቢያ መንግስት ባለፈው ቅዳሜ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ የሌሎች ታሳሪዎችን የባንክ ተቀማጭ ሒሳብ አገደ። ከእስሩ ጋር በተያያዘ በአጠቃላይ ለአደጋ የተጋለጠው የባለሀብቶቹ ንብረት 33 ቢሊየን ዶላር እንደሚገመትም ከብሉምበርግ ዘገባ መረዳት ተችሏል። የሼህ መሀመድ አላሙዲን ቃል አቀባይ ከብሉምበርግ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ርምጃው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ የተገደበና በሌሎች ሀገራት ያላቸውን ንብረት የማይመለከት መሆኑን ገልጸዋል። ቋሚ መኖሪያቸውን በሳውዳረቢያ ጅዳ ያደረጉት ሼህ መሀመድ አላሙዲን እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ በሳውዳረቢያ ሪያድ በተካሄደው ግሎባል ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከተገኙ በኋላ መያዛቸውና መታሰራቸውም ተመልክቷል። ከሳውዲ ባሻገር በሞሮኮ፣በሲውዲን...ና በኢትዮጵያ ከፍተኛ ኢንቨስትመትን ያላቸው ሼህ መሀመድ አላሙዲን የሳውዲው እስራትና እገዳ በሌሎች ሀገራት ኢንቨስትመንታቸው ላይ ተጽእኖ አይኖረውም ሲሉ ቃል አቀባያቸው ቲም ፓንደር ተናግረዋል። በሳውዲ የተፈጠረውም ሁኔታ የንጉሳውያን ቤተሰቦች የውስጥ ችግር ነው ሲሉ ለብሩምበርግ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የ10 ነጥብ 3 ቢሊየን ዶላር ሀብት ባለጸጋ በሆኑት በሼህ መሀመድ አላሙዲንና በሌሎች ታሳሪዎች ላይ የተጣለው እገዳ የግል ተቀማጭ ሂሳባቸውን ብቻ የሚመለከት መሆኑንም የሳውዳረቢያው ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። የታሳሪዎቹ ኩባንያ ተቀማጭ ሒሳብ አለመታገዱንና ሕጋዊውን የባንክ ስርአት ተከትለው ገንዘባቸውን ማንቀሳቀስ እንደሚችሉም ይፋ ሆኗል። የብሪታኒያው ዴይሊ ሜል ይፋ ያደረገውና በታዋቂው ሪትዝ ካርልተን ሆቴል ወለል ላይ ፍራሽና ብርድልብስ ታድሏቸው የታሰሩት ባለስልጣናት፣ባለሃብቶችና ልኡካን በቁጥር 50 ያህል መሆናቸው ተመልክቷል። የሳውዳረቢያ ጠቅላይ አቃቢ ህግ እንደገለጹት ደግሞ ይህ እስራት የመጨረሻው ሳይሆን የመጀመሪያ ምዕራፍ ሲሆን በቀጣይ የሚታሰሩ መኖራቸውንም አስታውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዲቪ ቪዛ ሎተሪ እንዲሰረዝ በጠየቁት መሰረት ኢትዮጵያ ተጎጂ ነች ተባለ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 29/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዲቪ ቪዛ ሎተሪ መርሃ ግብር እንዲሰረዝ በጠየቁት መሰረት ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ በአፍሪካ ኢትዮጵያ፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ግብጽ ዋነኛ ተጎጂዎች ይሆናሉ ተባለ። እነዚህ ሀገራት በመርሃ ግብሩ መሰረት ብዙ ኮታ ከሚያገኙት ግንባር ቀደሞቹ መካከል መሆናቸውም ታውቋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ጥያቄውን ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት አንድ የኡዝቤክስታን ተወላጅ ኒዮርክ ውስጥ ባደረሰው ጥቃት 8 ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ ነው። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሀገሪቱን የተወካዮች ምክር ቤት የዲቪ ቪዛ ሎተሪ መርሃ ግብር እንዲሰረዝ በጠየቁት መሰረት መርሃግብሩ የሚቀር ከሆነ በአፍሪካ ኢትዮጵያ፣ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና ግብጽ ዋነኛ ተጎጂዎች እንደሚሆኑ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት አንድ ...የኡዝቤክስታን ተወላጅ በእቃ መጫኛ መኪና ባደረሰው ጥቃት 8 ሰዎችን በኒዮርክ ከተማ ከገደለ በኋላ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወዲያውኑ የሀገሪቱ ምክር ቤት የዲቪ ቪዛ ፕሮግራምን እንዲሰርዝ ጠይቀዋል። የኡዝቤክስታኑ ተወላጅ ሳይፉሎ ሳይፓቭ የዲቪ ሎተሪ እድለኛ በመሆን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2010 ወደ አሜሪካ መምጣቱ ታውቋል። በዲቪ ሎተሪ ወደ አሜሪካ የመጡ ሰዎች ጥቃት ሲፈጽሙ ይሄ ለ6ኛ ጊዜ መሆኑ ነው። በዚህም ምክንያት ይመስላል የዲቪ ሎተሪ ጉዳይ በአሜሪካ የፖለቲካ ሰዎች ዘንድ እንደገና መነጋገሪያ እየሆነ ነው። በተለይ የሪፐብሊካን ፓርቲ ሰዎች የዲቪ ሎተሪው ወንጀለኞች ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ቀላል መንገድ ፈጥሯል ባይ ናቸው። በአሜሪካ ምክር ቤት ያሉ አባላት የፕሬዝዳንቱን ሃሳብ እንደሚቀበሉትም ባልፈው ሰኞ አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኒዮርክ የደረሰውን ጥቃት እንደሰሙ ይህ የሎተሪ መርሃ ግብር ሰዎች በችሎታቸው ሳይሆን እንደ እድል ዕጣው ስለደረሳቸው ብቻ የሚመጡበት ነው ብለዋል። አፍሪካ በአንደኝነት የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ስትሆን አውሮፓና ኢሲያ ደግሞ ይከተላሉ። ባለፈው አመት ከአፍሪካ ከግብጽ 2 ሺ 855 ሰዎች የዕጣው አሸናፊ ሲሆኑ ከዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኮንጎ 2 ሺ 778 ሰዎች እንዲሁም ከኢትዮጵያ ደግሞ 2 ሺ 143 ሰዎች የዕጣው እድለኞች በመሆን በ3ኛ ደረጃ ተመዝግባለች። በየአመቱ ወደ 50ሺ የሚጠጉ ሰዎች የዕድሉ ተጠቃሚ እንደሆኑም ታውቋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2001 በኒዮርክ ከደረሰው የአሸባሪዎች ጥቃት 10 አመት ቀደም ብሎ በ1990 በፕሬዝዳንት ጆርጅ ኤች ደብሊው ቡሽ ፍርማ ህግ ሆኖ የወጣው የዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ መርሃ ግብር የዕድሉ ተጠቃሚ ሆነው የሚመጡ ጥቂት ሰዎች እያደረሱ ባለው የሽብር ጥቃት ምክንያት መርሃ ግብሩ እንዲያከትም ግፊት እየተደረገ ይገኛል።

መረጃ በ ቄሮዎች በጨፌ ዶንሳ ከተማ የኦህዴድ ጽ/ቤትን ጨምሮ በርካታ ድርጅቶች ወድመዋል።

መረጃ
በጨፌ ዶንሳ ከተማ የሚገኙ ቄሮዎች ለሁለተኛ ቀን ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ እያደረጉ ነው። ከሸንኮራ ምንጃር ወጣቶች ጋር በመደዋወልና በመነጋገር ተቃውሞውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የኦህዴድ ጽ/ቤትን ጨምሮ በርካታ ድርጅቶች ወድመዋል።
መከላከያና ፌደራል ፖሊስ ገብቶ በህዝብ ላይ መተኮስ ጀምሯል። የቻይና አረርቲ እንዱስትሪ ፓርክ ከፍተኛ ወድመት ደርሶበታል።

20 ሚሊየን የሚሆነዉ የደቡብ ህዝብ ለምን ዝም አለ?



ሁልጊዜ ስለ አማራና ኦሮሞ ነዉ የሚወራዉ ሌላ ብሄረሰብ በኢትዮጵያ የሌለ እስኪመስል ድረስ::
የደቡብ አክቲቪስትወች የሉምወይ??በ2ቱ ብሄር ትግል ብቻ ነፃ መውጣት የስርአት ለዉጥ ማምጣት ይቻላል ወይ? ደቡብ ላይ የሚሰራ በደል የለም ወይ? የራሳቸው አካባቢያዊ ችግርወች እንዳሉባቸዉ ይታወቃል ትምህርታቸዉን አቁዋርጠዉ ወደ አዲስ አበባ በመሄድ በዝቅተኛ ስራወች ላይ በሰፊው ተሰማርተው የሚታዩት ህፃናትና ታዳጊወች በተለይም የወላይታ ታዳጊወች ጉዳይ በአንድ ወቅት የአዲስ አበባ ህዝብ መነጋገሪያ ነበር መንግስትትም አምኖ የተለያዩ የደቡብ ወረዳዎች በመሄድ ዶክመንተሪ የሰራበት አንዳንድ አካባቢዎች አዛውንቶች ብቻ የቀሩበት ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚደረገዉ ለከፍተኛ ስቃይና ሞት የሰውነት አካላት ዝርፍያ የተጋለጠ ዘግናኝ ጉዞ መነሻው የደቡብ አገራችን ክፍል ነዉ የደቡብ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ትግል በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ ለምን ደካማና ቀዝቃዛ ሆነ? በኦሮሚያ ና በአማራ የተነሳውን አመፅ ተከትሎ 76 የኦሮምኛ ወደ15 የአማራ የትግል ዘፈኖችና መዝሙር ወች ሲሰሩ የደቡብ አርቲስቶች ዝምታን ነዉ የመረጡት ተመችቱዋቸዉ ይሆን? አደራጅ አንቀሳቃሽ ማጣት???ምንድነዉ ምክንያቱ???የደቡብ ህዝብ ለመብትና ለኩልነት የሚደረገዉን ትግል ለምን መቀላቀል አልቻለም?? የደቡብ ምሁራንስ ልክ እንደ አሰፋ ጫቦ ለምን ድምፃቸዉን አያሰሙም አገር እየፈራረሰ……

