Monday, October 17, 2016

አስቸኳይ የፋይናንስ አዋጅ ሊታወጅ እንደሆነ ተሰማ። የብሔራዊ ባንክ ውጭ ምንዛሪ ካዝና ባዶ ነው።

አስቸኳይ የፋይናንስ አዋጅ ሊታወጅ እንደሆነ ተሰማ። የብሔራዊ ባንክ ውጭ ምንዛሪ ካዝና ባዶ ነው።
የኢህአዴግ ጽ/ቤት በትርምስና የእርስ በእርስ ውንጀላ ላይ ነው። በውጪ እና በሀገር ውስጥ ኢንቬስተሮች ከኤክስፖርት ይገኝ የነበረው የውጭ ምንዛሪ በ5 ወራት ውስጥ በ71.1 በመቶ በመቀነሱ ለመጀመሪያ ጊዜ የ1.9 ቢሊዮን ዶላር የገቢ ውድቀት ታይቷል። ከተጠበቀው በታች በመቀነሱ ይሄንን የህዝብ አገልግሎት ሰጪ የሆኑ የትምህርት ቤት በጀት (የመምህራን ደሞዝን ጨምሮ)፣ የጤና አገልግሎት፣ ትራንስፖርት፣ ከፍተኛ ወጪ ያስከተለው የፖሊስ ሰራዊትና የወታደሮች ደሞዝ በዚህ የበጀት ቀውስ ምክንያት በመስተጓጎሉ አዲስ አዋጅ ማስፈለጉ ተሰምቷል።
ከሁሉም አስከፊ የሆነው ከቻይና ሌሎች አበዳሪዎች ለኢንቨስትመንስት ጉዳይ ተብሎ የተገኘው ብድር 16 ቢሊዮን ዶላር በመድረሱ በመጀመሪያው የክፍያ በ2016 አመት አስከፊ የፋይናንስ ቀውስ መገባቱ ምክንያት ሆኗል። ኢትዮጵያ በአሳሳቢ የዕዳ ሽክም ከአለም 11ኛ ሆናለች። ከዚህ ባለፈ ለውድቀቱ ተጨማሪ ምክንያት የሆነው እርዳታ ሰጪ ሀገሮች በየጊዜው የሚያስገኙት የበጀት ድጋፍ እየቀነሰ በመምጣትና ወደ ሰብዓዊ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ ላይ ትኩረት በማድረጋቸው መሆኑም ጭምር ነው።

No comments:

Post a Comment