
(ዘ-ሐበሻ) ባለፈው ሳምንት ዘ-ሐበሻ አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌን ኢትዮጵያ ከእግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት ማባረሯን ከዘገበች በኋላ ዛሬ ፌዴሬሽኑ በይፋ አሰልጣኙን ማባራሩን ገልጿል:: የብዙዎች ጥያቄ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ማን ይረከብ ይሆን? የሚለው ነበር:: እንደ ዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘገባ ከሆነ የቀድሞው የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይሌ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኖ ተመርጧል::
በ1977 ዓ.ም የብሔራዊ ቡድናችን አምበል የነበረው አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የመከላከያ ስፖርት ክለብን ከ2004 ጀምሮ ሲያሰለጥን ቆይቷል:: ገብረመድህን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ 2 ጨዋታዎች የቀሩትን ብሔራዊ ቡድናችንን ይዞ እነዚህን ጨዋታዎች እንደሚያደርግም ይጠበቃል::
ገብረመድህን ኃይሌ የቅዱስ ጊዮርጊስ ኮከብ ተጫዋችም ነበር::
No comments:
Post a Comment