አስተያየትዎን ይፃፉ

ዜና ሰበር በምንጃር እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ የቻይና ፋብሪካ እየወደመ ነው


መረጃ
በምንጃር እየተካሄደ ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ የቻይና ፋብሪካ እየወደመ ነው
የፋብሪካው ዘበኛ ተኩስ በመክፈቱ እስካሁን 3 ሰዎች መጎዳታቸው ታውቋል።
ተጨማሪ መረጃ
የአረርቲ እንዱስትሪ ፓርክ ሃላፊዎች ወታደሮች እንዲላኩላቸው ጥያቄ ቢያቀርብም እስካሁን ከገዢው ፓርቲ በኩል የተሰጠ መልስ የለም። የቻይና ዜጎችን ለማስወጣት መኪኖች ተንቀሳቅሰዋል።

Tuesday, November 7, 2017

ኬንያ 132 ኢትዮጵያውያንን እስር ቤት ከተተች


      
  

 
በኬንያ 132 ኢትዮጵያውያን ለእስር ተዳረጉ፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ለእስር የተዳረጉት እንደተለመደው በህገ ወጥ መንግድ ድንበር አቋርጣችሁ ገብታችኋል በሚል ምክንያት ነው፡፡ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአንድ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ሳለ ሲሆን፣ ባይያዙ ኖረ ወደ ታንዛንያ የማቅናት ዕቅድ ነበራቸው፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ከሀገራቸው ተነስተው መንገድ የጀመሩት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት ሲሆን፣ ሆኖም ወደ ታንዛንያ ከማቅናታቸው በፊት ናይሮቢ ላይ በቁጥጥር ስር ለመዋል ተገድደዋል፡፡

ኢትዮጵያውያኑ ከሀገራቸው የተነሱት በደላሎች አማካይነት ሲሆን፣ ደላሎቹ እስከ ደቡብ አፍሪካ እንደሚያደርሷቸው ውል እንደነበራቸውም ታውቋል፡፡ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላም፣ በድለላ ስራው ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉ ሁለት ኬንያውያንም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ስደተኞቹ በቀጣይ ፍርድ ቤት ቀርበው ቅጣት ሊተላለፍባቸው እንደሚችል ይጠበቃል፡፡ ቅጣቱ ወደ ገንዘብ ተቀይሮ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ሊደረግ እንደሚችልም ተገምቷል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች በሀገራቸው ያለውን የስራ አጥነት፣ የአገዛዙን አምባገነንነት እና መሰል ጉዳዮች ሸሽተው እንደሚሰደዱ ይታወቃል፡፡ ፊደል ያልቆጠረውን ጨምሮ እስከ ባለ ድግሪ ድረስ በስራ አጥነት የተነሳ ሀገር ጥሎ የሚሰደድባት ኢትዮጵያ፣ ለዜጎቿ አጅግ አስከፊ ሀገር እየሆነች መምጣቷን በሀገር ቤት ያሉ ዜጎች ይገልጻሉ፡፡ ‹‹በሀገር ቤት ያለው ኑሮ ከአቅም በላይ ባይሆን ኖሮ፣ ሰው እንደ ቅጠል የሚረግፍበትን በረሃ እና ውቅያኖስ አቋርጦ ስደት የሚወጣ አይኖርም ነበር፡፡›› ይላሉ-በሀገር ቤት ኑሮ የተማረሩ አስተያየት ሰጪዎች፡፡ በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በኑሮውም በፍትሐዊ አስተዳር በኩልም ያልተዋጣለት እና ከቀን ወደ ቀን እየባሰበት የመጣ ስርዓት መሆኑን የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎቹ፣ የአገዛዙ ዕድሜ ካላጠረ በቀር በቀጣይ ዛፍ እና ወንዙ ጭምር ሳይሰደድ አይቀርም እንኳን ሰዉ ይላሉ- አስተያየት ሰጪዎቹ፡፡
BBN News November 7, 2017

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶች የተሳሳተ መረጃ ሰጠ

  


 

