Thursday, March 31, 2016

የወያኔ የደህንነት ተቋም በመረጃ ድርቅ ተመታ:: ዳግም ግምገማ ሊገባ ነው:: Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

 - ለደህንነት ተቋም ቢሮ ቅርብ የሆኑ ምንጮች የኦሮሚያ ክልል የሕዝብ ተቃውሞ ከፈነዳ በኋላ ባሉት ጊዜያት በመላው ሃገሪቱ እንደ ውሃ ይፈስ የነበረው የመረጃ አገልግሎች በ75 በመቶ መቀነሱን እና ሕዝቡ ለሕወሓት የደህንነት ሃይሎች እና ለጸጉረ ልውጦች ያለው ማግለል እና መጠራጠር ችግር በመፍጠሩ እንዲሁም ከብኣዴን እና ኦሕዴድ የወጡ የደህንነት አባላት የሚያመጡት መረጃ ፍሬ አልባ እና ተራ በመሆኑ የደህንነት ቢሮው በመረጃ ድርቅ መመታቱን እና እንቅስቃሴው በሕዝብ ጫና መቀዝቀዙን የደህንነት ተቋሙ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::በሹሞች እና በተራ አባላት መካከል ዘርን መሰረት ያደረገ ቅርርቦሽ እንዲሁም በሕወሓት የደህንነት ሹሞች እና በሌሎች ብሄር የደህንነት አባላት መካከል ጥርጣሬ እየሰፋ መምጣት በዘር ላይ የተመረኮዘ ጥቅማ ጥቅም ክፍፍሎሽ የአማራ ደህንነት አባላትን ማግለል በኦሮሞ ወጣቶች ላይ የደረሰው ግፍ የኦሕዴድ የደህንነትና ጸጥታ ሃላፊዎችን መወንጀል መጀመሩ የደህንነት ቢሮው መታመሱን እና በመረጃ ድርቅ መመታቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::
ከወራት በፊት የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ አስራ ስምንት የትግራይ ተወላጆች ከአዲስ አበባ ተነስተው በአልታዘዝ ባይነት ወደ መቀሌ መቀየራቸው ጥያቄ ያስነሳ ሲሆን ለሃገር የሚሰሩ አባላት ለሹሞች የግል ጉዳይ አልታዘዝ ስላሉ ብቻ ከደረጃቸው ዝቅ ብለው የማይሆን ቦታ ላይ መመደባቸው ጥያቄ ቢያስነሳም ሹሞቹ ለአሸባሪ ድርጅቶች ተባባሪ የሆኑ ሲሉ አባላቱን ወንጅለዋል::በሃገሪቱ በሕወሓት የበላይነት የተያዘው የደህንነት ተቋሙ ከሹሞቹ እና በጥቅማ ጥቅም በዝምድና በአብሮአደግነት እና እከክልኝ ልከክልህ በቡድን ከተያያዙ የደህንነት አባላት ውጪ በሃገር ጉዳይ በስራ የተሳሰረ መረቡ መላላቱን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::መረጃ አነፍናፊዎች እና የመንደር መረጃ አቀባዮች ራሳቸውን እያራቁ መሆኑ ታውቋል::
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜና የደህንነት ተቋሙ አሰልጣኞች የሆኑት አቶ ሰለሞን አስራት እና አቶ በትረ መንግስተአብ የስራ መልቀቂያ አቅርበው ወደ ሚኖሩበት አውሮፓ መመለሳቸውን የደህንነት ምንጮች የጠቆሙ ሲሆን አዳዲስ የወታደራዊ እና የሲቭል ደህነት እና ስለላ አሰልጣኦችን ለመቅጠር የደህንነት ቢሮው ከአለም አቀፍ የሴኩሪቲ ደላሎች ጋር እየተነጋገረ መሆኑ ታውቋል::የደህነት ተቋሙ በመረጃ ድርቅ መመታቱን ተከትሎ ዳግም ወደ ግምገማ ለመግባት ዝግጅት ላይ መሆኑን ምንጮቹ ተናግረው ምናልባት በመጪው ወር አጠቃላይ ግምገማ እንደሚደረግ የገለጹት ምንጮች በተቋሙ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን/በጥርጣሬ መተያየት ለስራ ደንታቢስ መሆን ስርኣቱ የመጨረሻው ምእራፍ ላይ መሆኑን በግልኣ ይጠቁማል ብለዋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment