Saturday, April 9, 2016

ጠ/ሚ/ር ሃይለማሪያም ኤርትራን ለመውረር መዘጋጀታቸውን ነግረውኛል” – የአውሮፓ ህብረት ሹሙ ጅያኒ


ከታምሩ ገዳ
የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ መንግስታቸው በጎረቤት አገር በኤርትራ ላይ የወረራ ዘመቻ ሊያደርግ መዘጋጀቱን እና የአውሮፓ ህብረት ለኤርትራ ያለውን ቀና አመለካከት ካልለወጠ /ሁኔታዎች ግፍተው ከመጡ ኢትዮጵያ የአወሮፓ ጎዳናዎችን በሰደተኞች እንደምታጨናንቃቸው አቶ ሃይለማሪያም ለአንድ የአውሮፓ ህብረት ከፈተኛ የፓርላማ አባል ሰሞኑን ማስጠንቀቃቸው ተገለጸ።
Tamriu geda
hailemariam
ይህ “የማሰጠንቀቂያ” እና የማስፈራሪያ” ገለጻ የተደረገላቸው ሰሞኑን ከ አውሮፓ ህብረት መናገሻ ከተማ ቤልጂዩም/ ብራስለስ ወደ አዲስ አበባ ለሰራ ጉብኘት ያቀኑት በህብረቱ የሶሻሊስት እና የዲሞክራት ፓርቲ አባልት ጥምረት ፕሬዜዳንት የሆኑት ጅያኒ ፒቲላ ሲሆኑ የፓርላማው አባል እና የፓርቲው መሪ በአ/አ ቆይታቸው ከአቶ ሃይለማሪያም ደሳልኝ ጋር በበርካታ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው የጠቀሰው ዘ ሁፊንግ ቶን ፖስት ድህረ ገጽ በእሮብ ሚያዚያ 6 / 2016 እኤአ እትሙ ሲያብራራው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካክል ባለፈው 1998 -2000 እኤአ ከተካሔደው ደም አፋስሽ የድንበር ይገባኛል ግጭት በሁዋላ የዘለቀው የውጥረት ደመና ዛሬም ማንጃበቡን የተናገሩት ሚስተር ጅያኒ “የተባበሩት መንግስትታት ያስተላለፈው ወሳኔን አሻፈረኝ ያለቸው አዲስ አበባ የመፍትሄ ሃሳቦች እንድታቀርብ ስትጠየቅ በአስመራ ያለው መንግስት አምባ ገነን በመሆኑ ለዚህም መፍትሄው የኤርትራ መንግስትን ማስወገድ እና ይህንንም ለማድረግ/ኤርትራን ለመውረር ተዘጋጅተናል። በለውናል ሲሉ የአውሮፓው ህብረት የሕዝብ እንደራሴው ፣የሶሻሊስት እና የዲሞክራሲ ፓርቲ ሹሙ ለዜናው ዘገባው በሰልክ ገልጸውለታል።

ሚስተር ጅያኒ ለጀርመን ራዲዮ የአማሪኛው ክፍለ ጊዜ የብራስልሱ ወኪል ይህንኑ ሁኔታ በተመለከተ ሲናገሩ ” የአወሮፓ ህብረት ለ ኤርትራ የሚያደረገው እርዳታን አቁሟል ።እርዳታው ከቀጠለ ግን ኢትዮጵያ በኤርትራ መንግስት ላይ ወረራ ለማድረግ መዘጋጀቷን እና በግዛቷ (በኢትዮጵያ ) ውስጥ የሚገኙ በ 10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣት ኤርትራዊያን ሰደተኞችን ወደ ጣሊያን እና ወደ አውሮፓ አባል አገራት እንዲጎርፉ እንደምታደርጋቸው ዝተዋል። “ሲሉ ሚስተር ጅያኒ ለዘጋቢው ተናግረዋል ። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ዛሬ ድርስ ያላቆመው “የገደብ የለሹ” ወታደራዊ ስልጠና የሚያደርገው “ኢትዮጵያ ልትወረን ሰለምትችል እራሳችንን በቅድሚያ ማዘጋጀት አለብን።” የሚል አቋም እንዳለው በሆፊንግተን ፖስት ላይ ተገልጿል። ከዚሁ ከወታደራዊ ስልጠና ጋር በተያያዘ ሰሞኑን ወደ ስልጠና ማእከል ሊወስዱ ከነበሩ ወጣት ኤርትራዊያኖች መካከል ቁጥራቸው

No comments:

Post a Comment