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች የተሳሳተ መረጃ ሰጠ፡፡ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በተገኙበት በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በተካሔደው ወይይት ላይ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች ተገኝተው ነበር፡፡ ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ለማድረግ በስብሰባው ላይ ቢገኙም፣ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል የተለያዩ ነባራዊ ሁኔታዎችን አዛብተው ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት የፖለቲካ ምስቅልቅል እና የህዝብ ተቃውሞ እየበረታ ቢመጣም፣ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ግን ለዲፕሎማቶቹ ገለጻ ባደረጉበት ሰዓት፣ ሀገሪቱ ፍጹም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ ነው የተናገሩት፡፡ ‹‹በሀገሪቱ የተከሰተውን ግጭት አስቁመናል፡፡›› ሲሉ የተናገሩት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ህዝብ ላነሳው ጥያቄዎችም መንግስታቸው ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም የዶ/ር ወርቅነህ መንግስት ለህዝብ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ከመስጠት ይልቅ፣ ንጹኃንን በአደባባይ እየገደለ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ስለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ገለጻ ባደረጉበት ሰዓት ደግሞ፣ ‹‹መንግስት ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር እየተደራደረ እንደሚገኝና፣ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መግባባት ላይ እንደተደረሰም›› ተናግረዋል፡፡ ከመንግስት ጋር እየተደራደሩ ይገኛሉ የተባሉት ተቃዋሚዎች ግን፣ በህዝብ ዘንድ ፍጹም ተቀባይነት የሌላቸው፣ ከሊቀ መንበራቸው እና ከራሳቸው ሰራተኞች በቀር ሌላ ደጋፊም ሆነ ተከታይ ህዝብ የሌላቸው ፓርቲዎች መሆናቸው ሲነገር ቆይቷል፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ ከእነዚህ ጉዳዮች በተጨማሪም፣ በሀገሪቱ በጠቅላላ አሁን ላይ የሚያሰጋ ነገር እንደሌለ፣ የህዝቡም ጥያቄ በመንግስት አመራሮች እየተመሰለ እንደሆነ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ፍትሐዊ አስተዳደር እንደሰፈነ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ ድርጅት ተወካዮች ገለጻ አድርገዋል፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ገለጻ ያደረጉበት ውይይት እጅግ የሚያሳፍር እና አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በዲፕሎማቶች ፊት በዚህ ደረጃ ይዋሻሉ ተበሎ ያልተጠበቀበት እንደነበር ውይይቱን የተከታተሉ ታዛቢዎች ተናግረዋል፡፡ ወይይቱ በጠቅላላ በተሳሳተ መረጃ እና የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ በማይገልጹ ቃላት የታጨቀ እንደበር ታዛቢዎቹ አክለው ተናግረዋል፡፡

በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው መከላከያ ወታደር እየከዳ መምጣቱ ታወቀ

 

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ)
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር መከላከያውን እየከዳ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ስጋት ተፈጥሯል። በጄነራል ሳሞራ የኑስ የተመራው ከፍተኛ የጦር አዛዦች የተገኙበት ስብሰባ ላይ ከወታደሮች መክዳት ጋር በተያያዘ ሰፊ ውይይት እንደተደረገ ለማወቅ ተችሏል።
በተለያዩ ክፍለ ጦሮች ውስጥ የወታደሩ መክዳት በከፍተኛ ሁኔታ መስተዋሉንና ባሉትም ወታደሮች መሀል የመንፈስ ጥንካሬ መዳከሙ በስብሰባው ላይ በሰፊው ውይይት የተደረገበት ጉዳይ ሆኗል። የክፍለ ጦር አዛዦች የወታደሮችን መክዳት የመከላከል ሃላፊነት የነሱ ድርሻ እንደሆነና ከአሁን በኋላም እድገት የሚሰጠው ወታደሮችን በማቆየት አመርቂ ውጤት ላመጡ አዛዦች እንደሚሆን ጄነራል ሳሞራ ገልጿል። በመከላከያ ውስጥ ከመክዳት ጋር ተያይዞ እየተፈጠረ ያለው ችግር ሃገሪቷ ከገባችበት የፖለቲካ ምስቅልቅል ጋር የተቆራኘ እንደሆነ መከላከያ ውስጥ ያሉ የጦር አዛዦች እርስ በርስ ሲያወሩ የሚገልጹት ቢሆንም በስብሰባው ላይ ደፍሮ የተናገረ እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል። እንዲሁም የመከላከያ ሃይል ከምንጊዜም በላይ ጠንካራ እንደሆነ በሳሞራ የኑስ የቀረበው ገለጻ በስብሰባው ላይ የተገኙ አዛዦችን ሊያሳምን እንዳልቻለ ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተል የነበረ ወኪላችን ተመልክቷል።
በስብሰባው ማጠቃለያ ላይ የጄነራል ሳሞራን ስም እያነሱ ሲያሞጋግሱ ተስተውሏል። ከስብሰባው በኋላ የጦር አዛዦች እንዴት ተኩኖ ነው እየከዳ ያለውን ሰራዊት ማስቆም የሚቻለው፤ ሰራዊቱ ልቡ ከኛ አይደለም፤ በዚህ ሁኔታ መከላከያ አደጋ ውስጥ እየገባ ነው በማለት ጭንቀታቸውን ሲገልጹ ተስተውለዋል። በመከላከያ የተለያዩ ክፍለ ጦሮች ውስጥ የሚገኙ ወታደሮች በከፍተኛ ቁጥር መከላከያውን እየለቀቁ መምጣታቸውን ተከትሎ በአሁኑ ሰአት አንድ ሬጂመንት ጦር መያዝ ከሚገባው 700 የሰራዊት ቁጥር ውስጥ ከ400 በላይ እንዳልሆነ ከመከላከያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

አላሙዲንን በሆቴሉ ወለል ፍራሽ ታድሏቸው በአንድ ቦታ መታሰራቸውን በምስል የተደገፉ ሪፖርቶች አመለከቱ።

(ኢሳት ዜና–ጥቅምት 28/2010)ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ በቁጥጥር ስር የዋሉት የሳውዲ ባለሃብቶችና ባለስልጣናት የታሰሩበት ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል መሆኑ ቢረጋገጥም በሆቴሉ ወለል ፍራሽ ታድሏቸው በአንድ ቦታ መታሰራቸውን በምስል የተደገፉ ሪፖርቶች አመለከቱ። የሼህ መሀመድ አላሙዲን በሙስና ተጠርጥሮ መታሰር በኢትዮጵያ ባላቸው ኢንቨስትመንት ላይ የሚኖረው አንድምታ አነጋጋሪ ሆኗል። የሼህ መሀመድ አላሙዲን ከሳውዲ ልኡላንና ነጋዴዎች ጋር መታሰር በአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በስፋት መዘገቡ ቢቀጥልም በኢትዮጵያ ውስጥ የመንግስትና የፓርቲ መገናኛ ብዙሃን በዝምታቸው ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሳውዲ ከሙስና ጋር በተያያዘ እስራት መከተሉን ቢዘግብም የሼህ መሀመድ አላሙዲንን መታሰር ሳይጠቅሰው አልፏል። ዳሽን ባንክ ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባ ከተ...ማ ከአንድ ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ባስገነባው ግዙፍና ዘመናዊ ሕንጻ ምርቃት ላይ ይገኛሉ ተብለው የተጠበቁት ሺህ መሀመድ አላሙዲን በዕለቱ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ በመታሰራቸው ሕንጻው እሳቸው በሌሉበት ተመርቋል። በኢትዮጵያ ሕግ በባንክና ኢንሹራንስ ዘርፍ ለመሰማራት የተፈቀደው ለኢትዮጵያ ዜጎች ብቻ በመሆኑ ሼህ መሀመድ አላሙዲን ዳሽን ባንክን በቤተሰቦቻቸው አማካኝነት ማቋቋማቸው ተመልክቷል። በኢትዮጵያ በዋናነት በሆቴልና በማዕድን እንዲሁም በእርሻና በሲሚንቶ ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራታቸው የተገለጸው የ71 አመቱ ባለሃብት ሼህ መሀመድ አላሙዲን በተለይ ከ1997 ምርጫ ወዲህ ስልጣን ላይ ላለው ቡድን በግልጽ በሚያሳዩት ድጋፍ ተቃውሞ ይሰነዘርባቸዋል። በተለይ በማዕድን ዘርፍ በሚሰሩት ኢንቨስትመንት የሀገሪቱን የወርቅ ሀብት በከፍተኛ ደረጃ እየመዘበሩ ነው በሚል ትችቶች እየቀረበባቸው ይገኛል። ይህም ለስርአቱ ለሚያሳዩት አጋርነት ስልጣን ላይ ባለው ቡድን በሚደረግ ድጋፍ የሚከናወን መሆኑም ተመልክቷል። በሌላም በኩል ባለሃብቱ ለስርአቱ ከሚሰጡት ድጋፍ ባልተናነሰ የሚያደርጉት በጎ አድራጎት ለሀገር ይጠቅማል በሚል ባለሃብቱን በበጎ የሚያነሷቸውም አልጠፉም። በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የመንግስትና የገዢው ፓርቲ መገናኛ ብዙሃን የሼህ መሀመድ አላሙዲንን መታሰር በተመለከተ በዝምታ መቀጠላቸው የባለሃብቱ መታሰር በስርአቱ ውስጥ ድንጋጤ ስለመፍጠሩ የተገለጸውን የሚያጠናክር ሆኖ ተገኝቷል። የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ የሰፈነውን የፖለቲካ አፈናና የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲያሻሽል ያግዛል በሚል የአሜሪካ ኮንግረስ እንዲያጸድቀው የቀረበውን ረቂቅ ህግ ለማክሸፍ ከመንግስት ጋር ሎቢስት በመቅጠር ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውና በዚህ ረገድ የሚፈጠረው ክፍተት የመንግስት ባለስልጣናትን ሳያሳስብ እንዳልቀረ የሚገልጹ ወገኖች አሉ። በሌላም በኩል ብዙዎቹ ባለስልጣናት ገንዘብ የሚያሸሹት በርሳቸው አማካኝነት በመሆኑም ይህም ተጨማሪ ምናልባትም ዋና ስጋት እንደሆነባቸው ታውቋል። የሼህ አላሙዲን መታሰር በርሳቸው የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው አንድምታ በእስሩ ርዝመትና ውጤት እንደሚወሰንም ባለሙያዎች ይናገራሉ። ሼህ መሀመድ አላሙዲንን ጨምሮ ባለፈው ቅዳሜ የተያዙትና አሁንም በመያዝ ላይ የሚገኙት ባለሃብቶችና ባለስልጣናት በሪያድ እጅግ ውድ በተባለው ሪዝ ካርተን ሆቴል ወለል ላይ የነፍስ ወከፍ ፍራሽ ታድሏቸው መታሰራቸውን አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን በምስል አስደግፈው ይፋ አድርገዋል። የሆቴሉ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡም ይፋ ሆኗል።

