Saturday, November 19, 2016

የሰው ልጅ ጭካኔ ።


የሰው ልጅ ጭካኔ ።
ከሁለት ቀን በፊት በእሳት አደጋ ከሁለት ልጆቹ ጋር ተቃጥሎ የሞተው ክብረአብ ዳዊት ሁሉን በጣም አሳዝኖ እያለ አሁን ደግሞ የበለጠ የሚያሳዝን ወሬ መጣ ።
ታሪኩ እንደዚህ ነው በአዋሳ ከተማ እግር ኳስ ግብ ጠባቂ ክብረአብ ዳዊ ከለሊቱ 7 ሰዓት አካባቢ በመኖሪያ ቤቱ በተነሳ የእሳት አደጋ ህይወቱ አልፏል ።
ከብረአብ ዳዊት ብቻውን አይድለም አደጋው የደረሰበት ከሦስት አመት እና የወራት እድሜ ካላቸው 2 ልጆቹ ጋር ነበር በተኙበት ህይወታቸው ያለፈው በዚህ ጊዜ ባለቤቱ (ሚስቱ) ጉዳት አልደረሰባትም ።
ዛሬ ግን በጣም የበለጠ አሳዛኝ አዲስ ዜና መጣ በተለይ እንዴት የእሳት አደጋው ደረሰ የሚል ጥርጣሬ በፖሊስ ምርመራ ተጀመረ ።
እሳቱ እንዴት ተነሳ ወይስ ሆነ ብሎ ሰው ያደረገው ነው የሚል ጥያቄ በዛ በዚህም ከፍተኛ ምርመራ ተካሄደ ።
በጣም የሚያሳዝነው ግን እሳቱ የተነሳው ዝም ብሎ ሳይሆን በእውነትም ታስቦበት እና ተጠንቶበት ነበር ከብረአብ ዳዊትን ለመጉዳት ሰው ያደረገው ነበር ።
በፖሊስም ተጠርጣሪን በቁጥጥር ስር አደረገ
ሌላም ሳይሆን የራሱ ባለቤት ( ሚስት) ነበረች እሳቱን ያቃጠለችው ፖሊስ ካቆማት በኋላ እንዴት አድርጋ እንዳቃጠለችው አንድ ባንድ አስረድታለች ።
በጣም የሚገርመው እና የሚያሳዝነው ህፃናቶች ምን አደረጓት የሚለው ነው ።
እግዚአብሔር እንዲህ ካለ አደጋ ይጠብቀን ።

No comments:

Post a Comment