Wednesday, May 4, 2016

በርካታ ኢትዮጵያውያን የሚኖሩባት የካናዳዋ ፎርት ማክማሪ ከተማ በእሳት እየነደደች ነው



ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት
ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት
(ዘ-ሐበሻ) የካናዳ የነዳጅ ዘይት እምቅ ሃብት ያላት ፎርት ማክማሪ ከተማ በ እሳት እየነደደች መሆኑና ሁሉም የከተማው ነዋሪ ከተማዋን ለቆ እንዲወጣ መደረጉን ኤንቢሲ የዜና አውታር ዘገበ::
የከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ከተማዋን ለቅቀው በሚወጡ ሰዎች ተጨናንቆ እንደነበር የገለጸው የዜና ምንጩ በተለያዩ ካምፖች ተጠልለው እንደሚገኙ አስታውቋል::
በከተማው እየደረሰ ባለው ቃጠሎ የተነሳ ነዋሪዎች ከተማዋን እየለቀቁ ሲወጡ የ እሳቱን እና ጭሱን እያለፉ ለመንዳትና ለመሸሽ እንደተገደዱ የገለጸው የዜና ምንጩ በጠቅላላ የከተማዋ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ ት ዕዛዝ መተላለፉንም ዘግቧል::
ከትናንት ማታ ጀምሮ በከተማዋ በተነሳው እሳት በርካታ ንብረቶች ሲወድም እስካሁን በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት ስለመድረሱ የተዘገበ ነገር አላገኘንም::
 ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት

ነዋሪዎች በዚህ መልኩ ነው ከከተማዋ እየሸሹ የሚገኙት
በፎርት ማክማሪ ከተማ ቤከን ሂል መንደር 80 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች በቃጠሎ ነደው ወድመዋል:: መላው የካናዳ የ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች ከተማዋን ለማትረፍ እሳቱንም ለማጥፋት እየተረባረቡ ነው::
በሰሜን አልበርታ ካናዳ ግዛት ስር የምትገኘው ፎርት ማክማሪ ከተማ የሃገሪቱ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ማውጫ ከተማ ስትሆን በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራዊያን እንደሚኖሩባት ይታውቀዋል::

No comments:

Post a Comment