የአማራ ብሄር ተወላጆች ከአሶሳ ከተማ እንዲወጡ እየተደረገ ነው

(ኢሳት ዜና ጥቅምት 28 ቀን 2010 ዓም) ኤች አይቪ ቫይረስ አለባቸው የተባሉ የአማራ ብሄር ተወላጆች ከአሶሳ ከተማ እንዲወጡ እየተደረገ ነው
በቤንሻንጉል አሶሳ ከተማ የሚኖሩ ምግብ ና የጀበና ቡና በመሸጥ የሚተዳደሩ የአማራ ሴቶች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአስገዳጅ ሁኔታ የኤች አይቪ ምርመራ እንዲያደርጉ እየተገደዱ ሲሆን፣ ቫይረሱ ተገኝቶባችሁዋል የተባሉት ሴቶች ከስራ ቦታቸው ተፈናቅለው ወደ ክልላቸው እንዲሄዱ መገደዳቸውን ለአማራ ክልል ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እንዲሁም ለአማራ ክልል ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ማመልከታቸውን ከቢሮው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የሴቶችን አቤቱታ ተከትሎ ከክልሉ ቢሮ አጣሪ ኮሚቴ ተመድቦ ወደ አሶሳ መላኩን ለማወቅ ተችሎአል። ድርገቱ የክልሉን ተወላጆች ከቤንሻንጉል ክልል ለማስወጣት የተቀየሰ አዲስ ስልት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋ...ል።
በሌላ በኩል ሰሞኑን በሳምንቱ መጨረሻ በፋሲል ከነማ እና ውልዋሎ አዲግራት መካከል የተካሄደውን ጨዋታ ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት ደማቸው የፈሰሰውን ወጣቶች ደም ደም እንመልሳለን በማለት ሁከት ለመቀስቀስ እንቅስቃሴ ጀምረዋል የተባሉ ወጣቶች ተለይተው በክትትል ውስጥ እንዲገቡ እና የእጅ ስልካቸውም እንዲጠለፍ መደረጉን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል።
ትናንት በነበረው የፖሊሶች ስብሰባ ላይ ኮማንደር ተኮላ " ደህና ወደ ሰላም የመጣውን ህዝብ እራሳቸው እየነካኩ ሌላ ችግር እየፈጠሩብን ነው፣ አሁን እንደገና የሞተ ሴል ነፍስ እየዘራ ነው፣ ካሁን በሁዋላ እነሱ እዛ እየነካኩ እዚህ ችግር ቢፈጠር እኛ ተጠያቂ አንሆንም” በማለት መናገሩን የፖሊስ ምንጮቻችን ገልጸዋል።


ከአዲስ አበባ ዙሪያ ካሉ ኦሮሚያ ከተሞች የወላይታ ተወላጆች እየታፈሱ ነው።





በአዲስ አበባ ዙርያ የኦሮምያ ክልል ልዩ ዞን ውስጥ የሚኖሩ የኦሮምያ ተወላጅ ያልሆኑ በብዛት የወላይታ ተወላጆችን ከከታ አካባቢ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎችና ባለስልጣናት አስገዳጅነት በመኪና ተጭነው እንዲወጡ ከተደረገ በሁዋላ በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6  የወጣቶች ማዕከል ህንፃና በወረዳው ፅ፨ቤት ቅፅር ግቢ ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፥፥ ቁጥራቸው በግምት ከ400 - 500 ይደርሳል፥፥ የተፈናቀሉበት ምክንያት ለጊዜው በውል የታወቀ አይደለም፥፥

ሰበር_መረጃ ደሴ ነጋዴዎች የስራ ማቆም አድማ ጀምረዋል፡፡



#ሰበር_መረጃ
#በዛሬው እለት በደሴ ከተማ ልዩ ቦታው አራዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደሴ ከተማ ትልቁ የንግድ ማእከል በሆነው ቦታ አምስት ትልልቅ ህንፃዎች በድምሩ ከአንድ ሺህ በላይ ሱቆች የስራ ማቆም አድማ ጀምረዋል፡፡
************
#አገዛዙ በህዝብ ላይ ጥሎት የቆየው ካቅም በላይ የሆነ የግብር ክፍያን በመቃወም በአካባው ይነግዱ የነበሩ ባለሱቆች ሱቆቻቸውን መዝጋታቸውና ስራ ማቆመማቸው ታውቋል፡፡ ነጋዴዎቹ እንደሚሉትም አገዛዙ ያለ ሃቅማችን መክፍል የማንችለውን ግብር ጥሎብናል የተጣለብን ግብር ከጠቅላላው ገቢያችን የበለጠነው በማለት ቅሬታቸውንም አሰምተዋል የአገዛዙ አገልጋይ የሆኑ የቀበሌው ሹሞችም በቦታው በመሆን ሱቃችሁን ካልከፈታችሁ እርምጃ እንወስዳለን እያሉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ነጋዴዎቹም በበኩላቸው የዚህ ስርዓት አምባገነንነትና ዘራፊነቱን ተገንዝባችሁ ሌሎቻችሁም የአካባቢው ሰዎች የነዚህን ነጋዴዎች ፈለግ በመከተል አገዛዙን እምቢ አልገዛም ያለ አግባብ ግብር አልከፍልም ለሹሞች መበልፀጊያ ይሆን ዘንድ የልጆቼን ጉሮሮ አልዘጋም በማለት የዚህ ትግል አካል እንድትሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ ውድ ተከታታዮቻችን ከስፍራው የሚደርሱንን መረጃዎች እየተከታተልን የምናቀርብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬዲዮ
አስተያየትዎን ይፃፉ

የዝቅጠት መጨረሻ!


