በፈትያ አንዋር
ዓመት በዓል ከመድረሱ ሳምንት በፊት ጀምሮ የተለያዩ ውክቢያዎች፣ ፈንጠዚያዎች እንዲሁም ደስታና ሳቅ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ሀዘንም ሊኖር እንደሚችል እሙን ነው፡፡
ዓመት በዓል ከመድረሱ ሳምንት በፊት ጀምሮ የተለያዩ ውክቢያዎች፣ ፈንጠዚያዎች እንዲሁም ደስታና ሳቅ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ ሀዘንም ሊኖር እንደሚችል እሙን ነው፡፡
ባሳለፍነው የፋሲካ በዓል ዋዜማም በጣም አስደንጋጭ ነገር ተፈጥሯል፡፡ መቼም ሰው ነንና በበዓል ዋዜማ ደስታችንን ለመግለፅ ወደተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች ማምራታችን የማይቀር ነው፡፡ በዋዜማው በአዲስ አበባ መብራት ሀይል ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሁለት የዛው አካባቢው ነዋሪዎች ሊዝናኑ በወጡበት ባልታሰበ ፀብ በሳንጃ የአንደኛው ሰው ሕይወት ሲያልፍ ሌላኛው ደግሞ ሳንባው ተወግቶ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በህክምንና ላይ ይገኛል ፡፡
የሟች ስም ለይኩን እሸቱ(ራስ ይኩኖ) ሲሆን እድሜው 35 ነው፡፡ ከወራት በፊት ከአውሮፓ ኑሮውን ትውልድ ሀገሩ ላይ ለማድረግ ነበር የመጣው ፡፡ የእሱ ጓደኛ ዳንኤል ንጉሴ ሲሆን እድሜው 36 ነው፡፡ በግል ስራ የሚተዳደር ነበር፡፡ በግድያው የተጠረጠሩት አምስት ግለሰቦች ደግሞ በፖሊስ እየተፈለጉ ሲሆን የሟች ለይኩን ስርአተ ቀብር በፋሲካ ዕለት ከተፈፀመ በኋላ ቀብርተኛው በቀጥታ ጎተራ ፔፕሲ አካባቢ ወደሚገኘው ፓሊስ ጣቢያ በማምራት ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በአስቸኳይ እንዲዝ ጠይቋል ።
የፀቡ መነሻ እንደ እንደ ሰማነው የተጎጂ ኮፋያ በጎጂዎች መወሰዱ እና ሟች ለምን ትወስዳላችሁ በማለቱ በተነሳ አምባጓሮ ነበር።የፀቡ መነሻ ምንም እንኳ አጥጋቢ ባይሆንም ለአንዳንድ ግብዞች ግን ከበቂ በላይ ነው፡፡
ከላይ የምትመለከቱት የሟች ለይኩን እሸቱ(ራስ ይኩኖ) ፎቶ ነው ።
No comments:
Post a Comment