የዝቅጠት መጨረሻ! የኢትዮጵያ መንግስት ስንቱን ዜጋ በፖለቲካ አቋሙና በጋዜጠኝነት ሙያው ሳቢያ አስሮ ዘቅዝቆ ሲገርፍ ትንፍሽ ያላለ ሁላ አሁን አንድ ሀብታም ያውም በወንጀል ያውም ሳውዳረቢያ ሲታሰር የፍቱልን ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣል! እስኪ ምን ይመስላችሁዋል?

Sunday, November 5, 2017

ሰበር ዜና በአሜሪካ በቶክስ እሩምታ በጥቂቱ 27 ሰው ሞተ ::

ሰበር ዜና
አሜሪካ- ቴክሳስ በአንድ ቤተክርስቲያን በእሁድ /ሰንበት ፀሎት ላይ በነበሩ ፀላዩች ላይ ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተከፈተ የቶክስ እሩምታ በጥቂቱ 27 ሰው ሲሞት በርካቶች መቁሰላቸው እየተዘገበ ነው::

ሼክ መሐመድ አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረከት ስምዖን ጀርባ ሰርተውታል ተብሎ የሚጠረጠሩበት የሙስና ወንጀሎች

 

ሼክ መሐመድ አላሙዲ ኢትዮጵያ ውስጥ ከነበረከት ስምዖን ጀርባ ሰርተውታል ተብሎ የሚጠረጠሩበት የሙስና ወንጀሎች

 

Wednesday, November 1, 2017

ህወሃት ከየመን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን እንጂ የታገሉለትን አላማ መጥለፍ አልቻለም

Print Friendly, PDF & Email
(ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌ)
ዘረኞቹ ህወሃት ወያኔዎች የምንወዳትን ኢትዮጵያ ሀገራችንን ደግመው ደጋግመው እንዳያደሙት የህዝባችን መከራና ስቃይ እንዲያቆም ገዳዮቻችንን አጥፊዎቻችንን ሊፋረዳቸው በህይወቱና በቤተሰቦቹ የጨከነ የስርዓቱን የውድቀት ምዕራፍ ወደፊት ያፋጠነ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኃላ የምንመለስባት ሌላ ኢትዮጵያ እንደሌለን እውነታውን አስረግጦ ያስገነዘበን አንዳርጋቸው ፅጌ ዛሬ በወያኔ ህወሃት ውድቀት ዋዜማ ልናስታውሰው ይገባል። ዳኛውም ዝንጀሮ ፍርድ ቤቱም ገደል እምን ላይ ተሁኖ ይነገራል በደል እንዲሉ በሀገራችን ውስጥ ምንም ዓይነት ፍትህ እኩልነትና ዲሞክራሲ እንደሌለና ዜጎች በመናገራቸው የሚታሰሩበት የሚገደሉበት በዘራቸው ምክንያት እንደ ጠላት የሚፈረጁበት ከአንድ አካባቢ የመጡ ሰዎች ብቻ ሀገሪቱን ኢኮኖሚዋን ስልጣኑን ተቆጣጥረው ሌላውን ኢትዮጵያዊ የበይ ተመልካች አድርገው ወያኔዎች ሲጨርሱት ሲያስፈልጋቸው በጥይት ሲደፉት ይህንን እውነት ቀድሞ የተረዳው ያስቆጣው ያንገበገበው አንድአርጋቸው ፅጌ ፍትህ በዛች ሀገር ላይ እንዲሰፍን በማለት የኔ የሚለውን ነገ ሁሉ ላይ ጨክኖ ህወሀት (ወያኔን) ሊፋለም እስከ ህይወት መስዋአትነት ሊከፍል እርሱ ሞቶ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ነፃ ሊያወጣ ሁሉን ጥሎ ሜዳ ገብቶ አምባገኑን የወያኔ ስርዐትን ሊታገል የወሰነና የታገለ ሁሌም በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ያለ ታላቅ ታጋይ ነው አንድአርጋቸው ፅጌ፡፡
እርሱ ነዶ ብርሀን ሆነ የድርሻውን ያለውን ሁሉ ለአንዲት ኢትዮጵያ ከፈለ። አምባገነኑ ስርዐት የአንዳርጋቸው ፅጌን አቅምና ችሎታ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ እንቅልፍ ነስቶትና ስጋቱንም ከጫፍ አድርሶት እንደነበር ግልፅ ነው፡፡ ይህንን ታላቅ ታጋይ ወጥመድ ውስጥ ለማስገባት የህወሀት (ወያኔ) የስለላ ተቋም በሚልዮን የሚቆጠርን ዶላር ከማውጣት ጀምሮ ብዙ ድካምና ዋጋ እንዳሰከፈለው ግልፅ ነው ለዚህም ነው በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሀገራትን አቋርጦ በመሄድ ጠለፋን ያካሄደው የታጋይ አንድአርጋቸው ፅጌን ተፅእኖ ፈጣሪነትና ለሕወሀት ወያኔ ራስ ምታት እንደነበር የሚያሳይ ግልፅ ትእይንት ነው።
አንድአርጋቸው ፅጌ ዛሬም ቢሆን በልባችን ውስጥ ያለ ጀግና ነው ባለው ፅኑ አቋምና ቆራጥነት አልበገሬነት የወያኔን አምባገነንና አፋኝ ስርዐትን እንቅልፍ የነሳ የቁርጥ ቀን ልጅ እንዲሁም የኢትዮጵያዊያን ባለውለታ ነው፡፡ ለሁሉም ነፃነት ናፋቂና ታጋይ ኢትዮጵያዊ ለትግል ጉዞ አርአያ በመሆን የቆራጥነትን ጥግ ያሳየ መሪ ነው፡፡
አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ ከማንም በተሻለ ሁኔታ የወያኔ (ሕወሀት) መሰሪ አሰራርን ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ኢትዮጵያ ሀገራችንን ወደ ድቅድቅ ጨለማ እየከተትዋት እንደሆነ የተረዳ ሰው ነው ዛሬ ላይም ለነፃነት፣ ለአንድነት ፣ ለዲሞክራሲ መከበር የምንታገል ኢትዮጵያዊያን ትግል ማለት ምን እንደሆነ በደንብ የተረዳነው ከአንድአርጋቸው ፅጌ የህይወት ቆራጥነት ነው ለነፃነት የሚከፍሉ መስዋዕትነት ግራ ቀኝን ማየት መመልከት አይጠይቅም፡፡ በጠቅላላ ትኩረት እና ሀሳብን ግብ ላይ ማድረግን ብቻ ነው የሚፈልገው።
ይህ አጥፊ ስርዐት ላለፉት 26 አመታት ኢትዮጵያዊያን ላይ የቀበራቸው ፈንጂዎች ኢትዮጵያዊያን ላይ ሳይሆን ራሱ ላይ እያፈነዳ እየፈጀው ይገኛል። ጀግናው ታጋይ አንድአርጋቸው ፅጌን ቢያስሩም እርሱን የቆመለትን አላማ ማሰር አልቻሉም ለዚህም ነው ከሃገር ውስጥ ሆነ ከውጭ ሀገራት ወያኔን ገዝግዞ ሊጥለው የደረሰው አዲሱ ነፃነት ፈላጊው ትውልድ ያነገበው የፍትህ የዲሞክራሲ ጥያቄና ስርዐቱንም ከስልጣን የማስወገድ ትግል አቶ አንድአርገቸው ፅጌ ዋጋ የከፈለለትና ማየት የሚናፍቀው የነበር ነው ዛሬ ላይ ግን የእርሱ ህልም እውን ሊሆን የወያኔ የከፋፍለህ ግዛ ዘመን ሊያበቃ ዘረኝነቱም ሊቋጭ ቀብሩ ሊፈፀም 11ኛ ሰዐት ላይ እንገኛለን፡፡
የነፃነት አባት የሆነውን አንድአርጋቸው ፅጌና ሌሎች ብዙ ዋጋ የከፈሉ ኢትዮጵያዊያንን የታሰሩ የተገደሉ አሁንም ድረስ በየ እስር ቤቱ የሚገኙትን ጨምሮ ሁሉንም ማስታወስ ያስፈልጋል፡፡ ሃገራችንን ኢትዮጵያን ሕወሀት ወያኔ አጥፍቶ ሳይጨርሳት ታጋይ አንድአርጋቸው ፅጌ እና ከፍተኛ የተቀዋሚ አመራሮችን ጨምሮ ህዝብን በማደራጀት እንዲሁም በማስተማርና ግንዛቤው እንዲጨምር በማድረግ የእያንዳንዳቸውን ድርሻ ቀድመው ተወተዋል ዛሬ የምናየው ህዝባዊ እንቢተኛነትና የነፃነት ትግል በእነ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ የመመካከርና የመተባበር አጀንዳ የመጣ ውጤት ነው፡፡
አሁን በምናየው የሃገራችን ሁኔታ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲያሸንፍ አንድነት ሀይል እንደሆነ ዘረኛውንና አሸባሪውን የወያኔ ስርዐት በዘረጋው የመከፋፈል እና የመበታተን ሃሳብ ውጤታማ እንዳይሆን ይህንን የሕወሀት (ወያኔ) ሴራ ቀድሞ በማጋለጥ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌ ዋነኛና ቀዳሚ ነው፡፡
አንድአርጋቸው ፅጌ ለሃሩና ለወገኑ ቆመ እንጂ ወገኑንና ሀገሩን ለገንዘብና ለንዋይ አልሸጠም ለግል ክብሩ አልተጨነቀም የኢትዮጵያ ህዝብን እንደ መዥገር ከተጣበቀበት ስርዐት ለመገላል የከፈለውን ዋጋ እንዲሁም ለዜጎች መብትና ነፃነት መከበር የነበረውን አስተዋፅኦ የትግል አጋሮቹና ኢትዮጵያዊያን ጠንቅቆ ያውቃል፡፡
የወያኔ (ሕወሀት) ግፍና በደል የህዝባችን ሮሮ ማብቂያ ዋዜማ ላይ የደረስነው ቆራጥና ለአላማው ብርቱ የነበረው አንድአርጋቸው ፅጌ ያነገበውን አላማ ይዘን በፍጥነት በመጔዝ ስለቻልን ነው ከዚ ቡሃላ ያረጀው ስርዐት ምንም እድል ፋንታ የለውም በኢትዮጵያ ህዝብ እምቢተኛነት የተሸነፈ ነው፡፡ አርቆ መቅበር ብቻ ነው የሚያስፈልገው።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!